በአማራ ክልል አንድ ክፍለ ጦር ሰፍሯል ጎንደር እና ጎጃም በ2 ሂሊኮፍተር እና በ8 ኦራል ወታደር ገብቷል::

የአማራ ክልል እምቢተኝነት እየተቀጣጠለ መሔዱ ያሳሰበው ፌደራል መንግስት በርካታ ወታደሮችን ወደ ክልሉ ላከ፡፡ ሁኔታው ያሰጋው ህወሓት አልሞ ተኳሽ ገዳዮቹን እና የጸጥታ ኃይል ወታደሮቹን ወደ ስፍራው ማጓጓዝ የጀመረ ሲሆን፣ ቁጥራቸው በርከት ያሉት ወታደሮችም በሂሊኮፍተር እና በኦራል መኪኖች ወደ ክልሉ ገብተው በተጠንቀቅ መቆማቸው ታውቋል፡፡ ስምንት አራል ሙሉ ወታደር ወደ ጎንደር እና ጎጃም መግባቱን የገለጹት የየአካባቢው ነዋሪዎች፣ 5ቱ ኦራል ወደ ጎንደር 3ቱ ደግሞ ወደ ጎጃም መግባታቸውን ነዋሪዎቹ ጨምረው ገልጸዋል፡፡ ከተማዎቹም በከፍተኛ ውጥረት ላይ እንደሚገኙ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡
“መከላከያ ወደ ጎጃም እና ጎንደር መጓዝ የጀመረው ከጠዋት ጀምሮ ነው፡፡ አንድ ክፍለ ጦር እና እልፍ የተለያዩ ከባድ መሳርያዎችን ወደ ክልሉ በገፍ ሲያጓጉዝ እንደነበር ታይቷል፡፡ መከላከያ ኃይሉ ከመንገድ ጉዞ በተጨማሪ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ 1000 በላይ ወታደር ወደ ቦታው ተልኳል፡፡›› ሲሉ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ትላንት አመሻሹን ከትግራይ የተነሱ ወታደሮች በውጫሌ ዞረው ወደ ሰሜን ጎንደር ማምራታቸውን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ይህም በህዝብ ላይ ጦርነት ከማወጅ እንደማይተናነስ ታዛቢዎች ይናገራሉ፡፡
መረጃ ወደ ውጭ እንዳይወጣ እና ወደ ውስጥም እንዳይገባ ሲባል በአንዳንድ የአማራ ክልል ቦታዎች የስልክና የኢንተርኔት ግንኙነት በትክክል እንደማይሰራ መረጃዎች እየጠቆሙ ነው፡፡ በተለይ ወታደሮች በሰፈሩበት አካባቢ ከወታደራዊ መገናኛ ዘዴዎች ውጭ ሌሎች የስልክም ሆነ የኢንተርኔት አውታሮች ከአገልግሎት ውጭ እየተደረጉ ነው ተብሏል፡፡
በተወሰነ የአማራ ክልል ቦታ ብቻ ተወስኖ የነበረው ህዝባዊ ተቃውሞ በአሁን ወቅት ክልሉን ሙሉ ለሙሉ በሚያስብል ደረጃ እያዳረሰው እንደሚገኝ የሚገልጹት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ በተለይ በጢስ አባይ ህዝቡ ከፍተኛ ሰላማዊ ሰልፍ ማካሔዱን እና ከተማዋም በወታደሮች ተከብባ መዋሏን ተናግረዋል፡፡ በጢስ አባይ በነበረው ተቃውሞ አራት ሰዎች መገደላቸውንም ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፡፡ በስፍራው የተሰማሩት የጸጥታ ኃይል ወታደሮች ያገኙትን ሰዎች በተለይም ወጣቶችን እያፈኑ ሲያግዙ ታይተዋል፡፡
ዳንግላ በተባለችው ሌላኛዋ የአማራ ክልል ግዛት ደግሞ ወታደሮች የቤት ለቤት ፍተሻ በማድረግ ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቀ ወጣቶችን አፍሰው መውሰዳቸውን መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡ በተጨማሪም በአካባቢው የሚገኙ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችን እና አባላትንም ወስደው እንዳሰሯቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡ ደብረ ታቦር፣ ወረታ፣ አዲስ ዘመን፣ ጋይንት (ንፋስ መውጫ) እና አርብ ገበያ ሙሊ ለሙሉ የስራ ማቆም አድማ ላይ እንደሆኑ ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፡፡ ስማዳ ላይ በድጋሚ አራት ሰው ሲገደል፣ ለጊዜው ስሙ ያልታወቀ የእስልምና እምነት ተከታይ መገደሉን እና የቀብር ስነ ስርዓቱ መፈጸሙን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በተያያዘ ዜና፤ የደብረ ማርቆስ ህዝብ በዛሬው ዕለት ለሶስት ቀን የሚቆይ ከቤት ያለመውጣት አድማ ዛሬ ጠኋት መጀመሩ ታውቋል፡፡ በዚህም መሰረት የንግድ ተቋማት፣ መስርያ ቤቶች፣ የትራንስፖርት አገልግሎቶች እና መሰል የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት መቋረጣቸውን ከስፍራው የደረስን መረጃ ያመለክታል፡፡ በሌላ ዜና ደግሞ፤ ከወሎ የተነሳው የአጋዚ ጦር ወደ ጎንደር እና ጎጃም እንዳያልፍ የጋይንት ህዝብ ድልድይ መስበሩን የገለጹት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ገበሬው እና የከተማው ሰው አብሮ ወታደሩን ማለፊያ መንገድ እንዳሳጣው ገልጸዋል፡፡ እንደዚሁም አምባ-ጊዮርጊስ በተባለው ስፍራ ሌሊቱን ሙሉ የተኩስ ድምጽ ሲሰማ እንዳደረ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የተኩስ ልውውጡን ተከትሎም ከታጣቂዎችም ሆነ ከአርሶ አደሮች የተጎዱ መኖራቸውን ምንጮች የገለጹ ሲሆን፣ በባህርዳር ቀበሌ 14 አካባቢ ደግሞ ዛሬም የተኩስ ድምጽ ሲሰማ ነበር፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ የጎንደር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ግቢውን ጥለው መውጣታቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s