የወልቃይት ተወላጆች ከአዲስ አበባና ካርቱም እየታፈሱ ነው

  የወልቃይት ተወላጆች ከአዲስ አበባና ካርቱም እየታፈሱ ነው::

የጎንደሩ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ተከትሎ የተደናበረው የወያነ አገዛዝ የወልቃይት ተወላጆችን ከአዲስ አበባ እና ካርቱን እያፈሰ በማሰር ላይ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል::ጎንደር ከተማና በአጠቃላይ በአማራ ክልል ሕዝባዊውን አመጽ ተከትሎ በአደባባይ ሰዎች በብዛት ባይታዩም ውስጥ ውስጡን ግን ሰዎች መንቀሳቀስ እንዳቃታቸውና እየታሠሩ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የአከባቢው ነዋሪዎች ይገልጻሉ::

በተለያዩ ሰበቦች የአማራውን ሕዝብ ለማጥቃት ዝግጅት እያደረገ ያለው የወያነእ አገዛዝ በጎንደር የወልቃይት ማነት ጉዳይን የሚመሩ ግለሰቦችን ለመያዝ ሃይል የተቀላቀለበት እርምጃ ለመውሰድ ሲገሰግስ በሕዝብ ሃይል አደጋ ተጥሎበት ከጥቅም ውጪ መሆኑን በዚህ ሰውን የሚወጡ ዘገባዎች መስክረዋል::በዚህ ከፍተኛ እፍረት እና ድንጋጤ የገባው የወያኔው አገዛዝ በሌሎች ክልሎች በሚኖሩ አማሮች ላይ በተለይ የወልቃይት ተወላጆች ላይ የበቀል ዱላውን ለማሳረፍ በአዲስ አበባና በሱዳን ወና ከተማ ካርቱም አፈሳውን ተያይዞታል::በተለይ የወልቃይት ተወላጆች ይበዙበታል በሚባለው ገዳሪፍ እና ካርቱም ውስጥ የፈሰሱት የወያነ የደህንነት አባላት አፈናው አጠናክረው በመቀጠል ላይ ሲሆን የተለያዩ መሳሪያዎች እና ጥይቶችን በመግዛት ወደ ጎንደር ያስገባሉ የተባሉ የወልቃይት ተወላጆች መያዛቸውን ምንጮች ጠቁመዋል::

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s