ይድረስ ለአማራ ክልል ልዩ ኃይል፣ ፖሊስና ሚሊሺያ ሰራዊት በሙሉ፥

ይድረስ ለአማራ ክልል ልዩ ኃይል፣ ፖሊስና ሚሊሺያ ሰራዊት በሙሉ፥ ታሪክ ሰሪ እንጂ ታሪክ እንዳይሰራብህ፥
በጎንደር የአማራ ተጋድሎ፥ የጎንደር ልጅ እየተሰዋ ነው። እስከ መቼ ቆመህ ታያለህ?
==========================================================
በወልቃይት ጠገዴ አማራዎች በተጀመረው የማንነት ጥያቄ ምክንያት፤ የትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር ወያኔ በጎንደር ህዝብ ላይ ጦርነት አውጇል።

የአማራው ክልል ፖሊስ ሰራዊት ሆይ፥ የወያኔ የጭቆና አገዛዝ ያንገፈገፈው አማራ ወገንህ አፋኝ ስርአቱን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አሽቀንጥሮ ለመጣል ብሶት በወለደው እልህና ቁጣ ጎንደር ላይ ገጥሞታል፥ ጎንደር የነደደው ሕዝባዊ እምቢተኝነት በኢትዮጵያ ግዛቶች ሁሉ እንደ እሳተ ገሞራ እየገነፈለ ወያኔን መለብለቡን ተያይዞታል፥ የትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር የዘረጋው ፋሺስታዊ ስርዓት በስብሷል፥ ገዥዎች ያልፋሉ፣ ሕዝብና አገር ግን ዘላለም ይኖራሉ።

ሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ. ዓ ጀግናው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ የወሰደውን ራስ የመከላከል እርምጃ ተከትሎ ፤ የጎንደር አማራ ህዝብ ባደረገው የመስዋዕትነት ተጋድሎ ቅስሙ የተሰበረው ወያኔ፤ ህጋዊ የሕዝብ ወኪሎቹን አስሮ፥ መላው ጎንደርን በአሸባሪነት ፈርጆ በአማራ ሕዝብ ላይ ከባድ ጥቃት ለመፈፀም በመፈራገጥ ላይ ነው።

በትግራይ መሳፍንቶች የሚመራው የወያኔ አጋዚ ጦርና ፌደራል የሚባለው የስብሐትና የአባይ ፀሐዬ ታጣቂ፥ የኃይል እርምጃ ለመውሰድ ከዶክተር ደብረፅዮን እና ከአቶ አባይ ወልዱ ትዕዛዝ በመጠባበቅ በጎንደር ዙሪያ እያደቡ ይገኛሉ።

የወያኔ መንግስት በአማራ ሕዝብና በቀረው የኢትዮጵያ ዜጋ ላይ የሚፈፀመው በደልና ግፍ ለሠራዊቱ አዲስ ባለመሆኑ እዚህ መዘርዘሩ አስፈላጊ መስሎ ባይታየንም።
ወያኔ ቢሳካለትና ዛሬ እናንተን አልፎ የአማራን ተጋድሎ በሃይል ቢጨፈልቅ ነገ የእናንተ ተራ እንደሚሆን ስናስጠነቅቅ፤ ሰሞኑን አንድ ፌደራል ፖሊስ፥ የአዲስ አበባን ፖሊስ አናቱን ተረግጦት እያፌዘ ሲቀጠቅጠው በፎቶ ያየነውን የወያኔች እብሪትና ግልጽ ማናለብኝነት እንድታስተውሉ ሳንመክር ግን ዓናልፈውም።

ስለሆነም ማንኛውም የአማራ ተወላጅና ለሰው ልጆች መብት የሚቆረቆር ሁሉ የሚሰዋለት የአማራ ተጋድሎ የሁሉም ኢትዮጵያዊ የነጻነት ትግል በመሁኑ፥ አማራው መለዮ ለባሽ ሁሉ፥ የአገር አደራ የሕዝብ አለኝታ የመሆን ግዴታው የሚፈተንበት ሰዓት ላይ ትገኛላችሁና የተጀመረው የአማራ ተጋድሎ በድል እንዲከናወን የሞት ሽረት ትግሉን የመቀላቀል ወገናዊ አደራ እንዳለባችሁ በጥብቅ አስቡበት ለማለት እንወዳለን።
በመሆኑም፥
የአማራው ክልል ልዩ ኃይል፣ ፖሊስና ሚሊሻ ሰራዊት ከሕዝብ ጋር ጸንቶ እንዲቆም ወገናዊ ጥሪያችን እናቀርባለን።

ጎንደር ላይ የተጀመረው የአማራ ተጋድሎ ለኢትዮጵያዊነት ነው፥ የጎንደሮች ትግል ለኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነት ነው።

Gondar Ethiopia's photo.

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s