አርቲስት ቴዎድሮስ ተስፋዬ በትያትር ስም 4 አርቲስት ያልሆኑ ሰዎችን ወደ አሜሪካ ወስዷል በሚል ተከሰሰ

tewedros teshome

በቅርቡ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ እና አትላንታ የታየውን የቴዎድሮስ ራዕይ ትያትር ተከትሎ ብሔራዊ ትያትር አርቲስት ቴዎድሮስ ተስፋዬ ከሥራ ታገደ:: የብሔራዊ ትያትር ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ተስፋዬ ሽመልስ አርቲስት ቴዎድሮስ በቴዎድሮስ ራዕይ ትያትር ሰበብ 4 አርቲስት ያልሆኑ ሰዎችን አርቲስት እንደሆኑ በማስመሰል ለአሜሪካ ኢምባሲ ወረቀት አቅርቦ እንዲሄዱ አድርጓል በሚል ክስ እንደቀረበበትና በፖሊስ ምርመራ ላይ እንደሆነ ለቁምነገር መጽሔት ተናግረዋል::

ነገ በኢትዮጵያ የሚታተመውና የሚሰራጨው ቁምነገር መጽሔት ላይ ቴዎድሮስ ተስፋዬና የትያትር ቤቱ ዳይሬክተር ቃለምልልሳቸው የሚወጣ ሲሆን መጽሄቱ ከመታተሙ በፊት በቁንስሉ የሚከተለውን ዘገባ አስነብቧል::

‹‹በባለሙያ ስም ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እየተደረገ ስለመሆኑ ምርመራ እየተደረገ ነው››

ህገወጥ ስደት በየዕለቱ የምሰማው ከመሆኑ ጋር ተያያዞ አንደ ተራ ነገር እየተየቆጠረ ያለ ይመስላል፡፡ የዛሬ አንድ መዓት ገደማ በሊቢያ በአሸባሪው አይኤስአይ ኤስ አንገታቸውን የተቆሉ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ መነጋገሪያ መሆኑን ተከትሎ ሌሎች የህብረተሰቡን አመለካካት መቀየሪያ መንገዶች ሲዘየዱ ታይተዋል፡፡ ይህንኑ ተከትሎም በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ድጋፍ ሰጪነት በህገወጥ ስደት ዙሪያ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር አርቲስቶች ተሰርቶ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሊቀርብ የነበረው ተከታታይ ድራማ በውዝግብ ታጅቦ ተመልካች ጋር መድረስ አልቻልም፡፡

ቴአትር ቤቱ ማኔጅመንና ድራማውን ለመስራት ከተቋቋመው ኮሚቴ መሀከል እየተሰማ ያለው ውዝግብ እስከ 900 ሺ ህ ብር ወጪ ተደርጎ ጅቡቲ፤ኬኒያና ሱዳን ድረስ ተሄዶ ጥናት የተሰራበት ድራማ የውሃ ሽታ ሆኗል፡፡ ከድራማው አዘጋጆች መሀከል አንዱ የሆነው አርቲስት ቴዎድሮስ ተስፋዬ በበኩሉ ማኔጅመንቱ ለስራው እንቅፋት መሆኑንና ሰሞኑን በቴአትር ቤቱ የተጣለበትን እገዳም ህገወጥ ነው›› ይላል፡፡

የቴአትር ቤቱ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ተስፋዬ ሽመልስ በበኩላቸው ‹ከፕሮጀክቱ የገንዘብ ጥቅም ለማግኘት ተዘጋጅተው የነበሩ ሰዎች በመኖራቸው ስራው መራመድ እንዳልቻለ›› ይገልፃሉ፡፡

የህገ ወጥ ስደቱ አጀንዳ ሳይፈታም ሌላ አወዛጋቢ ጉዳይ ብቅ ብሏል፡፡ በአርቲስት ቴዎድሮስ ተስፋዬን ያካተተውና ሌሎች አርቲስቶችን ይዞ ወደ አሜሪካ በመሄድ ‹‹ የቴዎድሮስ ራዕይ ›› የተሰኘውን የአርቲስት ጌትነት እንየው ድርሰትና ዝግጅት ድራማ አሳይቶት የተመለሰው ቡድን ቴአትሩን በማን ፍቃድ ይዞ እንደሄደ አቶ ተስፋዬ ይጠይቃሉ፡፡ እንደውም ይላሉ አቶ ተስፋዬ ‹ቡድኑ ወደ አሜሪካ ሲያቀና አርቲስት ያልሆኑ አራት ሰዎችን በአርቲስት ስም ከኢትዮጵያ የተውኔት ሙያተኞች ማህበርና ከተስፋዬ አበበ የቴአትር ኢንትርፕራይዝ ደብዳቤ አፅፎ ከአሜሪካ ኤምሳቢ ቪዛ በማውጣት ከሀገር ማስወጣቱ ተደርሶበት በህገ ወጥ ስደት ድራማ ጀርባ ሌላ ህገ ወጥ ስራ በመኖሩ ፖሊስ ጥብቅ ምርምራ እያደረገ ነው› ይላሉ፡፡› ቁም ነገር መፅሔት ሁለቱንም ወገኖች አነጋግራለች፡፡

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s