ፓትርያርኩ እስከ ነገ አቋማቸውን የሚያሳውቁበት የማሰላሰያ ጊዜ ተሰጣቸው

ከንግግራቸው በተፃራሪ በአማሳኞችና በተሐድሶ መናፍቃን ተጽዕኖ ውስጥ ወድቀዋል የተጽዕኖው አስጊነት ምደባውን አስፈላጊ እንዳደረገው በምልዓተ ጉባኤው ታምኖበታል ፓትርያርኩ፣ “ሌላ አለቃ ልታስቀምጡብኝ ነው ወይ?” በሚለው ተቃውሟቸው ውለዋል በተቃውሞ ከጸኑ፣ ጉባኤው በአብላጫ ድምፅ ወስኖበት ሌላ ሰብሳቢ በመምረጥ ይቀጥላል * * * ቅ/ሲኖዶስ፣ የመጨረሻው መንፈሳዊ እና አስተዳደራዊ ሕግ አውጭ እና ወሳኝ አካል ነው ሕጎችን ያወጣል፤ ያሻሽላል፤ ይሽራል፤ የአስተዳደር መዋቅርን ደረጃና ተጠሪነት ይወስናል በእንደራሴ ምደባ ጉዳይ የሚያሳልፈው ውሳኔም፣ የሕገ ቤተ ክርስቲያኒቱ አካል ይኾናል ፓትርያርኩን በአመራር ለማገዝ ለሚሾመው እንደራሴ ምደባ፣ ዝርዝር ደንብ ይወጣል * * * ፓትርያርክ የሚባሉት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ የቤተ ክርስቲያን ካህናትና ምእመናን አባት ናቸው የፓትርያርክነት/ርእሰ ሊቃነ ጳጳስነት ሥልጣናቸው የአመራር እንጂ የክህነት ደረጃ አይደለም ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ጠብቀው ያለአድልዎ የማስተዳደር እና የመምራት ሓላፊነት አለባቸው ቤተ ክርስቲያንን ማስነቀፋቸውና ታማኝነት ማጣታቸው ከተረጋገጠ ከሥልጣናቸው ይወርዳሉ * * * በዛሬ፣ ግንቦት ፳፪ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም. ከምደባው ጋር በተያያዘ ከተካሔደው ውይይት የሚጠቀሱ፡- ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፡- “በሕጉ እንደራሴ ይመደብ የሚል ሕግ የለም፤ ከሕጉ ውጭ ነው፤ ሕጉ ይከበር፤ እኔስ ምን አደረግኋችኹ? እየሠራኹ አይደለም ወይ? ከእኔ በላይ ሌላ አለቃ፣ ሌላ ባለሥልጣን ልታስቀምጡ ነው ወይ?” ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፡- “ምልዓተ ጉባኤው÷ ሕግ የማውጣት፣ የወጣውን የማሻሻልና የመሻር ከፍተኛ ሥልጣን አለው፤ ውሳኔውም እንደ ሕግ ይሠራል፤ የቅዱስነትዎም ተጠሪነት ለቅዱስ ሲኖዶስ ነው፤ ሓላፊነትዎ ከባድና ክፍተቱ ብዙ ቢኾንም የተሰጠዎትን ከመናገር በቀር ምንም አልሠሩም፤ ምክርዎም ከአማሳኞችና ከመናፍቃን ጋር ነው፤ ከሕገ ቤተ ክርስቲያን ውጭ እስከ ሀገረ ስብከትና አጥቢያ ድረስ ወርደው ሥራ አስኪያጅ፣ ጸሐፊ እና ሒሳብ ሹም ይመድባሉ፤ የምንሾመው የሚያግዝ እንደራሴ ነው፤ አንድ ብቻ ሳይኾን ብዙ ሊያስፈልግ ይችላል፤ ከዚኽ በፊትም በየዘመነ ፕትርክናው ሠርተንበታል፤” እንደ ጉባኤው ሕግና ደንብ፣ አጀንዳው በድምፅ ብልጫ ሊወሰንበት ይገባል፤ ምልዓተ ጉባኤው 50 ለ1 ኾኖ መቀጠል የለበትም፤ ፕትርክናዎን ከቅዱስ ሲኖዶስ እና ለቤተ ክርስቲያን ከሚያስቡ ጋር ሊሠሩበት እንጂ ከማይመለከታቸውና ከሚያበጣብጡን ጋር ሊመክሩበት አይገባም፤ ካልኾነ ሥልጣኑ የቅዱስ ሲኖዶስ ነው፤ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጋር መሥራትዎ ግድ ነው፤ ሕዝብ ይግባ፤ መንግሥት ይግባ ማለት ሕገ ቤተ ክርስቲያንንና ሕገ መንግሥቱን አለማወቅ ነው፤ ማንም በማንም መግባት አይጭልም እኛም አንፈልግም፤ ቤተ ክርስቲያን በሕዝብ መካከል ኾና ኹሉንም በአንድነት የምትጠብቅ ችግር ፈቺና አስታራቂ ተቋም ናት፤ እነ እገሌ ይግቡ፤ እን እገሌ ይምጡ የሚለው አስተሳሰብ የመከፋፈል አጀንዳ ያላቸው ሰዎች ከውጭ የሚረጩት ነው፤ ለረጅም ጊዜ በቤተ ክርስቲያንና በብፁዓን አባቶች ለ፤ይ ሲዘምቱ የቆዩ መናፍቃን፣ ስለ አጀንዳው የሚያሰራጯቸው አሉባልታዎች፣ ፍጹም ሐሰት እና ኾነ ተብሎ የጉባኤውን አቅጣጫ ለማስለወጥ የሚያፍሷቸው ናቸው፡፡

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s