በጎንደር ለእሁድ የተጠራው የተቃውሞ ሰልፍ እንደማይታጠፍ ነዋሪዎች አስታወቁ

በጎንደር ለእሁድ የተጠራው የተቃውሞ ሰልፍ እንደማይታጠፍ ነዋሪዎች አስታወቁ

ሐምሌ ፳፩ ( ሀያ አንድ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጋር በተያያዘ በሰሜን ጎንደር የተነሳውን ህዝባዊ አመጽ ለማብረድ ገዢው ፓርቲ የተለያዩ የማዘናጊያ ስልቶችን ቢጠቀምም፣ በህዝቡ ውስጥ ያለው ስሜት ግን ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍ ማለቱን ዛሬ በጎንደር መድሃኒያለም ቤተክርስቲያን የተሰበሰቡት የኮሚቴ አባላትና በስብሰባው ላይ የተሳተፉ ነዋሪዎች ተናግረዋል። በመጪው እሁድ ሃምሌ 24፣ 2016 ከጠዋቱ 2 ሰአት ጀምሮ የሚካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ተፈቀደ አልተፈቀደ ሰልፉን ከማድረግ ወደ ሁዋላ የሚያግዳቸው ነገር እንደሌለ ወጣቶች ተናግረዋል።

በስብሰባው ላይ ከ300 በላይ ሰዎች ተሳትፈዋል። የጎንደር ዩኒቨርስቲ አመራር የመኪና አገልግሎት በመስጠት ችግር እየፈጠረ መሆኑን ተሰብሳቢዎች ገልጸዋል። ደህንነቶች ሆን ብለው ሽፋን ለማግኘት የዩኒቨርስቲውን መኪኖችና አምቡላንሶች ሳይቀር እየተጠቀሙ ነዋሪዎችን እየሰለሉ በመሆኑ፣ የዩኒቨርስቲው አመራሮች ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስጠንቅቀዋል።

ትናንት በከንቲባው ጽ/ቤት አቶ በረከት ነዋሪዎችን ሰብስበው በነበሩበት ወቅት “ ሰላማዊ ሰልፉን ሰላማዊ በሆነ መልኩ እስካካሄዳችሁ ድረስ ችግር የለም” ብለው ቢናገሩም፣ ዛሬ ግን ስብሰባውን ማካሄድ አይቻልም የሚል ትእዛዝ ለኮሚቴው አባላት መተላለፉ ታውቋል። አቶ በረከት “ የድንበሩን ጉዳይ ለመፍታት 3 ወር ይወስዳል፣ የማንነትን ጥያቄ በተመለከተ ግን ስብሰባውን በሰላም ማካሄድ ትችላለችሁ” ብለው ማናገራቸውን ተሰብሳቢዎች ተናግረዋል።

የኢህአዴግ አመራሮች የተለያዩ አወዛጋቢ መልሶችን መስጠታቸው ወጣቶችን ያስቆጣ ሲሆን፣ አመራሮቹ ምንም ይበሉ የእሁዱ የተቃውሞ ሰልፍ የሞት ቀጠሮ ነው ብለዋል።

“ከእንግዲህ የደህንነት ሃይሉና ወታደሩ እጃችንን ሊይዝ ቢሞክር ሁላችንም የኮሎኔል ደመቀን መንገድ እንደምንከተል እናሳያቸዋለን ሲሉ ወጣቶች ተናግረዋል።

በሰልፉ ላይ ለመሳተፍ ከተለያዩ የሰሜን እና የደቡብ ጎንደር ከተሞች ነዋሪዎች ወደ ጎንደር ከተማ እየተጓዙ ነው። ይህን እንቅስቃሴ ለመግታት በባህርዳር፣ ደሴና በሌሎችም የክልሉ ከተሞች ጥብቅ ፍተሻ በመደረግ ላይ ነው።

በነገው እለት ኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ ጎንደር ከፍተኛው ፍርድ ቤት ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል። ህዝቡ ወደ ፍርድ ቤት በማምራት ለኮሎኔሉ ያለውን ድጋፍ ይገልጻል ተብሎ የጠበቃል።

በክልሉ የሚገኙ አሽከርካሪዎች ወደ ጎንደር ጉዞ ለሚያደርጉ የተለያዩ አካባቢ ነዋሪዎች ተቢውን የተሽከርካሪ አገልግሎት እንዲሰጡም ጥሪ ቀርቦላቸዋል።

ህዝቡ በሰልፉ ላይ የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ እንዲመለስ፣ የታሰሩት በሙሉ እንዲለቀቁ፣ ኮ/ል ደመቀ ዘውዴ ከእገታ እንዲወጣ እንዲሁም በዘር ላይ የተመሰረተው የህወሃት አገዛዝ እንዲያበቃ ይጠይቃል ተብሎ ይጠበቃል። ጋጠወጥ በሆነ መልኩ የህዝቡን የነጻነት ትግል ያራከሱት የኮሚኬሽን ሚኒስቴር ጌታቸው ረዳ፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኤጀንሲ እንዲሁም ሬዲዮ ፋና የጎንደርን ህዝብ በይፋ በመገናኛ ብዙሃናቸው ይቅርታ መጠየቅ እንዳለባቸው የጎንደር ህዝብ እያሳሰበ ነው።

ሀምሌ ወር የመጀመሪያ ሳምንት ላይ በነበረው አመጽ፣ 18 ወታደሮች መገደላቸውን ባህርዳር በነበረው የሰሜን እዝ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ስብሰባ ላይ ተነስቶ ነበር። እነዚህ የሰራዊት አባላት በህዝባቸው ላይ ለመተኮስ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ተከትሎ ገዢው ፓርቲ የአጋዚ ሰራዊት አባላትን በማሰማራት ጥበቃ በማድረግ ላይ ነው።

Netsanet Beqalu Mannet's photo.
Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s