የኦሮሚያ አምቦ ዩንቨርስቲ ሁለት ኦፊሰሮች ሲገደሉ አንድ ክፉኛ ቆሰለ

በኦሮሚያ ክልል አምቦ ዩንቨርስቲ አዋሮ ካምፓስ በተነሳ ግጭት ሁለት ኦፊሰሮች ሲገደሉ አንዱ ክፉኛ መቁሰሉን የካምፓሱ የመረጃ ምንጮች ተናግረዋል፤ በኦሮሚያ ክልል እየተደረገ ያለው ተቃውሞ ያልቆመ ሲሆን በሃረርጌ በወለጋ እና በሌሎች የሸዋ ወረዳዎች ተቃውሞ ቀጥሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በዛሬው እለት እነበቀለ ገርባ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን በቦታው የነበረችው ማህሌት እንደጻፈችው የቂሊንጦ እስር ቤት አስተዳደር የሚያደርስባቸውን ሰብአዊ መብት ጥሰት እና ጫና በተያያዘ አቤቱታ አቅርበው ነበር። ዛሬ የእስር ቤቱ አስተዳደር የሚሰጠውን ምላሽ ለመስማት ነበር ቀጠሮ የተሰጠው። አስተዳደሩ ምላሽ ያለውን በፅሁፍ አቅርቧል። ምላሹን አይቶ ትእዛዝ ለመስጠት ለሃምሌ 8/2008 ቀጠሮ ተሰጥቷል። አቶ በቀለ እና አቶ ደጀኔ ካቀረቡት አቤቱታ ውስጥ ከጤናቸው ጋር የተያያዘ የሆነው ጊዜ መውሰድ ስለሌለበት ቶሎ ውሳኔ እንዲሰጥበት ጠበቃቸው አቶ አመሃ ለፍርድቤቱ ጥያቄ አቅርበው የነበረ ሲሆን የሁለቱን የጤና ጉዳይ በተመለከተ ትእዛዝ ተሰጥቷል። በቀለ እና ደጀኔ የታዘዘላቸው መድሃኒት በእስር ቤቱ ግቢ ውስጥ በሚገኘው መድሃኒት ቤት የለም ከተባለ እንኳን ከውጪ ተገዝቶ እንዲገባላቸው እንዲያደርጉ ከቂሊንጦ ለመጡ ኦፊሰሮች ተነግሯል።
በተያያዘ ደጀኔ ጣፋ እናቱ የታደሰ መታወቂያ ስለሌላቸው እስርቤት ገብተው ሊጠይቁት አለመቻላቸውን ገልፆ ወይ ችሎት ውስጥ እንዲገናኙ ወይ በጡረታ መታወቂያ መግባት እንዲችሉ እንዲፈቀድላቸው አቤቱታ አቅርቧል። ዳኛውም እንዲተባበሩት ለኦፊሰሮች ጠይቀዋል። የደጀኔ እናት የሚኖሩበት አካባቢ ቀበሌ መታወቂያቸውን ሊያድስላቸው ፈቃደኛ ባለመሆኑ ነው መታወቂያቸው ያልታደሰው እና እስካሁን ልጃቸውን ማየት ያልቻሉት።ከክሳቸው ጋር በተያያዘ ባቀረቡት መቃወሚያ ላይ ዳኞች የሚሰጡት ብይን ለማሰማት ለሃምሌ 25/2008 የተሰጠው ቀጠሮ እንደተጠበቀ ነው።

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s