ከጎንደር ህብረት ዓመታዊ ጉባኤ የተላለፈ የአቋም መግለጫ

በቅድሚያ የጎንደር ሕብረት የመጀመሪያ ድርጅታዊ ጉባዔውን ሲከበር፤ ጠባቡ የትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር በከፈተው ጦርነት፤ ለነጻነት ትግሉ ፋና ወጊ ሆነው፤ ለተሰው ጀግና ወንድም እና እህቶቻችን፤ ለክብር ሞታቸው የተሰማንን ጥልቅ ኃዘን ለየጎንደር ብሎም ለምላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ስንገልጽ፤ የሕዝብን የነጻነት አርማ አንግበዉ የሂይዎት ዋጋ የከፈሉበትን ዓላማ ከግቡ ለማድረስ ቃል መግባታችን ልናረጋግጥ እንወዳለን።

የጉባኤው መክፈቻ ንግግር በወቅቱ ሊቀመንበር በአቶ አበበ ንጋቱ፤ የጎንደር ህብረት ለዚህ ታሪካዊ ጉባኤ በመድረሱ የተሰማቸውን ከፍተኛ የደስታ መልክት ለጉባኤተኛው አስተላለፈው፤ ከዚያም በዋና ፀሐፊው አጠቃላይ ጎንደር ሕብረት ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ያደረጋቸውን የሥራ ክንዋኔዎች ሪፖርት አቅርቧል። በመቀጠልም የሂሳብ ዘገባና የድርጅቱ መዋቅራዊ የሥራ እንቅሥቃሴ በሰፊው ከተደመጠ በኋላ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች በጎንደር ክ/ሀገር ምሁራን ከዚህ በሚከተሉት አር ዕስቶች ላይ ሰፋ ያለ ትምህርታዊ ትንታኔ ቀርቧል

1. የጎንደር ሕብረት ለምን አሥፈለግ፤
2. የጎንደር ታሪክ፤
3. የጎንደር የምጣኔ ኃብት ምንጭ፤
4. የፍትሕ ምሶሶዎች እና የሚዲያ አስፈላጊነት፤
5. የቅራኔዎች አፈታት እና አያያዝ (Conflict Resolution).
6. ከምድረ ዕስራኤል አገር የቻፕተር ተወካይ ሊቀመንበር፤ “የዮቶር ኢትዮጵያ የጎንደር አባታችን ታሪክ ማወቅ”

በሚል የምርምር ጽሁፍ ቀርቦ፤ ጉባኤው በሰፊው ተወያይቶበታል።

በተጨማሪም በአሁኑ ሰዓት፤ በጎንደር ሕዝብ ላይ ያነጣጠረውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ መቋቋም እና ለዓለም ማህበረሰብ ለማሳወቅ በአፈፃጸም እቅዶች ላይ ሰፊ ውይይት አካሂዷል። ሌላው ይህ ጉባኤ አገራችን ኢትዮጵያ ከገባችበት እጅግ አደገኛ የፖለቲካ ቀውስ ለማውጣት ጠቃሚ ናቸው ብሎ ጉባኤው ባመነባቸው የትብብር እና ዲፕሎማሲ ተግባሮች ጠንክሮ ለመሥራት ቆራጥ አቋም ወስዷል።

በታሪክ አጋጣሚ በአገራችን ኢትዮጵያ ላይ ጠላት በጭካኔ ሲዘምትብን ከጣሊያን ተደጋጋሚ ጥቃት ጋር ሲነፃጸር ይህ እጅግ የከፋ የጥፋት አደጋ መሆኑ ልዩ የሚያደርገው ደግሞ ዎያኔዎች አገር በቀል በመሆናቸው የኢትዮጵያውያንን ልብ የሚሰብር አስከፊ ገጽታ መሆኑን የጉባኤው ተሳታፊው አሥምሮበታል። ሁሉም የአገሪቱ ዜጋ ተባብሮ መታገል እንዳለበትም ለሁሉም አገራቸውን እና ሕዝባቸውን አፍቃሪ ለሆኑ ዜጎች ጥሪዊን አስተላልፏል።

በተለይ በጉባኤው የተሳተፉ ሴት እህቶቻችን እና ወጣቶች በጎንደር/አማራ ብሎም በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ግፍ እና በደል ሲገልፁ እንባ እየተናነቃቸው የጉባኤውን ተሳታፊዎች ልብ ከመንካቱ በላይ የዚህ ድርጅት አባላትም ሆነ የአመራር አካላት ለገቡበት ዓላማ ቁርጠኝነት የተሞላበት ወኔ አሳይቷል።

እንዲሁም ጠንከር ባለ አገላለጽ የወልቃይት ጠገዴ፤ ጠለምት፤ ቃፍቲያ እና ሁመራ ተከዜ ደምበራችን ነው የሚለወ የጎንደር ሕዝብ ጥያቄ ለድርድር የማይቀርብ የማንነት እና የመብት ጥያቄ መሆኑን ተገንዝቦ ጥያቄውን ከግቡ ለማድረስ ጎንደር ህብረት የትግል ቃል ኪዳኑን አድሷል።

በተጨማሪም ወያኔ በጎንደር ብቻ ሳይሆን በጎጃም፤ በሸዋ እና እዲሁም በመላ የኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ ከዉጭ የባእድ ሰራዊት በማስገባት ጭምር እያደረሰ ያለውን ጭካኔ የተሞላበት ጭፍጨፋ የኢትዮጵያን ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ወያኔ የሚተማመንበትን ሰራዊት ጭምር የሚያሸፍት ተግባር እንደሆነ ጉባኤው አስምሮበታል።

ከዚህ በላይ ያስቀመጥናቸው በህዝባችን ላይ እየተፈጸሙ ያሉትን በደሎች ለማስወገድ ጎንደር ሕብረት ተጠናክሮ ለመታገል በመተዳደሪያ ደንቡ ላይ ሰፊ ውይይት ካካሄደ በኋላ ዋና ዋና በተባሉት ዓላማና መርሆች ላይ ለውጦችን አድርጓል። በድርጅቱ ስያሜ ላይም ማሻሻያ አድርጓል ፤ ይኸውም አርማው እና ጎሕ የሚለው ምልክት እንዳለ ሆኖ በአፃፃፍ ላይ “የጎንደር ሕብረት፤ ለኢትዮጵያ አንድነት እንዲባል ተወስኗል።

ጉባኤው አገራዊና ድርጀታዊ ጉዳዮችን በጥልቀት ከተወያየ በኋላ የሜከተሉትን የአቋም መግለጫ አስተላልፏል፦

1. በዘር የተቧደኑት ጥቂት የወያኔ ጨፍጫፊዎች በህዝባችን ላይ የሚያደርጉትን የ11ኛ ሰዓት አልሞት ባይ ተጋዳይነት የዘር ማጥፋት ጦርነት እንዲያቆሙ፤

2. ይህ የአጥፊ ቡድን ከዚህ በኋላ የኢትዮጵያን ሕዝብ መምራት የማይችልበት ደረጃ መድረሱን ተገንዝቦ ሥልጣኑን ለሕዝብ እንዲያሰርክብ፤

3. የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር ቡድን ከልክ ያለፈ የንዋይ እና የቁሳቁስ ዘረፋውን በአስቸኳይ እንዲያቆም፤

4. ወያኔ ከሥልጣን ላይ ለመቆየት ሲል በአብሮነቱም ሆነ በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደረውን የትግራይ ህዝብ ከመላው ኢትዮጵያ ጋር ለማጋጨት የሚጎነጉነውን ዘመቻ በአስቸኳይ እንዲያቆም፤

5. እንዲሁም በአገራቸው እና በህዝባቸው አንድነት ዙሪያ ልዩነት የሌላቸው የፖለቲካ ድርጅቶች፤ የብዙሃን ማህበራት፤ የኃይማኖት ተቋማት በአስቸኳይ አገርን ለማዳን የትብብር ሥራ እንዲሰሩ፤

6. ማንኛውም በኢትዮጵያ ላይ እውነተኛ ለውጥ ለማምጣት የሚፈልግ ድርጅትም ሆነ ግለሰብ፤ ወይም ቡድን ከዚህ እጁ በደም ከታጠበ መንግሥት ጋር ለመደራደር እንዳይሞክር፤

7. በመላ አገራችን እየተቀጣጠለው ያለው የህዝብ ትግል ባለቤቱ ራሱ የኢትዮጵያ ሕዝብ መሆኑን አምነን በደም እና በአጥንቱ የሚገነባው ሥራዓት ባለቤት እንዲሆን ከጎኑ መቆም ታሪካዊ እና የዜግነት ግዴት መሆኑን ተገንዝበን ሁላችንም ከድርጅት ኮፈን ወጥተን ከህዝባችን ጋር በአጋርነት እንድንቆም አደራ እንላለን።

8. በቅሊንጦ እስርቤት አቶ በቀለ ገርባ እና ብዙ የፖልቲካ እና የህሊና እሥረኞች ላይ በወያኔ የተቀነባበረ የግድያና የሳት ማቃጣል ሴራ በጥብቅ እናወግዛለን።

9. የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር የእስረኛ ቤተሰቦች እና የህዝብን ህሊና የማስጨነቅ ኢሰባዊ ድርጊት አቁሞ በህይወት ያሉና የተገደሉ ወገኖቻችን ስም ባስቸኳይ ይፋ እንዲያደርግ ።

10. እንዲሁም የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድ ድምጽ ወጥቶ በፖለቲካና በህሊና እስረኞች ላይ የደረሰዉን ጭፍጨፋ በቁጣ እንዲገልጽ እንጠይቃለን!!

መሪላንድ/ባልቲሞር

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s