ኢትዮጵያ የኤርትራ ተቃዋሚዎችን እና “ጃሃዲስቶችን “ለማስታጠቅ ፣ ለመደጎም ቃል ገባች

Tamiru Geda's photo.

ኢትዮጵያ የኤርትራ ተቃዋሚዎችን እና “ጃሃዲስቶችን “ለማስታጠቅ ፣ ለመደጎም ቃል ገባች

ይሔ “የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው ቅኝት”ከየትኛው መንገድ ያደረሰን ይሆን?

መቀመጫውን በፈረንሳይ /ፓሪስ በማድረግ ምስጢራዊ ነክ በሆኑ ዲፕሎማሲያዊ ፣ ወታደራዊ እና የኢንቨስትምነት ጉዳዮች ዙሪያ የሚያውጠነጥነው “አፍሪካ ኢንተለጀንሲ” የተባለው መጽሄት በቅርቡ እንደዘገበው በአዲስ አበባ እና በአሰመራ ገዢዎች መካከል ቀደም ሲል የተፈጠረው ቅራኔን ተከተሎ የ ኢ ሕ አዲግ መንግስት የኤርትራው አቻው ተቃዋሚዎች ጥምረት የሆነው የኤርትራ ብሔራዊ ካውንስል ለዲሞክራሲ እና ለለውጥ (Eritrean National Council for Democractic Change,ENCDC) ለማቀራረብ ጥረት በማድረግ ላይ ነው ሲል አሰነብቧል ።
ዘገባው የ ኢ ሕ አ ዲ ግ መንግስት የ ኤርትራ ተቃዋሚዎችን በአዲስ መልክ ለመቅረብ ከወሳኔ የደረሰበትን ምክንያት ዘገባው ሲያስረዳ “በቅርቡ በ ኢትዮ- ኬኒያ ድንበር አካባቤ የኤርትራ ተቃዋሚ አባላት መታስራቸውን ተክትሎ ነው።” የተባለ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ የቀድሞ የአስመራ መንግስት ደፕሎማቶች እና በውጪ የሚገኙ ተቃዋሚዎች ያዋቀሩት የኤርትራዊያኖች ብሄራዊ የ ውይይት መድርክ(Eritrean Forum for National Dialogue ,EFND/Medrek) አንሰሳሸነት በኬኒያው ናይሮቢ ባለፈው ሃዳር 28 እስከ 29 የቀድሞው ጄነራል መሰፍን አማን የመሩት አስር የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካዮች የተካሄደው ስብሰባ በመንተርሰስ አጋጣሚውን የተጠቀመው የወቅቱ የኢትዮጵያው ገዢ መንግስት ፣ኢሕ አዲግ፣ ለኤርትራ ተቃዋሚዎች ቀደም ሲል ሲያቀማማ የነበረውን የገንዘብ እና የሎጀስቲክ እገዛውን በአዲስ መልክ ለማጠናከር ቃል መግባቱን የጠቀሰው ዘገባው ኢሕ አዲግ ለአስመራ መንግስት ተቃቃሚዎች “እረዳልሁ” ብሏል የተባለው የገንዘብ ምንጩ ፣መጠኑ እና የሎጀሰቲክ ደጎማው አይነት በተመለከተ ለጊዜው በውል አልተገለጸም ። በአንዳንድ የአሰመራ መንግስት ደጋፊዎች እይታ ከእነዚህ ተደራጁ እና የኢ ሕ አዲግ ልገሳ ሊቸራቸው ነው ከተባሉት የኢርትራ ተቃዋሚዎች መካከል እራሱን የኤርትራ እስላሚክ ጅሃድ እንቀሰቃሴ/Eritrean Islamic Jihad Movemnet በሎ የሚጠራው ቡድን ቢን ላዲንአ ከመሰረተው አክራሪው የአልቃይዳ ቡድን ጋር ቁርኝት አለው እስከማለት ደርሰዋል። ይህ አባባል እና ጥርጣሬ ግን በድርጁቱ በኩል ምላሽ አልተሰጠበትም አሊያም በነጻ ምንጮች አልተረገጋጠም።
የዛሬ 25 አመት የደርግ መንግስትን በመገርሰስ በአ/አ እና በእስመራ ላይ የራሳቸውን መንግስታት በመመሰረት በጦርነት፣ በችግር እና በሰደት ይታወቅ የነበረው የአፍሪካ ቀንዱ አካባቢን በአንጻራዊ ሰላም ተምሳሌነት ለመቀየር ቃል የገቡት ኢ ሕ አዲግ እና ሻቢያ ዛሬ ለሕዝባቸው የሰላም ፣የመረጋጋት እና የእድገት ባለቤት እንዳደረጉት ቢሰብኩም በገሃዱ አለም ያለው ሁኔታ ግን በተቃራኔው እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ ።
በተለይ ደግሞ በድንበር ይገባኛል ጥያቄ ሳቢያ እኤ አ ከ 1998 እስከ 2000 በዘለቀው ውጊያ ሳቢያ ከሁለቱም ሕዝቦች ውስጥ ከሰባ ሺህ በላይ ወጣቶች ሕይወታቸውን የገበሩበት ( በዚህ አጋጣሚ ፕ/ት ኢሳያስ አፈወርቂ በሰሞነኛው ንግግራቸው ከ 20ሺህ በላይ ወጣት ኤርትራዊያኖች ማለቃቸውን/መሰዋት መሆናቸውን በግላጭ አምነዋል) ዛሬም ድረስ የጦርነቱ ዳመና ሳይገፈፍ “ጦርነት የለም ሸላምም የለም “ በሚል ፍልስፈና የተዘፈቁት ሁለቱም ገዢዎች ድንበሮቹ በወታደሮች እና በከባድ መሳሪያዎች በሚጠበቁበት በእሁኑ ወቅት አንዱ የሌላኛውን ተቃዋሚዎችን በማደረጀት፣ በማስታጠቅ እና መንገድ በመምራት ከበትረሰልጣኑ ለማስወገድ የሚያደርጉት እርብርቦሽን ለተመለከተ “ እውን እነዚህ በውስጣቸው ደሞክራሲያዊ ባህሪይ በጭራሽ ያለተላበሱት የአ/አ እና የአሰመራ አምባ ገነን ገዢዎች ለአካባቢው ሰላም ፣ መረጋጋት እና ዲሞክራሲያዊ ስር አት መሰፈን ካላቸው ጽኑ ምኞት የተነሳ ወይስ ‘የጠላቴ ጠላት… ‘ከሚለው እና ዛሬ አላማችንን ብትንትኗን እያጠፋ ካለው የመጠላለፍ ቅኝት ላለመውጣት አሰበው ነው?” የሚሉ ጥያቄዎችን በሰከነ መንፈስ የሚያስተጋቡ ወገኖች ቁጥራቸው ቀላል አይደለም።

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s