25 አመታት በአማራው ህዝብ ላይ ከተፈጸመው ዝግናኝ ግድያ፥ ጀርባ እጁ ያለበት አቶ ንጉሱ ጥላሁን *የክልሉ የኮሙኒኬሽን ሀላፊ*

ላለፉት 25 አመታት በአማራው ህዝብ ላይ ከተፈጸመው ዝግናኝ ግድያ፥እስራት፥ስደት እና ወከባ ዋናዎች የህወአት ሰዎች ቢገኙም በተላላኪዎች እና በጉዳይ አስፈጻሚነት የሚንቀሳቀሱት ግን በክልሉ ያሉ በብአዴን ስም የተሰገሰጉ የጥፋት ሀይሎች ናቸው።
ሰሞኑን በአማራ ክልል የሚካሄደውን ህዝባዊ ትግል ጥላሸት በመቀባት ሰላማዊ ሰልፉ ህጋዊ አደለም ከማለት ጀምሮ በዜጎች ላይ የሚወሰደውን ዘግናኝ እርምጃ ሳያወግዝ አለቆቹ ጽፈው የሰጡትን እንደበቀቀን የሚያስተጋባው የክልሉ የኮሙኒኬሽን ሀላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በ14/08/2016 የተገደለውን ወጣት አስመልክቶ ከአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው ዝግጅት ክፍል ለቀረበለት ጥያቄ ሰዎች የፈለጉትን መልበስ እንደሌለባቸው እና የተገደለው ወጣትም በአመጽ እና በቅስቀሳ ተግባር ስለተሰማራ ነው እንጂ ነጭ ስለለበሰ አደለም ሲል ግድያው ተገቢ መሆኑን አረጋግጧል።ወደ ፊትም እርምጃ እንደሚወሰድ አሳውቋል።
ታዲያ እንዲህ አይነቱ ሰው ማን ነው?የኋላ ታሪኩስ ምን ይመስላል?እንዴት ወደዚህ ስልጣን መጣ ብሎ መጠየቅ ስለ ግለሰቡ የተሟላ መረጃ እንዲኖረን ፥መወሰድ ያለበት ቀጣይ ተግባርም ለመወሰን ስለሚረዳ እነሆ ተከታታሉኝ።
ንጉሱ ጥላሁን በ1998 አ.ም ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ፔዳ ካምፓስ በፔዳጎጅካል ሳይንስ የተመረቀ ሲሆን በዩኒቨርሲቲ ቆይታው የተማሪዎች መማክርት ውስጥ ይሰራ ነበር።በዚህም ወቅት ከግቢው የተማሪዎች የምግብ አቅራቢ ድርጅት ጋር በመመሳጠር ጥራቱ ያልጠበቀ ምግብ እንዲቀርብ፥ነጭ ጤፍ መቅርረብ ሲገባው ቀይ ጤፍ እና በቆሎ የተቀላቀለ፥ትክልት መቅረብ ሲገባው አተር ከክ ፥ወዘተ እያደረገ በተማሪው በጀት የግል ኪሱን ሲሞላ የነበረ ሰው ነው።የ97 ምርጫ ብጥብጥ ተከትሎ በዮኒቨርሲቲው ውስትጥ የነበሩ ተማሪዎችን እየጠቆመ ያሳስር የነበረ ሰላይ ነበር።
ንጉሱ ትምህርቱን ሲይጠናቅቅ ገና በይፋ የምስክር ወረቀት ዲፕሎማው በሬጅስትራር ተሰርቶ ብይፋ ለሁሉም ከመታደሉ በፊት በነበረው የባንዳነት ተግባሩ ዲፕሎማው ተሰርቶ ተሰጦት በዳሸን ቢራ ፋብሪካ ያለ ምንም ውድድር የተቀጠረ ሰው ነው።ከዚያም በቀጥታ ለአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሀላፊነት ተመደበ።
ለዚህ ሁሉ ተግባር ከንጉሱ ጀርባ ማን አለ?ንጉሱን ማን ወደ ዳሸን ቢራ አስገባው?
ቁልፍ ካድሬዎች ተመርጠው በሚቀመጡበት የኮሙኒኬሽን ቦታ ማን ንጉሱን አስቀመጠው ብለን ስንጠይቅ መልሱ ህወአት ሁኖ እናገኘዋለን።እንግዲህ ይህ ሰው ነው የአማራውን ትግል በሌሎች ብሂሮች ላይ ያነጻጸረ እያለ የህወአትን አጀንዳ በህዝባችን ላይ የሚያስፈጽመው።
ወገኔ ትግል ሩቅ አያስሄድም።ከጎናችን ብዙ ጠላቶች አሉ ትልልቁን ዛፍ መቁረጥ ከመጀመራችን በፊት ቅርንጫፉን መመልመል ተገቢ ነው።

ንጉሱ ጥላሁን የአማራው ጠላት

 Aseged Tamene photo
Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s