በጽኑ ህመም ውስጥ የሚገኘው አቶ ሀብታሙ አያለው ያለው አማራጭ ውጭ ሄዶ መታከም ብቻና ብቻ ነው

ሰበር ዜና
በጽኑ ህመም ውስጥ የሚገኘው አቶ ሀብታሙ አያለው Colo_Rectal በሚባል ህክምና ዘዴ ካልሆነ በስተቀር ማከም እንደማይቻል በዶክተሮች ተረጋግጧል። ይህ ዘመናዊ የህክምና ቴክኖሎጂ በአህጉራችን የለም። ያለው አማራጭ ወዳለበት ሄዶ መታከም ብቻና ብቻ ነው።
የሀብታሙ አያለው የህክምና ሰነድ ለህዝብ ይፋ እንዳይሆን ማቆየታችን ይታወቃል። ይሁን እንጂ አሁን፣አሁን ሀብታሙ የራሱ (ለራሱ የሚኖር) አሊያም የተወሰኑ ጘጓደኞቹ ወይም የቤተሰቦቹ ሀብት ብቻ አይደለም። ድፍን የኢት/ያ ህዝብ እንጂ። የሚያሳክመው፣ የሚፀልየው፣ የሚንከባከበው ይህ ህዝብ ነውና። ስለዚህ እሱን የሚመለከቱ ወሳኝ እውነቶችን ባለቤቱ ለሆነው ሁሉ ማሳወቅ ከነገ ወቀሳም ይታደገኛል። እኔ ብቻም ሳልሆን እኔና ሀብታሙ፣ ባለቤቱም ሆነ የተቀሩ ጓደኞቻችን እና አማካሪዎቻችን ተስማምተናል። ይህ እንዲገለጽ የፈለገንበት ዋናው ዓላማ የዚህ አይነት የህክምና ማስረጃ (Medical Certificate) እያለ ዳኞች እንዳይወስኑ ምኑ ነው የከበዳቸው? ለሚለው ጥያቄ ፍርድ እንድትሰጡበት ነው ለኢት/ያ ህዝብ እና በተለይም ለጤና ባለሙያዎች ይፋ የተደረገው።
የፊ/ጠ/ፍ/ቤት በእቶ ሀብታሙ አያለው ጉዞ እቀባ ለይ ውሳኔውን ለማሳወቅ ዛሬ (30.10.2008) ለ7:30 በድጋሚ መቀጠሩን ግልጨ ነበር። እሁን ደግሞ የህክምና ቦርድ ውሳኔ ከሆስፒታሉ አምጡ ተባልን፤ በዳኛ ዳኜ መላኩ። እስከ መጨረሻው ተጉዘን ማስጨረስ ስላለብን ወደዚያው እያመራን ነው። በቀደመው ትእዛዝ ግን የተባልነው ያቀረብነውን ሴርትፌኬት እንጂ የቦርድ የሚል አልነበረም።
Daniel Shibeshi

Tilaye Tarekegn ZE Ethiopia's photo.
Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s