ሕዝባዊ እንቅስቃሴው በህወሓት የንግድ ተቋማት ላይ ያነጣጠረ የኢኮኖሚ ጦርነት ሊጀምር ነው

gonder-before-and-after-1991

በሰሜን ኢትዮጵያ ጎንደር እና ጎጃም በደቡብ ኢትዮጵያ ከኦሮሚኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን አመጽ ጋር በተያያዘ በስልጣን ላይ ያለው የህወሓት የፖለቲካ መናጋት እንደደረሰበት የሚወስዳቸው ግብታዊ ርምጃዎች ያመላክታሉ።

ምንም እንኳን በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በአማራም በኦሮሚያም የኢትዮጵያ ክፍሎች ቢገደሉም ሕዝባዊ ተቃውሞው በተቃራኒ ጉልበቱን እያደሰ ስርዓቱን ግራ አጋብቶታል።

የህወሓትን ኢኮኖሚ አቋም ለማዳከም በሚመስል ሁኔታ በጎጃም ባህር ዳር ከስርዓቱ ጋር ንክኪ ያላቸውን የንግድ ተቋማት ዝርዝር የያዘ እና የኢኮኖሚ እቀባ የሚጠይቅ ጽሁፍ ተበትኗል። በጎንደር እና ሌሎች የጎጃም አካባቢዎች ተመሳሳይ እርምጃ እንደሚወሰድም ታውቋል። የኦሮሚኛ ተናጋሪ የፖለቲካ መሪዎች ተመሳሳይ የኢኮኖሚ ጦርነት በህወሓት ተቋማት ላይ ለማድረግ እቅድ ነድፈው ወደ ስራ ለመግባት እንደተዘጋጁም ተሰምቷል።

ከህወሓት ጋር የፖለቲካ እና ጎሳን መሰረት ያደረገ ግንኙነት ያላቸው ወገኖች ያላአግባብ በመበልጸግ ሃገሪቷን ዘርፈዋል የሚል ተደጋጋሚ ክስ ከኢትዮጵያውያን ይሰነዘራል። ከጥቂት አመታት በፊት ኤፈርትን ጨምሮ ህወሓት እንደፓርቲ የሚያንቀሳቅሳቸው የንግድ ተቋማት ብቻ ከአምስት ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ እንደሚገመቱ ባለስልጣናቱን በመጥቀስ የወጡ ዘገባዎች ያመለክታሉ። የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ከዚህ በፊት የህወሓት ቁልፍ ሰው ናቸው ከሚባሉት ከስብሃት ነጋ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ስብሃት ህወሓት ግዙፍ ሃብት እንዳካበት ሳይደብቁ ተናግረዋል።

በተያያዘ ዜና ትላንት ቅሊንጦ እየተባለ ከሚጠራው እስር ቤት በቀለ ገርባን ጨምሮ የፖለቲካ እስረኞች ባለፉት ጥቂት ወራት ለተገደሉ ኢትዮጵያውያን ሶስት ቀን የሃዘን ቀን እንዲታወጅ እና ኢትዮጵያውያን ጽጉራቸውን በመላጨት የተገደሉትን ንጹሃን ኢትዮጵያውያን እንዲያስቡ ባቀረቡት ጥሪ መሰረት ፤ ብዙ ኢትዮጵያውያን ጥሪውን በመቀበል ጽጉራቸውን በመላጨት እና የኦሮሚኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውን የተቃውሞ ምልክት የሆነውን የተሳሰረ እጂ በፎቶግራፍ በማሳየት ለጥሪው ምላሽ ሰጥተዋል።

ቦርከና14012564_10205198112430990_355381106_o

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s