ህወሀት ኢአደግ ለድርድር ፈቃደኛ አለመሆኑን ገለጸ

መንግስት በውጭ ሀገር ከሚገኙ የተቃዋሚ ፖለቲካ ኃይሎች ጋር ለመደራደር እንደማይፈልግ ተሰማ፡፡ ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ሁኔታ ተከትሎ አሜሪካ እና ሌሎች ለጋሽ ሀገራት የተለያዩ ሀሳቦችን በማንሸራሸር ላይ ሲሆኑ፣ እንደ አማራጭ እየቀረቡ ካሉ ሀሳቦች መካከል አንዱ ከተቃዋሚ ኃይሎች ጋር የሚደረግ ድርድር መሆኑን ምንጮች ጠቅሰዋል፡፡ ድርድሩም በውጭ ያሉ ተቃዋሚ ኃይሎችን እንዲያካትት ሃሳብ ቢቀርብም፣ ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል ግን አሻፈረኝ ባይነት መኖሩ ተሰምቷል፡፡
መንግስት በውጭ ሀገር ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተቃዋሚ ኃይሎች ጋር እንዲደራደር የቀረበለትን ሀሳብ ተቀብሎ እንደነበር የገለጹት የመረጃ ምንጮች፣ ከቆይታዎች በኋላ ግን ከየትኛውም የውጭ ኃይል ጋር መነጋገር እንደማይፈልግ መናገሩን መረጃዎቹ ገልጸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ባለፈው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉባኤ ላይ ‹‹ከአንዳንድ ሀገራት ጋር ጥሩ ወዳጅነት አለን፡፡ ግን ጽንፈኞች በሀገራቸው ተቀምጠው የማሸበር ስራ እንዲሰሩ ፈቅደውላቸዋል፡፡›› በማለት በውጭ የሚገኙ የተቃዋሚ ኃይሎችን በአሸባሪነት ፈርጀዋል፡፡ በዚህም ከተቃዋሚ ኃይሎች ጋር ለመደራደር መንግስታቸው ፈቃደኛ አለመሆኑን አንጸባርቃዋል፡፡
ኤርትራ ከመሸገው ተቃዋሚ ኃይል ስያሜ በመዋስ እና ‹‹አርበኞች ግንባር›› የተሰኘ ፈጠራ በመፍጠር ከሊቀ መንበሩ ጋር ሰለም መፍጠሩን ተናግሮ የነበረው ገዥው ፓርቲ፣ እንዲህ ዓይነቱን ዜና የሰራው በምዕራባውን በኩል ከተቃዋሚዎች ጋር እንዲደራደር የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ ለማድረግ እንዲሁም በራሴ መንገድ መሔድ እችላለሁ የሚለውን ትምክህቱን ለማሳየት እንደሆነ ታዛቢዎች ገልጸዋል፡፡
እንደ ምንጮች ገለጻ ከሆነ፣ አሜሪካም ሆነች እንግሊዝ መቀመጫቸውን በውጭ ካደረጉ ተቃዋሚ ኃይሎች ጋር የሚደረግ ውይይት የሀገሪቱን ውጥረት ሊያረግበው ይችላል የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል፡፡ በተለይ አሜሪካ በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ትኩረት ሰጥታ እየተከታተለች እንደምትገኝ የገለጸው ይኸው የመረጃ ምንጭ፣ መንግስት በውጭ ሀገር ከሚገኙ ኃይሎች ጋር ከመደራደር አልፎ ስልጣን እስከማጋራት እንዲደርስ ጭምር እንደምትሰራ መረጃው አክሎ ገልጿል፡፡ በውጭ ከሚገኙ የተቃዋሚ ኃይሎች ጋር ላለመደራደር አሻፈረኝ ያለውን የህወሓት መንግስት ግትር አቋም ማስቀየር አሜሪካ ያቀደችው ሌላኛው የቤት ስራ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ሞት ለወያኔ ድል ለሰፊው ህዝብ

hailemariam-liar,,,,,,,,

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s