ጎንደር ላይ ተጋድሎው ቀጥሏል፥ 58 አጋዚ ጦር ሲሞቱ 2ቱ ተማርከዋል፥ ከሳንጃ ሰራዊቱ ለቆ ሄዷል

ዛሬ ነሐሴ 1 ቀን 2008 ዓ ም ከጎንደር ሰቲት ሁመራ መንገድ ደበዝ ላይ በኦራል ሙሉ የወኔ አጋዚ ጦር ሰራዊት ተደመሰሰ፥ 58 አጋዚ ጦር ሲሞቱ 2ቱ ተማርከዋል፥
ጎንደር ከተማ የሰነበተው የአጋዚ ጦር በአርማጭሆ አቋርጦ ወደ ሁመራ ለመሄድ ፈረስ መግሪያ ሙሴባብ ከተማ ሲደርስ ጥቆማ የደረሰው አርሶ አደር ሕዝባዊ ሰራዊት ደበዝ ወንዝ ላይ ጠብቆ ተኩስ በመክፈት ሙሉ በሙሉ ደምስሶታል።
 በሁመራ በኩል ተጭነው ወደ ጎንደር ለመግባት የሞከሩ የአጋዚ ወታደሮችን የሳንጃ ገበሬዎች አናሳልፍም ብለው ለ2 ቀናት አግተው ይዘው ከቆዩ በሁዋላ ዛሬ ጦርነት ከፍተዋል። በአሁኑ ሰአት በታንክ የታገዘ ሃይል ከጎንደርና ከትግራይ ተነቃንቆ በሶረቃና አካባቢዋ ውጊያ እየተካሄደ ነው።
በሶረቃና ዳንሻ የገበሬ ጦርና ወታደሮች ተፋጠዋል። ብዛት ያለው የገበሬ ጦር ከእያካባቢው እየተሰባሰበ ነው።መተማ ሽንፋ ሸዲ እና ቋራ ተቃውሞ ተጀምሯል። ከፍተኛ ውጥረት አለ።
ሰሜን ጎንደር በተለያዩ አከባቢዎች በህዝቡና በመከላከያ ሰራዊት መሀል ውጊያ እየተካሄደ ነው ከሙሴ ባምብና ከሳንጃ ሰራዊቱ ለቆ ሄዷል
ደበዝ በአርጭሆ ወረዳ ከጎንደር ከተማ ወደ 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሙሴባምብ እና ኩርቢ ከተማ መካከል የሚገኝ ወንዝ ነው።
በዚህ ሰዓት ከኋላ የመጣ ሌላ ረዳት ጦር ጋር ፈረስ መግሪያና ሙሴባምብ ዙሪያ ከቦ እያሸው ይገኛል፥ ከፍተኛ ሕዝባዊ ጦር ወደ ጎንደር ከተማ እየተጠጋ ነው።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!
Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s