ከእልቂት እንዲድኑ ትግሬ ሁሉ ወያኔ አለመሆኑን ያሳዩን – አብርሃም ታዬ

 

የእናንተ ቤት እየተመረጠ ሲቃጠል፥ የእናንተ ድርጅት እየተነጠለ ጉዳት ሲደርስበት፥ የሰላም ባሳችሁ በየወቅቱ  ሲቃጠል ምንም አይሰማችሁም ትግሬ ወያኔዎች? ኢትዮጵያ ውስጥ ግርግር በተነሳ ቁጥር ለምን የሁሉም ጣት እኛ ላይ ያነጣጥራል ብላቹ ለምን አትገመግሙም። ምርጫ ዘጠና ስባትን ተከትሎ በተነሳው ነውጥ ሆነ የአሁኑ የጎንደር ህዝብ ጥያቄ ላይ የትግሬ  ሆቴል እና ንብረት ኢላማ መሆናቸው ሌላውም ሲነሳ ያንገበግባችኋል።መጽሃፍ እንደሚል በእርጥቡ እንዲህ ከሆነማ በደረቁ እንዴት እንደምትነዱ አስቡት። ዘላለም ስለማትነግሱ የለውጥ አብዮቱ አራት ኪሎ ቤተመንግስት ለመግባት ገና ግማሽ ሃገር ሲቀረው ሙሉ በሙሉ የዘረኝነት ጄኖሳይድ ሰለባ እንደምትሆኑ ግልጽ ነው። ከኢትዮጵያ ህዝብ  አምስት ከመቶ የማይሞላ የቁጥራችሁን ማነስን የባሰ የሚገዳደር ዕልቂት ተጋርጦባችኋል።በየጊዜው ቂም የያዘባቹ  ከዘጠና ፐርሰንት በላይ  የሚሆን ኢትዮጵያዊ ሁሉ የግፍ ጽዋው ሲሞላ ይበቀላችኋል። ከአብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በሰላም በፍቅር በመከባበር ለመኖር የሚያስችል የእርቅ ድልድይ  መፍጠር ካለባቹ ጊዜው አሁን ነው።debark car

የተገላቢጦሽ  እናንተ ግን  የአናሳ አምባገነን (minority dictatorship )ነታቹ ብሶባችኋል።ከናዚ ጀርመን  የበለጠ የሚዘገንን ሰይጣናዊ በሆነው ዘረኝነት ታውራቹ ዛሬም  አማራ እና ኦሮሞን በማናቆር  በዳኝነት  ስልጣን ለመክረም የማትፈነቅሉት ድንጋይ የለም። ይልቁንም ተጋሩ የተሰኘው ማህበራችሁ ሳይቀር ያባሳጨው የወደመው ንብረት እንጂ ከሁለቱም ወገን የተቀጠፈው የሰው ህይወት አይደለም በመግለጫቹ  እንዳሳሰባችሁት።

በአገዛዙ ተማረው ተሰደው  በግፈኛው  አይሲስ እና በሜዲትራንያን ባህር ያለቁት ኢትዮጵያውያን   መሆናቸውን የአለም ሚዲያዎች እየዘገቡት እየነገሯችሁ  ዜግነታቸውን ሳናጣራ እንደርስላቸውም በማለታችሁ ስንቶች መንግስት የሌላቸው አስከሬን ሆኑ? ለህወሃቱ ዘፋኝ ኢያሱ በርሄ ወይም ለመለስ ዜናዊ በድን ግን መንገድ ተዘግቶ ከሁለት ሳምንት በላይ ብሄራዊ የ ሃዘን ቀን ታውጆ ነበር። እነዚህ አብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ሊወክሉ የሚችሉ  ከመቶ በላይ የወገኖች  ደም ከዘረኛው መለስ ዜናዊ ወይ ካንዱ  ዘረኝነትን ሊተክል ከተሰዋ ትግራዋይ ደም በብዙ እጥፍ መከበር ነበረበት።  በጋምቤላ የአኙዋክና የኑዌርን ጎሳ በማጋጨት ለፈጸማችሁት የዘር ጅምላ ጭፍጨፋ የብዙ ሺ ሰዎች  ፍርድ ሳታገኙ የሩዋንዳን ሁቱ እና ቱት ሲን  ኢንተርሃሞይ ዕልቂት ትዘክራላቹ። የራሷ አሮባት የሰው ታማስላልች ማለት ህወሃት ናት። ጀኖሳይድ ዋች የተባለ ድርጅት እንደዘገበው ኢትዮጵያ ውስጥ በወያኔ ሁሉም አይነት  ድርጊት በዘር ከመከፋፈል classification እስከ ጅምላ ጭፍጨፋ ያሉት ሰባት እርከኖች ተፈጽሞብናል። “Genocide Watch considers Ethiopia to have already reached Stage 7 of the 8 stages of, genocidal massacres, against many of its peoples, including the Anuak, Ogadeni, Oromo, and Omo tribes.”

በደኖ በሃረር በቁማቸው ለተቀበሩት የአማራ ወገኖች እልቂት መንስኤ መፍትሄ ሳታበጁ ከሃያ አምስት  አመት በላይ ተጎልታቹ በፌደራሊዝም ስም ትነግዳላችሁ።

አማራ የትግራይ ህዝብ ጠላት ነው ብሎ ህወሃት እንደተነሳ ሁሉ አማራው እናንተ ላይ የአጸፋ እርምጃ ቢወስድ አይደንቅም። ሆን ተብሎ በሰሜን ጎንደር ያሉ ሴቶች እንዳይወልዱ የሚያመክን መርፌ ለምን ተወጉ? ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ እንዳረጋገጠው የአማራ ህዝብ ብዛት መሆን ካለበት በሶስት ሚሊዮን ያነሰው በዘመናዊ ጀኖሳይድ ሂሳብ ብትገድሉ ኣይደል እንዴ? በጀቱን ለመቀነስ?

በታሪክ ድንበሩ ከተከዜ ወንዝ  አልፎ ያማያውቀውን የትግራይ ክልል ከሱዳን ጋር ለማዋሰን ስትሉ ብሎም በአፋርም በወሎም በኩል ያልነበራችሁን ይዞታ የመውረር አባዜ ግጭት የፈጠራችሁት እናንተ አይደላችሁ እንዴ? በጎንደር ወልቃት ጠገዴ  አማራነት ላይ ያልነበረ ማንነት ባትፈጥሩ ኖሮ ይኼ ሁሉ  ቀውስ ባልመጣ ነበር።

ለመሆኑ የትኛው የኦሮሚያ ክልል ወይ የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ነው በህወሃት ከተሰጠው ሃላፊነት ውጭ ራስ ገዝ የሆነው?  ለጠቅላይ ሚንስትር አማካሪ በትግሬው  መለስ ጊዜ ሳይኖር ከደቡብ ለመጣው ሃይለማርያም ደሳለኝ ሲሆን ግን አራት አማካሪ በአናቱ ማስቀመጥ ስድብ አይሆንም? ተጠቅላይ ምኒስትርነቱን ለማጉላት ለዛውም አለቆቹ ሁሉ ትግሬ። እራሳቹ  እንደምትናገሩት ኦሮሞዎችን የምታስፈራሩበት የምትገለገሉበት ድርጅት  ኦህዴዶች ልባቸው ቢፋቅ ኦነግ ናቸው። በቅርቡ ግምገማቹ   ስጋታችሁን እንደገለጻችሁት  የአማራው ብአዴን ወይ የደቡቡ አሻንጉሊት ድርጅት  ደኢህዴን ውስጥ ግንቦት ሰባቶች  አሉ። እነዚህ ህወሃትን ያዘሉ አንቀልባ ድርጅቶች ማዘል ደክሞአቸው በቃ ሲሉ ማንም የሚያዝንላቹ የለም።  እስካሁንም ያላችሁት በነዚህ ተላላኪ ካድሬዎች ብቻ ነው። አንዳንድ የኦህዴድ፥ የብአዴን ወይም የደቡብ ህዝብ ደኢህዴን  አመራሮች ከአለቃቸው ህወሃት የበለጠ ዘረኝነቱንስ ሲያስፈጽሙ ወገናቸው ላይ የመጨከናቸውን ያህል ትግሬ ሆኖ ህወሃትን ጨክኖ አንቅሮ የሚተፋ አርአያ ሰብ ያስፈልጋል።

በየድርጅቱ ፥በየሰራዊቱ ፥በየህዋሱ ጠርናፊው ህወሃት ብቻ ሲሆን አንድ ቀን በቃኝ የማይሉ ይመስላችኋል? እስቲ አስቡት ከስልሳ የጦር ጄነራሎች 57 ትግሬ፥ ብሎም የቴሌ እና ሌሎች ሲቪክ መስሪያ ቤቶች ጠርናፊ አለቃ ትግሬ ሲሆን አይሰቀጥጣችሁም?  ንግዱንማ ሙሉ በሙሉ  በድፍረት ተቆጣጥራሁታል።

ኢፈርት በተባለ የህወሃት ክንዳቹ  የሃገሪቱ ሃብትን ስትቀራመቱ ያልመሰላችሁን ከገበያ ስታባርሩ ከርማችሁ  በቅርቡ የሆላንድ ካር(Holland car ) ድርጅትን  ከአዲስ አበባ በቀይ ካርድ አባራችሁ  የፈረንሳዩ ፔጆ መኪና በመስፍን ኢንደስትሪያል ስር እንዲመረት ፋብሪካውን መቀሌ ላይ ገነባችሁ። ትግራይ ልትለማ ሌላው የሚደማ ለምንድነው? ኢትዮጵያ ውስጥ ቲቪ  ከፍተን ስናይ ማስታወቂያው ሁሉ ሲሚንቶ፣ መድሃኒት ፋብሪካ፥ ምግብ እና የተለያዩ ሸቀጦች ወዘተ የተገነቡት ወይ አድራሻቸው ትግራይ ላይ ነው። ብቻውን የበላ ብቻውን እንደሚሞት ማን በነገራችሁ? የሃገሪቱ ሃብት ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ለሁሉም ተደራሽ ይሁን የሚል እንዴት አንድ ቅን አሳቢ ከመሃላችሁ ይጥፋ?

ለኮሎኔል አታክልቲ ገብረሚካኤል  ልጅ ህክምና ከኢፌዲሪ የብረታብረት ኮርፖሬሽን ኤጀንሲ 14 ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶች  ሶስት ሚሊዮን ብር አዋጥተው ባንኮክ ታይላንድ አሳከሙት። ብቸኛው የህዝብ ልጅ ሃብታሙ አያሌው ግን በከፍተኛ ኪንታሮት ታሞም ከሃገር ወጥቶ እንዳይታከም ተከልክሏል። ኢፍትሃዊነት በየፈርጁ ማለት ይኸ ነው። ህወሃት ማለት ኢፍት ሃዊነት ነው።

በእርግጥ ትግሬ ሁሉ አልፎለታል ወይም ትግሬ ሁሉ ወያኔ ነው ባይባልም ትግሬ ሆኖ ተቃዋሚ የሆነ አስር አይሞሉም። እንዘርዝር ሲባል ወያኔ አስሮ ከሚፈታቸው አብርሃ ደስታ ፤ አሰግድ ገብረስላሴ ወይም በስደት ካሉት ገብረመድህን እና አረጋሽ ይጠቀሳሉ።በቃ። ከነዚህ  ውጭ ሰው የለም እንዴ? ህወሃት እየገነባ ካለው ራሱን አጥፊ ዘረኝነት አንጻር ቅን ትግሬዎች ተሰባስባቹ ትግራይን እናድን የሚል ማህበር ወይ ፓርቲ ብትመሰርቱ ጥቅሙ ለራሳችሁ ነው። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በጉልህ ከሚጠቀስላችሁ የጣልያን ጊዜ ባንዳነታቹ (የመለስ ዜናዊ አባትንም የጣልያን ተላላኪ እንደነበሩ በመጥቀስም) ወይም ወይም ሞላ አስገዶም ትህዴንን  ስለካደ    አይደለም ካሳ የምትከፍሉት። ይልቅ ከትግራይ ማሕጸን ተወልደው መሰዋዕት የሆኑት የራስ አሉላ አጽም ብሎም ለጣልያን ያደሩ መስለው ለአጼ ምኒልክ መረጃ በማቀበል ለአደዋው ድል  አስተዋጾ ያበረከቱት የባሻ አውአሎም አጽም እንዳይወቅሳችሁ  ነው።ለወያኔ ተብሎ  የተተኮሰ ጥይት ወይ ፍንጣሪ  እናንተንም በማወቅም ይሁን ባለማውቅ   ስለሚመታችሁ አስቡበት።ነግ በኔ በሉ። ለወያኔ የተወረወረ እሳት ትግሬዎችን በሙሉ እንዳያቃጥል መፍትሄውን ራሳቸው አሁኑኑ ይጠቁሙን ትግሬ ሁሉ ወያኔ ላለመሆኑ በተናጥል ወይ በማህበር  አሳዩን።  ጀግኖች በአንድነት የተዋደቁላትን ሃገር እንዳትፈራርስ ማደረግ  የሁሉም ሃላፊነት ነው።

አብርሃም ታዬ  zeabraham@gmail.com

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/63042

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s