ፍትህን እና እዉነትን በእግራችሁ ለመርገጥ አትንጠራወዙ ! (ከመኢአድ የተሰጠ መግለጫ)

imgres

የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አንድ ብቻ ነዉ::እሱዉም በአቶ ማሙሸት አማረ ነዉ የሚመራዉ:: በ2006 ዓም በተደረገዉ ጠቅላላ ጉባኤ ከ483 ጠቅላላ ጉባኤ ተሰብሳቢዎች ዉስጥ በ477 ጠቅላላ ጉባኤ ተሳታፊዎች የተመረጠዉ የአቶ ማሙሸት አመራር ነዉ::ሆኖም ወያኔ በምርጫ ቦታ እንኳን ተገኝቶ የማያዉቀዉን ተላላኪዎቿን አቶ አበባዉን እና ዶ/ር በዛብህን መርጣ የመኢአድን ቢሮዉን አስረክባቸዋለች::ከዚያ ጊዜ ጀምሮ መኢአድ በአቶ ማሙሸት እየተመራ ፍትህን እና እዉነትን የማስከበር ተጋድሎ ላይ ነዉ:: የመኢአድ ቢሮ ሲጀምር የመኢአድ የትግል ሜዳ አይደለም እና ቢሮዉን ነቅለዉ መዉሰድ ሲፈልጉ ማቃጠል ይችላሉ::መኢአድ የሚታገለዉ የወያኔን ኢፍትሃዊ ህግ እና ኢ ፍትሃዊ የህግ አፈጻጸምን ነዉና ወያኔ በህገ ወጥ መንገድ ህግ ነዉ እያለች ወያኔ እያነሳች የምትጭንብንን ነገር ሁሉ አንቀበልም:: ስለሆነም መኢአድ የሚከተሉትን እርምጃዎች በመዉስድ የወያኔን ኢፍትሃዊ እና ኢ-ዲሞክራሲያዊ አካሄድ አምርሮ ይቃወማል:-

-የወያኔን ምርጫ ቦርድ በወያኔ ፍርድቤት ከሶ መፈናፈኛ ቢያሳጣዉም የወያኔ ካንካሮ ፍርድቤት እንደተለመደዉ ፍትህን ሽሮታል::ቢሆንም መኢአድ ትግሉን ቀጥሏል:: እናም መኢአድ ተቃዉሞዉን እና ለፍትህ ብሎም ለእዉነት የሚያደርገዉ ተጋድሎ ቀጥሎ የወያኔን ፍርድ ቤት ዉሳኔ እንደማይቀበለዉ መግለጫ ሰጥቷል::
-መኢአድ የተመሰረተዉ በወያኔ ፈቃድ ስላልሆነ መኢአድ ህልዉናዉን ይዞ እንደሚቀጥል እና የኢትዮጵያ ህዝብ ነጻ እስከሚወጣ እንደሚታገል ግልጽ አድርጓል
-መኢአድ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያደርገዉን የዲሞክራሲ ተጋድሎ እያበረታታ እና እየደገፍ በተግባር ከህዝብ ጋር የቆመ እና በህዝብ ዉስጥ የሚመላለስ ድርጅት መሆኑን አስመስክሯል

ለዚህ ዉሳኔዉም መኢአድ ከፍተኛ ዋጋ እየከፈለበት ነዉ:: በርካታ አመራሮቹ ታስረዋል: በቅሊንጦ ተቃጥለዋል: ተደብድበዋል: አሁን ድረስ የመኢአድ አባላት በመላ ሀገሪቱ ቤታቸዉ በከፍተኛ ከበባ ዉስጥ ነዉ:: በኢትዮጵያ እስር በቶች ዉስጥ ካሉ የማንኛዉም ፓርቲ ታሳሪዎች ቁጥር በላይ የሚበዛዉ የመኢአድ ታሳሪ ነዉ:: ወያኔም ሀገሪቱ ኮሽ ባለች ቁጥር : ምርጫ በመጣ ቁጥር: ህዝባዊ አመጽ በተቀሰቀሰ ቁጥር የሚበረግገዉ እና ለማሰር ሽህ እና ሽህ ሰራዊቱን እና ፖሊስ ሀይሉን የሚያሰማራዉ በመኢአድ አመራሮች እና አባላት ላይ ነዉ:: ወያኔ እዉነት አለዉ::ማን ጀግና እንደሆነ እና ማን ሞት ፊት በጀግንነት እንደሚቆም ጠንቅቆ ያዉቃል::ማን ለፍትህ ለመሞት እንደወሰነ እና ለኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነት እየዘመረ በታላቅ ተድጋድሎ እንደሚሞት ጠንቅቆ ያዉቃል::

እናም መኢአድ ለእዉነት እና ለፍትህ እስከ መጨረሻዉ የሚሞት ድርጅት መሆኑን ሁሉም ይወቅ:: አንዳንድ በነፈሰበት የሚነፍሱ ሰዎች እንደሚሉት ወያኔ ተቀበል የሚለዉን ሁሉ የሚቀበል ድርጅት አይደለም:: መኢአድ በደም እና በአላማ ተላቁጦ የተፈጠረ ድርጅት ነዉ:: መኢአድ በወጀብ እና በመከራ መሃከል ማለፍ የለመደ: በደም ታሪክ ከሚጽፉ አባቶች አብራክ በተወለዱ ልጆች በጥልቅ መሰረት ላይ የቆመ ድርጅት ነዉ::

ጠላትም ወዳጅም ይሄንኑ ይወቅ ! የፍትህ ህሊና የሌላችሁ : የባንዳ ልጆች እና በጥላቻ የተሞላችሁ አንዳንድ ወገኖች በመኢአድ መንገድ ላይ መቆማችሁን አቁሙ:: ፍትህን እና እዉነትን በእግራችሁ ለመርገጥ አትንጠራወዙ !
መኢአድ አሸናፊ ድርጅት ነዉ !
አንዲት ኢትዮጵያ ! አንድ ህዝብ ! አንድ ሀገር !

ኢትዮጵያን እግዚአብሄር ይባርካት

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s