ወንድማችን አቡበክር አህመድ መሀመድ እንኳን በሰላም ተፈታህ!

ሥዩም ወርቅነህ

Abubeker Ahmed Ethiopian Muslims fact finding committee member

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ 4 ዓመት(አሁን 5 ዓመት ተደረገ እንጂ እኔ ስማር 4 ዓመት ነበር) የህግ ትምህርታችን ጨርሰን ልንመረቅ ስንል አንድ ጓደኛዬ ሥዩም በፓርቲ ውሳኔ የሚሰጥበት አገር ላይ ህግን ተከትሎ የሚወሰን ውሳኔ ስለሌለ የህግ እውቀት ለመበሳጨት ካልሆነ በስተቀር ፋይዳው አይታየኝም ብሎኝ ነበር። እውነቱን ነበር!….

ከዚህ ፅሁፍ አባሪ ባደረኩት የይቅርታ የምስክር ወረቀት መሰረት አቡበክር (አቡኬ) ጥፋተኛ ተብሎ የተፈረደበት “በሃይማኖት አክራሪነት ወንጀል” እንደነበር ነው። በኢትዮጵያ የወንጀለኛ ህግም ሆነ በሌላ አዋጅ የሃይማኖት አክራሪነት ወንጀል ሆኖ የሚያስቀጣ መሆኑን የሚገልፅ የለም። እነ አቡኬ የተፈረደባቸው የፓርቲ አለያም የፖለቲካ ውሳኔ ነው ለዚህም ህዝብ የማያውቀው ገዢዎቹ ብቻ የሚያውቁት ህግ አለ የሚሉን ከሆነ ያስማማን ይሆናል። በእርግጥ እነ አቡኬ የተፈረደባቸው ህዝበ ሙስሊሙ ወክሏቸው ህገ-መንግስታዊ የእምነት ነፃነት መብታቸው በመጠየቃቸው እንጂ ህገ-ወጥ ስለነበሩ አልነበረም። ይህ ሀቅ ነው!

ሌላው የተከሰሱትና የተፈረደባቸው በአሸባሪነት ሆኖ ሳለ “በተከሰሱበት በሀይማኖት አክራሪነት ወንጀል ጥፋተኛ በመሆንዎ” ማለት ምን ማለት ነው? ኧረ ሼም የሚባል ነገር አለ ወየንቲዎች!

አሁንም እንላለን ንፁሃን ዜጎች አስሮ ማሰቃየት አግባብ የሌለው በመሆኑ የተቀሩት መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችም ሆነ የፖለቲካ እስረኞች ወንጀለኞች ስላልሆኑ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ፍቷቸው።

ምንም እንኳን ከፊል የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ቢፈቱም ህዝበ ሙስሊሙ አንግቦ የተነሳው ህገ-መንግስታዊ የእምነት ነፃነት ሦስት ጥያቄዎች አሁንም ስላልተመለሱ ሊመለሱ ይገባል። የህዝበ ሙስሊሙ ሦስት ጥያቄዎች የሚከያተሉት ናቸው፦

1. የአህባሽ አስተምሮ በግዳጅ አይጫንብን። አህባሽ ከኢትዮጵያ ይጥፋ አላልንም።
2. ያልመረጥናቸው የመጅሊስ አመራሮች አይመሩንም።
3. አወልያ ብቸኛ የህዝበ ሙስሊሙ ተቋም እንደመሆኑ መጠን ከህዝብ በሚመረጥ ቦርድ ይተዳደር።

ኮሚቴዎቹ ማሰርም ሆነ መፍታት ህዝበ ሙስሊሙ ወደ ቤቱ የሚመልሰው ባለመሆኑ እኝህ ከላይ የተጠቀሱት 3 ጥያቄዎችን መመለስ አማራጭ የማይገኝለት መፍትሄ ነው።

ድምፃችን ይሰማ!
ትግሉ ይቀጥላል!

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s