አዳዲስ መረጃዎች ….. የጉድ ዘመን መጣልን ጠበል መሸጥም ተጀመረልን {ዘመድኩን በቀለ}

እባክዎ ይህን መልእክት Share በማድረግ ኦርቶዶክሳውያን በሙሉ እንደዲነቁና እንዲዘጋጁ እናድርግ ።

ዋጋው 15 ሊትሩ ጠበል 5 ብር ተተምኖለታል ። ድሆች እርማችንን እናውጣ ።

በቀጣይ መስቀል ለመሳለም ፣ ቅዳሴ ለማስቀደስም ክፍያ ሳይጠይቁ አይቀርም እየተባለም ነው ።

ከዛሬ ጀምሮ በጎንደርና በጎጃም የሚገኙ አብያተክርስቲያናት በሙሉ ለማእከላዊው የጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር አንገዛም ለአቡነ ማትያስም አንታዘዝም አሉ የሚል ዜና እየወጣ ነው ።

matiasአሁን አሁን የቤተክርስቲያንን ክብር ዝቅ ያደረጉ የመሰላቸው ሰዎች በየሥፍራው ባላቸው መንግሥታዊ ስልጣን በመጠቀም በቅድስት ቤተክርስቲያን ላይ ክብሯን ዝቅ ያደርጋል የሚሉትን ተግባራት በሙሉ ያለአንዳች ከልካይና ተቆጪ በነፃነት በመፈጸም ላይ ይገኛሉ ።

ታቦት መሸጥ ፣ ቅርሶቿን መዝረፍ ፣ ይዞታዎቿን መውረስ ፣ የመስቀል አደባባዮችና የጥምቀት ባህሮችን ለኢንቨስተር መሸጥ ዋና ሥራቸው ከሆነ ውሎ አድሯል ። ይህ የተለመደ ቢሆንም አሁን በውስጥ መስመር ከሚደርሱኝ ብዛት ያላቸው መረጃዎች መካከል አንዱን አሳፋሪ የጠበል ሽያጭን የተመለከተውን ዜና እነሆ ብያለሁ ።

በምስራቅ ሸዋ ዞን በቦሰት ወረዳ በቆምቤ ቀበሌ ውስጥ የሚገኙ ወጣቶችን ሰብስቦ ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በማቋቋም በጥቃቅንና አነስተኛም በማደራጀት ፤ ፀበልን በሊትር እየሸጡ ይጠቀሙ ዘንድ የክልሉ መንግሥት የወረዳው ሰዎች ካርኒና ደረሰኝ አዘጋጅተው ለሥራ አጥ ወጣቶች በመስጠት የአከባቢው ወጣቶችን በጸበል ንግድ ላይ ላይ እንዲሰማሩ ማደረጉን ከሥፍራው የመጣ መረጃ ያመለክትናል።

ይህ ሁሉ ሲፈጸም እነ ፓትርያርክ አባ ማትያስና በየሀገረ ስብከቱ እየተሾሙ የሚላኩት ከአንድ ብሄር የሚውጣጡ ሹመኛ የቤተክህነቱ ባለስልጣናት ምንም አይነት ደንታም እንደማይሰጣቸው ተቃውሞም እንደማያሰሙ ይታወቃል ።

ዛሬ ጠበል በጠራራ ፀሐይ በደረሰኝ ከቤተክርስቲያን ቀኖና ውጪ መሸጥ ከተጀመረ ነገ እነዚህ ጉደኞች ምን ሊያመጡብን እንደሚችሉ ከወዲሁ መገመት አያቅተንም ።

እናም የተከበራችሁ የእምዬ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች በሙሉ አሁን መንግስት በሹመት ቤተክርሲትያን ላይ በግድ የጫነብንን የአቡነ ማትያስ አገዛዝ ከላይ እስከታች ገንዘብ ባለበት ሥፍራ ሁሉ የአንድ ብሄርና የአንድ ቋንቋ ተናጋሪዎችን ሰግስጎ ሰግስጎ በማስቀመጥ እንደመዥገር የሚመጠምጧትን ነቀዞች ማስቆም የምንችለው በአሁን ሰዓት ለቤተክርስቲያን የምንሰጠውን ማንኛውንም አይነት ገንዘብ ለጊዜው ማቆም ስንችል ነው ።

አሁን አሁን የሚደርሱኝ መረጃዎች እንደሚያሳዩኝ ከሆነ በጎንደርና በጎጃም የሚገኙ አብያተክርስቲያናት የሚያስደነግጥ እርምጃ በመውሰድ ላይ ይገኛሉ ።

በተለይ በጎጃም እና በጎንደር በኦሮምያም በሙሉ የፓትርያርክ አባ ማትያስ የሰፈር ልጆች በወሰዱት ጭካኔ የተሞላበት ጭፍጨፋ ፓትርያርኩና ሲኖዶሳቸው ዝምታን በመምረጥ ለሟቾች እና ለተጎጂ ቤተሰቦች መጽናናትን እንኳን ባለመመኘታቸው ፤ በተለይ በጎንደርና በጎጃም የሚገኙ አድባራትና ገዳማት ከዛሬ ጀምሮ ለዋናው መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ባለመታዘዝ ስባሪ ሳንቲም እንደማይልኩ በይፋ የማወጃቸው ዜናም በመላው ዓለም እየናኘ ይገኛል።

ይሄ ለዘረኛው ቤተክህነት በተለይ በአንድ ብሄር ተደራጅተው ከአለቃ እስከ ዘበኛ ድረስ ቤተክርስቲያኒቱን ለሚግጡት ነውረኞች ወደ መቃብር ለመውረዳቸው ትልቅ ምልክት ነው ።

በዚሁ መልኩ በለፉት 25 ዓመታት ከሳውዲ አረብያ የነዳጅ ጉድጓዶች በበለጠ የገዢው ፓርቲ ትጥቅና ስንቅ መግዣ የሚሆን ገንዘብ ሲሰበሰብበት የነበረውን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የዋና ሥራ አስኪያጅነት ሥፍራ ከትግራይ ተወላጆች ውጪ ሌላ ሰው እንዲይዘው አይደረግም ።

ለምሳሌ በቅርቡ እንኳን በሚልየን የሚቆጠር ብር ለልጁ ማሳከሚያ የሚሆን ገንዘብ ኮሚቴ በማዋቀር ጭምር ዘርፏል ተብሎ በብዙ ጩኸት ከአዲስ አበባ ሀገረስብከት ሥራአስኪያጅነት በተባረረው የኢቴቪ የትግርኛ ዜና አንባቢ በሆነው በአቶ የማነ ምትክ ጭራሽ አማርኛ እንኳን በቅጡ መናገር የማይችል ጎይቶም የተባለ ሰው በቦራው ሾመውበት በነጻነት ለአማራና ኦሮሞ ልጆች መግደያ የሚሆነውን ጥይት መግዣ የሚያገኙበትን ሥፍራ በቁጥጥር ስር እንዲውል አድርገውታል ።

እናም የተከበራችሁ ምእመናን ይህን ዐይን ያወጣ ዘረፋና ሌብነት ማስቆም የምንችለው በወርሀ ጳጉሜ የጀመርነውንና እስከ ህዳር ወር መጨረሻ ለ3 ወር ያህል የሚቆየውን የሙዳይ ምጽዋትና የአስራት በኩራት እቀባው አጠናክረን ስንቀጥል ነው ።

ማሳሰቢያ ለምእመናን በሙሉ

1ኛ፦ አስራት በኩራት የምታወጡም ሆነ ለሙዳየምጽዋት የምትሰጡት ገንዘብ ለእግዚአብሔር የምንሰጠውና አምላካዊ ትእዛዝ መሆኑን እንዳትዘነጉ ።ስለዚህም ምእመናን ይህ ለእግዚአብሔር የምናወጣው የራሱ የእግዚአብሔርን ገንዘብ ለግል ጥቅማችሁ ማዋል ስለሌለባችሁ በቤተሰብ ደረጃ ተመካክራችሁ አስፈላጊውንም ዘዴ ቀይሳችሁ የእግዚአብሔርን ገንዘብ ለይታችሁ ለብቻው አስቀምጡ ። ይህ የአደራ ማሳሰቢያዬ ነው ።

2ኛ፦ እንደሚታወቀው ይህ እርምጃችን ውጤታማ እስኪሆን ድረስ ከላይ በሙስና የተቀመጠት በዝባዦች ለጊዜው ምንም ላይጎዱ ይችላሉ ። ሆኖም በዚህ እቀባ ምክንያት የሚጎዱት ምስኪን ካህናትና ዲያቆናት መሆናቸውም ይታ ቃል ። እናም ምእመናንና የንስሐ ልጆች የሆናችሁ የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች በሙሉ አባቶችና ወንድሞችን በመደጎም ውጤታማ ሥራ እንድንሠራ ይሁን ።

3ኛ፦ እነሱ ከላይ እስከታች በዘረኝነት ተተብትበው እና ተጠምቀው ሳለ እኛ ለምን ብለን መጠየቅ ስንጀምር ለማሸማቀቅ ዘረኞች ፣ ጠባቦች ፣ ትምክህተኞች በሚሉ ራሳቸው በፈጠሩልን የማሸማቀቂያ ገመድ አንጠለፍም ። ዘረኝነትን መቃወም ፖለቲከኛም አያስብልም ። አለቀ አራት ነጥብ ።

አሁን በኢትዮጵያም ሆነ በቅድስት ቤተክርስቲያን እየተፈጸመ ስላለው ግፍና መከራ ለመናገር እውነት እውነት እላችኋለሁ ሰባኪም ፣ ፖለቲከኛም ፣ አትሌትም ፣ ሆነ ግንበኛ ፣ መሆንን አይጠይቅም ። ” ጉዳዩን ለመቃወም ሰው መሆን ብቻውን በቂ ነው ” ።

ጉዞው እስከ ቀራንዮ ነው ፣ ድል ለእምዬ ተዋህዶ !!! ወድቀት ለዘረኞች ።

ይህንንም ራሴው ዘመድኩን በቀለ ጻፍኩት ።ለማንኛውም በነጻነት እንወያይ ፤ ከስድብና ከዛቻ በራቀ መልኩ እንነጋገር ። +251911608054 የቫይበር ስልኬ ነው ። በተለይ ይህን መልእክቴን በተመለከተ ደግሞComent መስጠትናShare ማድረግ በእጅጉ ይበረታተል ።

ሻሎም ! ሰላም !

ዘመድኩን በቀለ ነኝ
መስከረም/2/2009 ዓም

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s