በምዕራብ አማራ የተለያዩ አካባቢዎች እሥራቶች እየተካሄዱ መሆኑን የሚጠቁሙ መረጃዎች እየደረሱን ነው፡፡VOA

በምዕራብ አማራ የተለያዩ አካባቢዎች እሥራቶች እየተካሄዱ መሆኑን የሚጠቁሙ መረጃዎች እየደረሱን ነው፡፡


በምዕራብ አማራ የተለያዩ አካባቢዎች እሥራቶች እየተካሄዱ መሆኑን የሚጠቁሙ መረጃዎች እየደረሱን ነው፡፡

በምዕራብ አማራ የተለያዩ አካባቢዎች እሥራቶች እየተካሄዱ መሆኑን የሚጠቁሙ መረጃዎች እየደረሱን ነው፡፡

በጎንደር፣ በአዴት፣ በዳንግላና ሌሎችም ሥፍራዎች የታሠሩ ሰዎች መኖራቸውንና የወልቃይት የአማራ ማንነት ኮሚቴ ዋና ፀሐፊም እየተፈለጉ መሆናቸው ተሰምቷል፡፡ ስለሁኔታው መረጃ እንደሌላቸው የኮሚቴው ዋና ፀሐፊ አቶ ተሻገር የሚሠሩበት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የፀጥታና የደኅንነት ኃላፊ አመልክተዋል፡፡

እንዲሁም ዳንግላ ላይ የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ – መኢአድ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የፓርቲው የሰሜን ቀጣና ኃላፊ አቶ ሙሉቀን ዐይናለም ተይዘው ዳኛ ፊትም ሳይቀርቡ፣ ክሥም ሳይመሠረትባቸው ለአሥር ቀናት መታሠራቸውን ባለቤታቸው ገልፀዋል፡፡

አዴት ላይም የፓርቲው የይልማና ዴንሣ ወረዳ ተጠሪ የሆኑት አቶ ስመኘው ገሠሠ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ተኩል ላይ ከመኖሪያ ቤታቸው በታጣቂዎች ተይዘው መታሠራቸውና ወደ ብር ሸለቆ መወሰዳቸውን የመኢአድ ምክትል ፕሬዚዳንት ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

በተለያዩ አካባቢዎችም በርከት ያሉ የጅምላ እሥራቶች እየተከናወኑ ሲሆን እንቅስቃሴዎቹ የተሣሣቱ ወጣቶችን ለማስተማር፤ በወንጀል ተጠያቂ ስለመሆናቸው ማስረጃ ያለባቸውን ደግሞ ሕግ ፊት ለማቅረብ ነው ሲሉ የክልሉ መንግሥት ቃል አቀባይ አስረድተዋል፡፡

ለተጨማሪ ሙሉው ዘገባ የተካተበበትን እንዲሁም ሙሉ ቃለ-ምልልሶች የያዙትን የድምፅ ፋይሎች ያዳምጡ፡፡

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s