ወያኔን በመቃወም ኢትዮጵያውያን በጀርመን ዋና ከተማ በርሊን ጎዳና ታላቅ የሰላማዊ ሰልፍ ትእይንት አካሄዱ

ለተጠናከረው  ዘገባ ዘርይሁን ሹመቴ ከጀርመን

Anti Ethiopian government protest in Germany, Berlin

በጀርመኗ  ዋና  ከተማ በርሊን( Germany Berlin) ዛሬ ጳጉሜ 4፣2008ዓም (09 Sep 2016) ኢትዮጵያውያን  ወያኔን  በመቃወም  ታላቅ  ሰልፍ  አድርገዋል።  መላው  የኢትዮጵያ  ህዝብ  በጨቋኞች  አምባገነንና  ከፋፋዮች መገዛት በቃን  ብሎ አደባባይ  ወጥቶ  ጸረ ወያኔ ትግሉን ለወራት አፋፉሞ  ቀጥሏል። ለተከበረው አርንጓዴ  ቢጫ   ቀይ  ባንዲራም እጅግ ከፍተኛ የሆነ  መስዋትንም  እየከፈለ ይገኛል። የኢትዮጵያ  የቁርጥ ቀን ልጆች በየቦታው እየተገረፉና  እየተደበደቡ በየእስር ቤቱ  ታጉረዋል። ከፊሎቹም  ያለምንም  ርህራሄ በወያኔ ወታደሮች ተገድለዋል።  በሃይለማርያም   የሚመራው  የወያኔ  አምባገነናዊ  መንግስት በንጹሃን የኦሮሞ እና የአማራ  ህዝብ  የፈጸመውን እንዲሁም እየፈጸመ ያለውን አፓርታይዳዊ  ግድያ፣ እስራት፥ድብደባና ጭቆና ለማውገዝና  አለም አቀፉ ማህበረሰብ በወያኔ ላይ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ጫና እንዲያደርግ   በተለያዩ  የጀርመን  ከተሞች  የሚኖሩ  ኢትዮጵያውያን የተለያዩ  ኢምባሲዎች  እና የመርሃዊ መንግስቱ መቀመጫ  በሆነችው  በበርሊን ጎዳና  ለተቋውሞ ወጥተዋል።  በዚህ  ለአገራችን  ፈታኝ  በሆነባት  ወቅት የወያኔን  አረመነዊያዊ  ተግባራቱን  ለአለም  በተለያዩ  መንገዶች  በመንቀሳቀስ  እያሳወቁ የሚገኙ  በጀርመን  አገር  የሚገኙ ኢትዮጵያውያን  ትላንት ጳጉሜ 3፣2008 ዓም ( 08 Sep 2016)በፍራንክፈርት የሚገኘውን  የኢትዮጵያን ቆንጽላ  ለሰአታት በመቆጣጠር ወያኔ ስልጣኑን  ለሽግግር መንግስት በሰላም  እንዲያስረክብ አለዚያ ግን በሃይልም  ቢሆን ከስልጣኑ  እንደሚወገድ ጀግንነት  በተሞላው  ድርጊት ለአምባሳደሩን  አሳውቀዋል።

Ethiopians protest in Germany, Berlin (September 9, 2016)

በበርሊኑ  የተቋውሞ ሰልፍ  በኢትዮጵያውያ ውስጥ   ወያኔ   እየፈጸመ ያለውን  የመብት ረገጣ እስራት  እንዲሁም  ግድያ  የጀርመን  መንግስት አይቶ  እንዳላየ  ሰምቶ እንዳልሰማ መሆን  እንደሌለበት  እንዲሁም  በየአመቱ  ዳጎስ  ያለ  የገንዘብና  የቁሳቁስ  ጥቅማጥቅም  ክቡር  የሆነውን  የሰውን  ልጅ  ያለርህራሄ  ለሚያጠፋ እንደወያኔ  ላለው  መንግስት  መስጠቱን  እንዲያቆም  ተጠይቋል። የኤርትራን የሶማሌንና  የደቡብ  ሱዳን ስደተኞችን  ወደ  አውሮፓ እንዳይመጡ  በሚል  ሰበብ  የጀርመን  መንግስት ወያኔ  ጡንቻውን  የሚያጎልበትን  በሚሊዮኖች ዮሮ  የሚቆጠር

ገንዘብ  በየአመቱ  እንደሚለግስ ይታወቃል። ሰልፈኞቹ  ዜጎችን  እያሸበር ለሚገድል ለሚያስር ለሚያሰቃይና ለሚያሳድድ  ለወያኔ  አገዛዝ የጀርመን  መንግስት   የሚያደርገውን  ኢኮኖሚያዊና ወታደራዊ ድጋፍ እንዲያጤነው አሊያም  እንዲያቆም  ጠይቀዋል። የጀርመን መንግስት ይህንን  ማድረግ ካልቻለ ወይም ካልፈለገ  እንደ ገዳዩ የወያኔ መንግስት ተጠያቂ ከመሆን  አያመልጥም።

ከጀርመን የውጭ  ጉዳይ ቢሮ  (Auswärtiges Amt) መነሻውን ባደረገው  በዚህ በበርሊኑ  ተቃውሞ  ላይ  ሰልፈኞቹ   በአጋዚ ጦር  ለተገደሉት ንጹሃን  ኢትዮጵያውያን  የተሰማቸውን ሃዘን ጥቁር  በመልበስ  ገልጸዋል። እጃቸውን ወደላይ  በማጠላለፍ  ኢትዮጵያውያን በጎንደር  በባህርዳር በጎጃም በኦሮምያና እንዲሁም  በሌሎች ክፍሎች ውድ  ህይወታቸውን  እየገበሩረለት ለሚገኘው  ትግል  አጋርነታቸውን  አሳይተዋል። ከዚህም  በተጨማሪ በእንግሊዘኛ  በጀርመንኛ በአማርኛና በኦሮምኛ  የወያኔን አረመናዊ  ግድያ ፣ አምባገነናዊነት፣ ጎጠኝነት እንዲሁም  አሸባሪነት በተለያዩ መፈክሮች ለጀርመን ነዋሪዎች፣ ባለስልጣናት እንዲሁም  ታሪካዊዋን  የበርሊንን ከተማ ለማየት ለመጡት ቱሪስቶች ከፍ ባለ ድምጽ ሲያሰሙ  አርፍደዎል። ጀርመን ተወልዳ ያደገች የ17 አመት ኢትዮጵያዊ  ወላጆቹዋን አጅባ በተቋውሞ  ሰልፍ በመገኘት  ከእሱዋ  እድሜ  ያነሱትን ተማሪዎችን እንኩዋን  ያለመራራት በኢትዮጵያ ውስጥ በአልሞ  ተኩዋሽ ጭንቅላታቸውን በጥይት  በመምታት የሚገድለውን የወያኔ ሃርነት ትግራይ  መንግስትን ለመቃወም ከመታደሙዋ  በላይ በተማርችበትና አቀላጥፋ  በምትናገረው   በጀርመንኛ ቋንቋ የተቋውሞውን  ሰልፍ  የኢትዮጵያን ባንዲራ ለብሳና ተሸክማ  በመምራት በትንግርት ለሚመለከቱት  የጀርመን ዜጎች ኢትዮጵያውያን ለ25  ዓመታት በወያኔ መንግስት  የደረሰባቸውን  ስቃይ መከራና ግድያ በመፈክርና  በንባብ አስረድታለሽ። ይህች  የ17አመት ታዳጊ  ኢትዮጵያ  የሚያኮራ ታሪክና ጀግና ህዝብ ያላት መሆናን  ድምጿን በተሰጣት የድምጽ ማጉያ  ከፍ  አድርጋ በኩራት በበርሊን  ጎዳናዎች  ተገርመው  ለሚመለከቱት  ጀርመናዊያን እየደገጋገመች ስትናገርና  ሰልፈኞቹም ከሷ በመከተል  በአንድ  ድምጽ ሲያስተጋቡት በርግጥም የወያኔ የ25 ዓመታት የመከፋፈልና  የጎጠኝነት ስትራቴጄው ሞቶ አፈር  እንደላሰ ምስክር ነው። በዚህ አጋጣሚ   የወለዱዋትና ያሳደጓት  አባትና እናት  ይህችን  ኩሩ  አበሻ  ስለሰጡን  ብቻ ሳይሆን ባህሏን  ህዝቧን አገሯን እንድትወድ አድርገው  በሰው  አገር ስላሳደጉ መደነቅና መመስገን ይገባቸዋል።

ሰላማዊ  ሰልፉ  በርከት ባለ  የጀርመን የጽጥታ  ሃይል በመታገዝ ውብና  አላማውን  ሙሉ በሙሉ የመታ ሆኖ ተጠናቋል። ነገር ግን ከጥንሰሱ  እስከ  ፍጻሜው  ጉልበታቸውን  ገንዘባቸውንና  ጊዜያቸውን  ሰውተው  ይህንን የተሳካ የተቋውሞ  ሰልፍ  ያዘጋጁት  በመላው  ጀርመን  የሚገኙ  የስቪክ ማህበራት ከፍ ያለ አድናቆትና  ምስጋና ይገባቸዋል። ሰልፉን  በዋናነት  ሲመሩ  የነበሩት አቶ ታደሰ  ሃይሉ  እነዚህ የስቪክ  ማህበራት ሙሉ  ሃላፊነቱን ወስደው የወያኔን አረመናዊ ባህርይንና  በንጹሃን  ኢትዮጵያውያን ላይ ያደረሰውን እያደረሰ  የሚገኘውን ኢሰብአዊ ድርጊቶችን ለአለም ለማጋለጥ እንዲህ አይነት ስምምነት ኢትዮጵያዊነትና አንድነት የተሞላበትን ሰልፍ  ለማዘጋጀት፣ለማስተባበርና በተሳካ ሁኔታ ለመተግበር ኮሚቴው  ከፍተኛ የገንዘብና የጌዜ መስዋትነት እንደከፈለ  ገልጸዋል።

የሰልፉ ዋና አላማዎች

1ኛ ለኢትዮጵያ ህዝብ አጋርነትን መግለጽ

2ኛ ወያኔ በኢትዮጵያ  ህዝብ ላይ  እየፈጸመ  ያለውን  ወንጀል   እንዲያቆም ማስጠንቀቅ

3ኛ አለአግባብ የታሰሩ የህዝብ ተወካዮች ጋዜጠኞች የፖለቲካና የሀይማኖት መሪዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ከፍተኛ ግፊት በማድረግ

4ኛ ወያኔ ኢህአዲግ ሃገሩንና ህዝቡን ማስተዳደር ስላልቻለ በአስቸኩዋይ ከስልጣን እንዲወርድ ማሳሰብ

5ኛ የጀርመን መንግስት ወያኔን በገንዘብም ሆነ በቁሳቁስ  መርዳቱን እንዲያቆም መጠየቅ ይገኙበታል።

ይህ የተቋውሞ  ሰልፍ በጀርመን  የውጭ ጉዳይ ቢሮና  በመርሃዊ መንግስቷ አንጌላ መርክል ጽህፈት ቤት ብቻ ሳይሆን  በርሊን  ከታሪካዊውና በብዛት ከሚጎበኘው  ብራንደን በርግ ቶር አጠገብ  በሚገኘው በዩናይትድ ስቴትስና በፈረንሳይ ኢምባሲዎች እንዲሁም በአውሮፓ  ህብረት ህንጻ ፊት ለፊትም  ጭምር ነበር። የበርሊኑ  የተቋውሞ  ሰልፍ የአቋም መግለጫ ደብዳቤዎችን  ለጀርመን ፌዴራላዊ ሪፐፕሊክ ፕሪዝዳንት፣ ለካንስለር አንጌላ መርክል፣ ለውጭ ጉዳይ ቢሮ፣ለፓርላማው እንዲሁም በጀርመን የልማትና እድገት እርዳት ቢሮ በመስጠት ተጠናቁዋል።

በተለያዩ  አገራት የሚገኙ  ኢትዮጵያውያን እንደዚህ የመሰለ  የተቋውሞ ሰልፎች ፣ ዲፕሎማሲያዊ  ግፊቶች እንዲሁም  የፔቲሽን  ፊርማዎችን  በማዘጋጀት  የአለም አቀፍ ማህበረሰብ  ወያኔ በሚመራው መንግስት ላይ  ከፍተኛ ጫና እንዲያደርጉበት እንቅስቃሴ  እያደረጉ  መሆኑ ይታወቃል። በጳጉሜ 2ቀን 2008ዓም የአውሮፓ  ህብረት ወያኔ በንጹሃን  ሰልፈኞች  ላይ  የወሰደውን  የግድያና  የሰብአዊ መብት ጥሰት ምርመራ  በማድረግ  ለወያኔ መንግስት ሊለግስ  ያቀደውን  እርዳታ ላልተወሰነ ጊዜ ማቀቡን  ይፋ  አድርጓል። ወያኔ  የሚመካባት  ዩናይትድ  ስቴትስ እንኩዋን የኋላ  ኋላ በኢትዮጵያ ውስጥ በንጹሃን  ህዝብ ላይ እየተወሰደ  ያለውን ወታደራዊ  እርምጃ  እንደሚያሳስባት በይፋ  መግለጽ  ለወያኔ  ጀርባዋን መስጠት እንደጀመረች አመላካች  ሆኗል።

By Zerihun Shumete/ From Germany

– See more at: http://ecadforum.com/Amharic/archives/16934/#sthash.unyIdPag.dpuf

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s