የእስክንድርያ ፖፕ እና የመንበረ ማርቆስ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎድሮስ ዳግማዊ የኢትዮጵያ ጉብኝት መርሐ ግብር

pat-abune-mathias-and-pope-abune-tawodros1
፻፲፰ኛው የእስክንድርያ ፖፕ እና የመንበረ ማርቆስ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎድሮስ ዳግማዊ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ባደረጉላቸው ወዳጃዊ ጥሪ መሠረት ባለፈው ፳፻፯ ዓ.ም.፣ ከጥር ፩ – ፯ ቀን ድረስ በግብጽ ኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የስድስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በጉብኝታቸው ማጠናቀቂያ ላይ በቀጥታ ስርጭት ለብዙኃን መገናኛ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎድሮስ በ፳፻፰ ዓ.ም. የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ላይ እንዲገኙ ጋብዘዋቸዋል፡፡ ግብዣውን የተቀበሉት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎድሮስ፣ መስከረም ፲፬ ሌሊት አዲስ አበባ የገቡ ሲኾን ከዛሬ መስከረም ፲፭ እስከ ፲፱ ቀን ድረስ የአምስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ያደርጋሉ፡፡

ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት እና ከኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት እንደተገኘው፣ የቅዱስነታቸው የጉብኝት መርሐ ግብር የሚከተለው ነው፡፡


  • ቅዱስነታቸው መስከረም 14 ቀን 2008 ዓ.ም. ከሌሊቱ 9:00 ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በሚደርሱበት ጊዜ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት እና የፕሮቶኮል ባለድርሻ አካላት አቀባበል ይደርግላቸዋል፡፡
  • Ethiopia-Mathias-I-Egypt-Pope-Tawadros-II-meet-in-Cairo-2ቅዳሜ መስከረም 15 ቀን፣ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል፣ አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ሓላፊዎች፣ የአዲስ አበባ አድባራት እና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ መዘምራንና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በተገኙበት፣ ‹‹የእንኳን ደኅና መጣችኹ›› ፕሮግራም ይከናወናል፤ በዚኹም ዕለት ከሚመለከታቸው የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ይወያያሉ፡፡
  • እሑድ መስከረም 16 ቀን፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎድሮስ ካልዕ በቦሌ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ካቴድራል ተገኝተው ሥርዐተ ቅዳሴውን በመምራት ጸሎተ ቅዳሴው ይፈጸማል፡፡ ከቁርስ እና ከምሳ ዕረፍት በኋላ በመስቀል ደመራ ክብረ በዓል ላይ ለመገኘት በክብር ታጅበው ወደ ዐደባባዩ ያመራሉ፤ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ጋር በመኾን ያከብራሉ፡፡
  • ሰኞ መስከረም 17 ቀን፣ በርእሰ አድባራት ወገዳማት አኵስም ጽዮንና በታሪካዊ ቦታዎች ኹሉ ጉብኝት ያደርጋሉ፡፡ ከሰዓት በኋላ ደግሞ የጎንደርን ታላላቅ አድባራት እና ታሪካዊ ቦታዎች ይጎበኛሉ፡፡
  • ማክሰኞ መስከረም 18 ቀን፣ በደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ጉብኘት ይደረግና ወደ አዲስ አበባ መልስ ኾኖ ከተወሰነ ዕረፍት በኋላ በሒልተን ሆቴል የራት ግብዣ ይደረጋል፤ የስጦታ መርሐ ግብር ይካሔዳል፡፡
  • ረቡዕ መስከረም 19 ቀን፣ ወደ ታላቁ ደብረ ሊባኖስ ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም አምርተው ጉብኝት ያደርጋሉ፡፡ ከዚኹ መልስ በጌቴሰማኔ ቤተ ደናግል ወጠባባት ገዳም ከመነኰሳዪያት ጋር አጭር ውይይት ይካሔዳል፤ ከቤተ ደናግሉ የሥራ ውጤቶች ስጦታ በገዳሙ ከተበረከተ በኋላ ወደ አዲስ አበባ ጉዞ ይደረጋል፡፡
  • በዚኹ ዕለት በጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል፣ የሰማዕቱ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ኹለተኛ ፓትርያርክ መካነ መቃብር ጸሎት ይደረጋል፡፡ በመጨረሻም ከመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ውይይት ከተደረገ በኋላ የኹለቱም ቅዱሳት ሲኖዶሳት አባላት ዝግ የኾነ ትውውቅ እና አጭር ውይይት ያደርጋሉ፡፡
  • ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና የተወሰኑ የመንበረ ፓትርያርክ ሓላፊዎች በተገኙበት ቅዱስነታቸው ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጋር በቅዱስ ሲኖዶስ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከ10፡00 – 12፡00 ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣሉ፡፡
  • ከጋዜጣዊ መግለጫው በኋላ የጋራ የፎቶ መርሐ ግብር ይደረጋል፡፡ በዚኹ ዕለት ምሽት 3፡00 ይፋዊ የአሸኛኘት ሥነ ሥርዐት በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ይኾናል፡፡
Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s