የአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊዎችን ጨምሮ ከ200 በላይ ሰራተኞችን አሰናበተ

የአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊዎችን ጨምሮ ከ200 በላይ ሰራተኞችን አሰናበተ
ኢሳት (ነሃሴ 9 ፥ 2008)

arrests
ከወራት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ የተካሄደውን የትራንስፖርት የስራ ማቆም አድማ ተከትሎ በሰራተኞቹ ላይ ግምገማን ሲያካሄድ የቆየው የከተማዋ የትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊዎችን ጨምሮ ከ200 በላይ ሰራተኞችን አሰናበተ።
የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ፈጽመዋል የተባሉ እነዚሁ ሰራተኞች በቅርቡ ክስ እንደሚመሰርትባቸው የከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ ሰኞ መግለጹን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል።
በከተማዋ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ታክሲዎችና የትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ ተቋማት አስተዳደሩ ፍትሃዊ ያልሆነ መመሪያን ተግባራዊ አድርጎብናል ሲሉ ከጥቂት ወራት በፊት የስራ ማቆም አድማ መምታታቸው ይታወሳል።
ይሁንና የከተማዋ የትራንስፖርት ቢሮ አዲሱ የቁጥጥር መመሪያ ተግባራዊ እንዳይደረግ የተለያዩ አካላቱ ሚናን ተጫውተዋል ሲል ቅሬታን ማቅረቡ የሚታወስ ነው።
ይሁንና የትራንስፖርት ማቆም አድማ ተከትሎ ለወራት ያህል በሁሉም ሰራተኞች ላይ ግምገማን ሲያካሄድ የቆየው ቢሮው ሃላፊዎችን ጨምሮ ከ200 በላይ ሰራተኞችን ከስራ እንዳሰናበተ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
እነዚሁ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን በየክፍለከተሞቹ የሚገኙ የቢሮው ቅርንጫፎች በህገወጥ ደላሎች የሚሽከረከሩ ነበሩ ሲሉ በጉዳዩ ዙሪያ ባቀረቡት ሪፖርት አመልክተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ የሆኑት አቶ ያብባል አዲስ በሁሉም የቢሮው ቅርንጫፎች ግምገማ ሲካሄድ ቆይቶ ጽ/ቤቶቹ በሙስናና በደላላ የተወረሩ መሆናቸው ተረጋግጧል ሲሉ ገልጸዋል።
ከሃላፊነታቸው ከተነሱት ከ200 በላይ ሰራተኞች በተጨማሪ ከ120 በላይ ሰራተኞች የመጀመሪያ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጣቸው ተወስኗል ያሉት ሃላፊው ከ2009 ዓም ጀምሮ በክፍለ ከተማ ደረጃ ይሰሩ የነበሩ ጽ/ቤቶች እንዲፈርሱ ውሳኔ መተላለፉን ይፋ አድርገዋል።
የከተማዋ የትራንስፖርት ቢሮ የባንኮች አሰራር ተግባራዊ በማድረግ የትራንስፖርት የተራ መጠበቂያ ስርዓትን ለመዘርጋት እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን አክሎ አስታውቋል።
የትራንስፖርት ሚኒስቴር ባለፈው ሳምንት ወደ 1ሺህ የሚጠጉ አዳዲስ ታክሲዎችን በከተማዋ ለማሰማራት ዝግጅት ማጠናቀቁን እንደገለጸ ይታወሳል።

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s