በርካታ አርቲስቶች የአዲስ አመት ኮንሰርቶቻቸውን ሰረዙ (አስቴር አወቀ፣ ማዴንጎ አፈወርቅ አብይ ላቀው መሐሪ ደገፋው ፋሲል ደሞዝ ታደለ ገመቹ ቴዲ አፍሮ )

በአሜሪካን አገርና በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች በአዲስ ዘመን የተለያዩ የመዝናኛ ዝግጅትች ይደረጋሉ። ዘፋኞች ይጋበዛሉ፣ ያው ዳንኪራ ነው። ሆኖም በዚህ አመት ብዙ ዘፋኞች ዝግጅቶቻቸውን እየሰረዙ ነው።

እስካሁን የሕዝብን ድምጽ በማክበር ሲዲያቸውን እና ኮንሰርታቸውን በመሰረዝ የሚክበሩ አርቲስቶች ስም ዝርዝር | ሌሎችም ኮንሰርታቸውን ሲሰርዙ ስማቸው እዚህ ይጨመራል | እነዚህን አርቲስቶች እናክብር – እናመሰግናለን::
1ኛ. ቴዲ አፍሮ – ሰው እየሞተ አልበሜን ለዚህ አዲስ አመት አላወጣም ብሎ የሰረዘ
2ኛ. ብርሃኑ ተዘራ – ኮንሰርቱን የሰረዘ
3ኛ. ማዲንጎ አፈወርቅ – ኮንሰርቱን የሰረዘ 
4ኛ. አስቴር አወቀ – ኮንሰርቷን የሰረዘች
5ኛ. መሐሪ ደገፋው – ኮንሰርቱን የሰረዘ
6ኛ. አቡሽ ዘለቀ – ኮንሰርቱን የሰረዘ
7ኛ) አብይ ላቀው- ኮንሰርቱን የሰረዘ
8ኛ) ኤፍሬም ታምሩ- ኮንሰርቱን የሰረዘ
9ኛ) አብዱ ኪያር- ኮንሰርቱን የሰረዘ
10) ፋሲል ደሞዝ- ኮንሰርቱን የሰረዘ
11) ታደለ ገመቹ- ኮንሰርቱን የሰረዘ
12) ይሁኔ በላይ- ኮንሰርቱን የሰረዘበጎድነር፣ ጎጃ፣ ወለጋ፣ ሃረርጌ በመሳሰሉት ቦታው ከፍተኛ የሆነ የሕዝብ ጭፍጨፋ እየተፈጸመ ነው። በአምባ ጊዮርጊስ ብቻ ከ26 በላይ ዜጎች ከየት እንደመጡ በማይታወቁ ታጣቂዎች ተገድለዋል። ከሴቶችና ክልጆች ዉጭ አብዣኛው የከተማዋ ነዋሪ ከቤቱ ሸሽቶ ወደ በረሃ ገብቷል። በአወዳይ ሃረርጌ በአድን ቀን ብቻ ከሃይ በላይ ዜጎች ነው የተገደሉት። በባህር ዳር ፣ ከአንድ ኮንዶሚኒይም ሶስተኛ ፎቅ ላይ ሆኖ በአልሞ ተኳሽ መሳሪያ 48 ዜጎችን በደቂቃዎች ዉስጥ ረሽኗል። በደብረ ታቦኢር፣ በቂሊንጦ እሥር ቤቶች እስረኞች በ እሳት እንዲጋይ ተደርገዋል።፡ደም በአገራችን እንደ ጎርፍ እየፈሰሰ ነው።

በዚህ ወቅት ዳንኪራ ማድረግ ነዉር ብቻ ሳይሆን ኢሞራል ነው። በዚህም ምክንያት በርካታ እንደ አስቴር አወቀ፣ ማዴንጎ አፈወርቅ ያሉ አርቲስቶች ብዙ ገንዘብ የሚያገኙበትን ኮንሰርቶች ሰርዘዋል። ቴዲ አፍሮ በአዲስ ዘመ ሊያወጣው የነበረውን አልበም አራዝሞታል። ህዝብ እየሞተ አላወጣም ብሎ። ለነዚህ ለሌሎች አጋርነታቸው ለወገናቸው ላሳዩ አርቲስቶች አክብሮቴን እገልጻለሁ።

ሆኖም አሁን በበዙ ቦታዎች ዳንኪራዎች እንደሚደረጉ ማስታወቂያዎች እየወጡ ነው። ተስፋ አለኝ ሁሉም በራሱ አነሳሽነት ዝግጅቶቻቸዉን እንደሚሰርዙ። ካልሰረዙ ግን በዚህ ወቅት እቼቼ ገዳሞ ማለታቸውን አንረሳውም።

Tilaye Tarekegn ZE Ethiopia's photo.

 

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s