23 የእስራኤል ልዑካን ከጎንደር አዉሮፕላን ማረፊያ መዉጣት አለመቻላቸዉ ታወቀ። የእስራኤል ኤምባሲና ሌሎች አይሁዳዊ ወኪሎች ጎንደር ያሉትን ልዑካን ለማዉጣት እየጣሩ መሆኑን ጄሩሳሌም ፖስት ዘግቧል። የእስራኤል የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳሳወቀዉ ልዑካኑ ጥበቃዉ በተሟላ ህንጻ ዉስጥ መሆናቸዉን አሳዉቋል። ሌሎች ቁጥራቸዉ በዉል ያልታወቀ የእስራኤል ቱሪስቶች ጎንደር ዉስጥ ሊገኙ እንደሚችሉ የታወቀ ሲሆን በምን አይነት ሁናቴ እንዳሉ ይፋ የሆነ ነገር የለም።እስከ 6000 የሚደርሱ ኢትዮጵያዉያን አይሁዳዉያን ጎንደር ዉስጥ ይገኛሉ ተብሎ ይገመታል። ብዙዎቹ የተወለዱትን እገር ጥለዉ “አሊያ” በመባል የሚታወቀዉን ጉዞ በማድረግ እስራኤል መኖር አንደሚፈልጉ ይታወቃል። ባለፈዉ ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ሲሆን ሁለቱ አገራት ያላቸዉን ዲፕሎማሲያዊ ቁርኝት ታሪካዊ እድርገዉ ለመለጠጥ የሚኮሩበት ሁናቴ የሚዘነጋ አይደለም።
Advertisements