የኢትዮጵያ አንጋፋ ሯጮች በሪዮ ኦሎምፒክ ተሳታፊ አትሌቶችን ምርጫ አወገዙ

የኢትዮጵያ አንጋፋ ሯጮች በሪዮ ኦሎምፒክ ተሳታፊ አትሌቶችን ምርጫ አወገዙ

ግንቦት ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በላቲን አሜሪካዋ በብራዚል በሚካሄደው 31ኛው የሪዮ ኦሎምፒክ ላይ አገራቸውን ወክለው የሚቀርቡትን አትሌቶች ምርጫ ላይ አግባብ ያልሆነ ስህተት መፈፀሙን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ማኅበር አንጋፋ ሯጮች በአዲስ አበባ ስታዲዮም ባደረጉት ስብሰባ አቋማቸውን አሳወቁ።

አንጋፋዎቹ ሯጮች ሻለቃ ኃ/ገብረስላሴና አሰፋ መዝገቡ ጨምሮ ሌሎችም ታዋቂ አትሌቶች በተገኙበት በአትሌቲክስ ማኅበሩ ምርጫና በሪዮ ኦሎምፒክ ዝግጅት ላይ የተሰማቸውን ቅሬታ ገልፀዋል። በኦሎምፒክ የሶስት የወርቅ ሜዳሊያ ባለድሉ አንጋፋው ሯጭ ቀነኒሳ በቀለ ከምርጫ ውጪ መሆኑ በፌደሬሽኑ በኩል የተደረገ አድሎዋዊ አሰራር እንደሆነ ከተሰብሳቢዎቹ አስተያየቶች ተሰጥተዋል። አትሌት ዳዊት ይህን አስመልክቶ ቅሬታውን ለተሰብሳቢዎቹ አሰምቷል።

አትሌት ገ/ግዛብሔር ገ/ማሪያምም አትሌቲክስ ፌደሬሽኑ እንደ አዲስ በባለሙያ መመራት እንዳለበትና የአተሌቶች ማኅበር በፌደሬሽኑ ፈቃድ የሚበትን ሕገ ደንብ መኖሩ አትሌቶቹን የመደራጀት መብት ይጋፋል ብሏል። ሻለቃ ኃ/ገብረስላሴ በበኩሉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ የውጤት ቀውስ ውስጥ እንዳለና በሪዮ ኦሎምፒክ ከኬኒያ የተሻለ ድል ማስመዝገብ እንደማይቻል በመጥቀስ፡ በ10 ሺና 5 ሺ ሜትር ወንዶች ውጤት መጠበቅ የማይታሰብ ነው ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ማኅበር ምርጫን የተቃወሙት የአትሌቲክስ ማህበር አባላት ወኪሎችን በመምረጥ ስብሰባቸው ፈጽመዋል። ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን የቀነኒሳ በቀለ ከምርጫ ውጪ መሆን በአድሎ እንደሆነ መዘገባቸው ይታወሳል። ቀነኒሳ በበኩሉ ምርጫው በሙያ የተደረገ ሳይሆን ሆን ተብሎ የተወሰኑትን በመጥቀም ሌሎችን ለመጉዳት መደረጉን በሰጠው ቃለ መጠይቅ ላይ አስታውቋል።

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s