በጎንደር ሐምሌ 24 ቀን 2008 ዓ.ም የተቃውሞ ሰልፍ የተያዘዉ መፈክሮች

ማሳሰቢያ ******** የተቃዉሞ ሰልፍ መነሻ ቦታ – መስቀል አደባባይ! *************** *********************** መነሻ – 3፡00 ሠዓት ላይ! ********************* ‪#‎AmharaResistance‬ – ሸር በማድረግ መረጃውን ለሌሎች ያካፍሉ! ከመስቀል አደባባይ ተነስቶ በከንቲባ ጽ.ቤት፣ዞን አሰተዳደር አድረጎ በፋሲል በኩል ወደ ዞን ፖሊስ መምሪያ በመታጠፍ በአርበኞች አደባባይ በኩል ወደ አስመራ መንገድ በማቀናት የሰልፉ ጉዞ ወደ አብዮት አደባባይ በማቅናት ኮለጅ 18 ማዞሪያ ደርሶ ይመለሳል፤የመልስ ጉዞዉን የሚያደርገዉ በሰርድ በኩል ሲሆን በፋሲለደስ ት.ቤት በኩል በአድረጎ በአዉቶ ፓርኮ በኩል ወደ ፒያሳ በማቅናት ማሰረጊያዉን መስቀል አደባባይ ላይ ያደርጋል፡፡ በመዝጊያ ሥነ ስርዓቱ ላይ ተተኪ የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አስተባበሪ ኮሚቴ አባላትና የተመረጡ የአገር ሽማግሌዎች ንግግር ያደርጋሉ፤የተቃዉሞ ሰልፉ የአቋም መግለጫዎች ይቀርባሉ፤ለክልሉና ለፌደራሉ “መንግስት” በጉዳዮ ላይ የጽሞና ግዜ ገደብ ይሰጣል፡፡

ለዕሁድ ሐምሌ 24 ቀን 2008 ዓ.ም የተያዘዉ የተቃውሞ ሰልፍ ሐገርኛ በሆኑ ሙዚቃዎች፣አዝማሪዋች፣ቀረ ርቶና ፉከራ በሚያሰሙ ሰዎች እንደሚታጀብ የተቃዉሞ ሰልፉ አስተባባሪዋች መረጃ ያመለክታል፡፡በዕለቱ የሚስተጋቡ መፈክሮች አገር አቀፍ ይዘት ያላቸዉ እንዲሆኑ ታስቧል፡፡ በዕለቱ ከሚስተጋቡ መፈክሮች ዉስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል፡-

1. ታሪክ ምስክር ነው ወልቃይት አማራ ነው!
2. የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ ሕገ- መንግስታዊ መብት ነው!
3. የሻዕብያ ተላላኪ ህወሓት እንጅ የወልቃይት ህዝብ አይደለም!
4. በግፍ የታሰሩ የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት በአስቸኳይ ይፈቱ! 5. አማራ ለኢትዮጵያ የግዛት አንድነትና ሉአላዊነት የተዋደቀ ታላቅ አርበኛ ሕዝብ ነው!
6. ዘረኝነትን አጥብቀን እናወግዛለን!
7. የትግራይን ሕዝብ እናከብራለን፤የህወሓትን አፋኝ የአገዛዝ ፖሊሲ አጥብቀን እናወግዛለን!
8. በኦሮሞ እህት ወንድሞቻችን ላይ የሚደርሰውን ግፍና በደል አጥብቀን እንቃወማለን!
9. የኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃነት ይፈልጋል!
10. ኢቢሲና ሌሎች መንግስታዊ ሚዲያዎች የጎንደርንና አካባቢውን ህዝብ ይቅርታ ይጠይቁ! 11. የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ እስኪመለስ ድረስ ትግሉ ይቀጥላል!
12. አማራነት ወንጀል አይደለም!
13.የትግራይ ወሰን ተከዜ ነው።ወልቃይት የአማራ ነው!!
14. የሐብታሙ አያሌዉ ከአገር የመዉጣት እግድ በአስቸኳይ ይነሳለት!
15. ዜጎችን በፖለቲካ አመለካከታቸዉ ማሰርና ስቅየት ማድረስ ይቁም!
16. በፖለቲካ አመለካከታቸዉ የታሰሩ የፖለቲካና የህሊና እስረኞች በአስቸኳይ ይፈቱ!
17. የህወሓት የበላይነት ይቁም! የሚሉ መፈክሮች በዕሁዱ የተቃዉሞ ሰልፍ ይስተጋባሉ፡፡

የኮረኔል ደመቀና የሌሎች የኮሚቴዉ አባላት ፍቶግራፍ በባነር ተዘጋጅቷል፡፡ ለተቃዉሞ ሰልፉ ሚያስፈልጉ ሌሎች ግበአቶች በጎንደር ከተማና አካባቢዉ ሀገር ወዳድ ባለሀብቶች ድጋፍ ተደርጓል፡፡በተጨማሪም የከተማዉ ወጣቶች በቡድን በቡድን በመደራጀት የተቃዉሞ ሰልፎን ለመድመቅ በዝግጅት ላይ ይገኛሉ፡፡ “በዕለቱ የተቃዉሞ ሰልፍ የጸጥታ ችግር በህዝቡ በኩል እንደማይፈጠር እርግጠኞች ነን!” የሚሉት የሰልፉ አስተባባሪዎች በ “መንግስት” የጸጥታ ኃይሎች በኩል ችግር እንፈጥራለን ቢሉ ምላሹን እንደማይችሉን በአጽኖት ገልጸዋል፡፡ በተያያዘ መረጃ ተተኪ የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አስተባባሪ የኮሚቴ አባላት የሰልፉ ዋና አላማ ኮሚቴዎቹ ይፈቱ የሚል ብቻ ሳይሆን ኮሚቴዎቹን በማሰር የማንነት ጥያቄዉን ማፈን እንደማይቻል ለመግለጽ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከዚህ ጉን ለጉን ተጨማሪ አገራዊ አጀንዳዎች እንደሚንጸባረቁ የኮሚቴዉ አባላትና የተቃዉሞ ሰልፉ አስተባባሪዋች ገልጸዋል፡፡ ድል የህዝብ ነዉ!!! ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Gonder‬ ‪#‎Amhara‬
Finote Abewye

Tilaye Tarekegn ZE Ethiopia's photo.
Tilaye Tarekegn ZE Ethiopia's photo.
Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s