ህወሀት የጎንደርን ታጣቂ ትጥቅ ለማስፈታት ከፍተኛ ገንዘብ መመደቡ ተሰማ

1098271_997344230319781_4862823142964158231_n

በተነሳው ህዝባዊ አመጽ አጣብቅኝ ውስጥ የገባ ህውሓት ህዝባዊ አመጹን ለማብረድ የቻለውን እያደረገ ይገኛል። በመላው አገሪቱ አመጹን ለማብረድ የሃይማኖት አባቶች ከመላክ እስከ ቤት ለቤት አሰሳ ላይ ተሰማርቶ ይገኛል። የጨነቀው ህውሓት በጎንደር እና አከባቢዋ ለታጠቁ በሙሉ መሳርያቸው በሃይል ለምጠቅ ቢሞክርም አልተሳካለትም። አሁን የመጨረሻ የመሳርያ ማስፈታት ስልቱ በገንዘብ ሆኖዋል።
.
በጎንደር እና አከባቢዋ ለታጠቁት በሙሉ ከፍተኛ ገንዘብ በማቅረብ መሳርያን የመግዛት ስልት ይዞ መንቀሳቀስ ጀምረዋል። በጎንደር በተነሳ አመጽ ምክንያት የአንድ መሳርያ ዋጋ ከአስራ አምስት ሺ እስከ ሃያ አምስት ሺ ደርሶ ነበር፣ ይህንን የተመለከተ ህውሓት አሁን መሳርያ ላለው ሰው በሙሉ እስከ ስድሳ ሺ በመክፈል ትጥቅን የማስፈታት ስልት ጀምረዋል። ህውሓት አመጹን ለማብረድ እና ትጥቅን ለማስፈታት በየ ቦታው ገንዘብ በማፍሰስ ላይ ነው።
.
ኢፈርት የትግራይ ህዝብ ነው ስትል የነበርከው የህውሓት ደጋፊ የትግራይ ህዝብ ሳያቅ ህውሓቶች እንደለመዱት ለራሳቸው የስልጣን ህልውና ሲሉ ገንዘቡን እየዘረፉት ነው። ህውሓቶች በኢፈርት ገንዘብ ሰው ያስገድላሉ ዊስኪ ይጠጣሉ ዘመዶቻቸውን ውጭ አገር ድረስ ልከው ያስተምራሉ ያሳክማሉ እናንተ የህውሓት ደጋፊዎች ደግሞ ኢፈርት የትግራይ ህዝብ ነው ትላላቹ። ህውሓቶች በራሳቸው ጊዜ ነገር ቆስቁሰው ነገሩን የሚያበርዱት ገንዘብ በመበተን ነው። የጎንደር እና አከባቢዋ ህዝብ ግን አሁንም ቢሆን ከገንዘቡ ይልቅ ለመብቱ እየተዋደቀ ይገኛል። ድል ለሰፊው ህዝብ!

 

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s