ሂውማን ራይትስ ዎች የተባለው ድርጅት ወያኔ የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ውስጥ አባል መሆኑ አሳሳቢ ነው አለ

(የፍኖተ ዴሞክራሲ ራዲዮ አጫጭር ዜናዎች)

#ሂውማን ራይትስ ዎች የተባለው ድርጅት ወያኔ የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ውስጥ አባል መሆኑ አሳሳቢ ነው አለ
#የወያኔ ልዩ ኃይሎች በኢትዮጵያ የሶማሌ ግዛት ጭፍጨፋ አካሄዱ
#በሰሜን ካሜሩን የቦኮ ሃራም አጥፍቶ ጠፊ ባፈነዳው ቦምብ ጉዳት አደረሰ
#በሱማሊያ በመንገድ ላይ በተቀበረ ፈንጅ በአውቶቡስ ሲጓዙ የነበሩ መንገደኞች ሞቱ
#በዳርፉር የተሰማራው የተመድ ሰላም አስከባሪ ኃይል ግዳጁ ለአንድ ዓመት ተራዘመ
ሰኔ 23 ቀን 2008 ዓ.ም. ርዕሰ ዜና
 ሰኔ 22 ቀን 2008 ዓም በአዲስ አበባ ከተማ በላፍቶ ክፍለ ከተማ ቀርሳ ኮንቱማ እና ማንጎ ሰፈር በሚባለው አካባቢው 200 የሚሆኑ የቤት አፍራሽ ግብረ ኃይል ፖሊሶች የነዋሪውን ቤቶች ለማፍረስ ሲሞክሩ ሕዝቡ ባደረገው ከፍተኛ ትግልና ግብግብ ፖሊሶችና የከተማው አስተዳደር አባላት እንዲሁም ነዋሪዎች የሞቱ መሆናቸውና በርካታዎችም የቆሰሉ መሆናቸው ተነግሯል። የወያኔ ባለስልጣኖች ሁለት ፖሊሶችና እንድ የወርዳው ኃላፊ የተገደሉ መሆናቸውን ይግለጹ እንጅ የሞቱትና የቆሰሉት ሰዎች ብዛት ከዚያ በላይ እንደሆነ የአይን እማኞች ይናገራሉ። በአካባቢው ከ30 ሺ በላይ ቤቶች የአሉበት ሲሆን የወያኔ መሪዎች የነዋሪውን መሬት ለመቀማት ያቀዱትን እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ቤቶቹ በሕግ ወጥ መንገድ የተሰሩ ናቸው በማለት በማለት ለማፍረስ ሙከራ ሲያደርጉ ነዋሪው መንግዶችን በመዝጋት እንዲሁም በድንጋይና በዱላ በአፍራሾች ላይ ጥቃት በማድረስ ቤቶችን ከመፍረስ ለመከላከል ሙከራ ሲያደርጉ በተነሳው ግጭት የአፍራሽ ግብረኃይል አባላት የሆኑት ፖሊሶችም ሆኑ አስተዳዳሪዎች እንዲሁም ነዋሪዎች ጉዳት ሊደርስባችው ችሏል።

File Photo

 ሂውማን ራይትስ ዎች የተባለው የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት ረቡዕ ሰኔ 22 ቀን ይፋ ባደረገው መግለጫ የወያኔ አገዛዝ በሰብአዊ መብት ረገጣ በኩል ግምባር ቀደም መሆኑን ገልጾ በተመድ የጸጥታ ምክር ቤትም ሆነ በተመድ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ውስጥ በአባልነት መመደቡ ቅሬታ ያሳደረበት መሆኑን አስታውቋል። ድርጅቱ መግለጫውን በመቀጠል የወያኔ ቡድን ጋዜጠኞችን በማሰር ሆነ የሲቪል ማህበረሰብ መብትን በመርገጥ እንዲሁም ተቃውሞን ለማፈን የሽብረተኛ ህግን እንደሽፋን በመጠቀም በኩል ከአፍሪካ ቀዳሚው አምባገነንግ አገዛዝ ነው ካለ በኋላ ለአመታት ተቃዋሚዎችን አዳክሞ ምርጫውን 100 ከመቶ አሸንፌያለሁ ያለ ቧልተኛ አገዛዝ ነው ብሎ ዘግቧል። አገዛዙ ስልጣን ላይ በቆየበት ወቅት በከፍተኛ ደረጃ የዜጎችን መብት የማፈንና የመርገጥ ታሪክ ያለው መሆኑ ግልጽ ሆኖ እያለ የተመድ የጸጥታ ምክር ቤትና የተመድ የሰብአዊ ኮሚሽን አባል ሆኗል ካለ በኋላ ድርጅቱ የወያኔ አገዛዝ የተባበሩት መንግስታት ልዩ ልዩ የልኡካን ቡድኖች ከሻዕቢያ ጋር ስለአካሄዳቸው ጦርነትም ሆነ የጦርነት ስለሚፈጽመው ሰቆቃዊ ድርጊቶች እንዲሁም በኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው ሀሳብን በነጻ ስለምግለጽ ነጻነት፤ በነጻ ስለመድራጀት ስለመሰብሰብ መብት እንዲሁም ስለሌሎች ገዳዮች ያሉትን ሁኔታዎች በአካል ለማየትና ለመገንዝብ ያቀረቧቸውን ጥያቄዎች መከልከሉን አጋልጧል፡፡ የሰብአዊ መብት ድርጅቱ በመግለጫው ማጠቃለያ ላይ የወያኔ አገዛዝ የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት እና የሰብአኢው መብት ኮሚሽን አባል መሆኑ የአለም አቀፉ ህብረተሰብ በሰብአዊ መብት ጉዳይ ላይ የሚያደረገውን ምርመራ እና ጥናት ለመከላከል ሽፋን እና መደበቂያ እንዳይሆን ጥረት መደረግ አለበት ብሏል።

 ከሶስት ሳምንት በፊት በኢትዮጵያ ሶማሌ ግዛት ጃማ ጁባድ በሚባለው አካባቢው የወያኔ ልዩ ፖሊስ አባላት 40 የሚሆኑ ዜጎችን ሴቶችንና ህጻናትን ጨምሮ የረሸኑ መሆናቸውን ሶማሌላንድ ፕሬስ የተባለው የኢንተርኔት ጋዜጣ ሰኔ 22 ቀን 2008 ዓም ባወጣው ዕትሙ ገልጿል። የወያኔው ልዩ ኃይል ግድያውን ያካሄደው የተወሰኑ የታጠቁ ሰዎች በኮንትሮባንድ ፖሊሶች የተቀማ የኮንትሮባንድ ጫትን ለማስመለስ ለወሰዱት ጥቃት የአጸፋ እርምጃ ሲወስዱ መሆኑን የዜና ምንጩ ገልጿል። ልዩ ኃይል በመባል የሚታወቁት ግለሰቦች ወታደራዊ ስልጠና የሌላቸው ቢሆንም በወያኔ ቡድን የታጠቁና የተረዱ መሆናቸው ግልጽ ነው። በየአመቱ በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር እርዳታ እየሰጡ ስልጣን ላይ ያቆየቱ የምዕራብ መንግስታት የወያኔን ግፈኛ አገዛዝ ለመግታት ተጽእኖ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ተብሏል።
 በሰሜን ካሜሩን አንድ የቦኮ ሃራም አጥፍቶ ጠፊ ባፈነዳው ቦምብ 10 ሰዎች የተገደሉ መሆናቸውን ሐሙስ ሰኔ 13 ቀን 2008 ዓም አንድ ወታደራዊ ቃል አቀባይ ገልጿል። ጥቃቱ የተፈጸመው ረቡዕ ለሐሙስ አጥቢያ ከናይጄሪያ ወሰን አካባቢ ጃካና ከተባለችው መንደር ውስጥ የቪዲዮ ፊልም ለማየት በተሰበሰቡ ሰዎች ላይ በተሰነዘረ ጥቃት መሆኑም ተግለጿል። ከሞቱት በተጨማሩ በርካታ ሰዎች የቆሰሉ ሲሆን በሆስፒታል እየተረዱ መሆናችው ተዘግቧል። ባለፈው ስድስት ወር ብቻ በቦኮ ሃራም ጥቃት 190 ሺ ካሜሩናውያን ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው የተሰደዱ ሲሆን ከናይጄሪያ ከመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ፈልሰው የመጡ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ስደተኞች አገሪቷ እያስተናገደች መሆኗ ተገልጿል።  ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 23 ቀን 2008 ዓ.ም ከሱማሊያ ዋና ከተማ ከሞጋዲሾ ወጣ ብሎ ባለ መንገድ ላይ የተጠመደ ፈንጅ በርቀት መቆጣጠሪያ አማካይነት ፈንድቶ በአንድ አነስተኛ አውቶቡስ ውስጥ የነበሩ አስራ ስምንት ሰዎች ወዲያውኑ የተገደሉ መሆናችው ታውቋል። አውቶቡሱን አጅበው ሲሄዱ የነበሩ ወታደራዊ መኪናዎች ከቦምቡ አደጋ ማምለጣቸውን የአይን እማኞች የገለጹ ሲሆን ምናልባትም የቦምቡ ኢላማ እነዚህ መኪናዎች ሳይሆኑ አይቀርም የሚል ግምት ተሰጥቷል። ለጥቃቱ እስካሁን ኃላፊነቱን የወሰደ ወገን ባይኖርም በአካባቢው ተመሳሳይ ጥቃት በማክሄድ የሚታወቀው አልሸባብ ሳይሆን አይቀርም የሚለው ግምት ከፍተኛ ነው።
 በዳርፉር ሱዳን የተሰማራው የተመድ የሰላም አስከባሪ ኃይል ግዳጁ ለአንድ ዓመት እንዲራዘም የተመድ የጸታጥው ምክር ቤት መወሰኑ ታወቀ። በዳርፉር 15 ሺ ስምንት መቶ አርባ ሶስት ወታደሮችና አንድ ሺ አምስት መቶ ሰማንያ ሶስት ፖሊሶች በተመድ የሰላም አስከባሪ ኃይል ስር የተሰማሩ ሲሆን ግዳጃቸው ለአንድ ዓመት ተራዝሞ በዚያው እንዲቆዩ የሚጠይቀው በእንግሊዝ የቀረበው የውሳኔ ረቂቅ ምክር ቤቱ ረቡዕ ሰኔ 22 ቀን 2008 ዓም ባደረገው ስብሰባ በሙሉ ድምጽ የወሰነ መሆኑ ተዘግቧል።
Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s