ከ30 በላይ ወታደሮች የታጠቁትን ዘመናዊ መሳሪያ ይዘው ህዝባዊ ተጋድሎውን ለመቀላቀል ጫካ መግባታቸው ታወቀ

ጎጃም መተከል በሚገኘው 23/45ኛው ወታደራዊ ካምፕ ይኖሩ የነበሩ ከ30 በላይ ወታደሮች የታጠቁትን ዘመናዊ መሳሪያ ይዘው ህዝባዊ ተጋድሎውን ለመቀላቀል ጫካ ገብተዋል። የመተከሉ 23/45ኛው ወታደራዊ ካምፕ ማለት በአማራ ተጋድሎ ወቅት ወጣቶች የተገደሉበት፤ አካለ ጎደሎ የሆኑበትና በስቃይ ርሃብና ጥም ውስጥ ደንጋይ እንዲፈልጡ ሲደረግብት የነበረ አካባቢ ነው። ወታደሮች ጫካ የገቡት ሌሊት ላይ የመሳሪያ መጋዘን በመስበር ከውስጥ የነበረውን በትንሹ 10 መትረጌየስና መሰል ዘመናዊ መሳሪያዎችን በመያዝ ነው።
በዚህ የተነሳም መተከል ከፍተኛ የሆነ ፍለጋ ተጀምሯል።ፓትሮል በየጫውካ ተጀምሯል። የወያኔ ደህንነቶችና ጀሌዎች እስከ ምሽቱ 2:30 ድረስ በግልገል በለስ ዞን አስተዳደር አዳራሽ ስብሰባ ላይ ነበሩ። ከወታደሮቹ በተጨማሪ በአማራ እና ኦሮሞ ላይ ወያኔ እየወሰደው ባለው ግድያ ሲበሳጩ ከነበሩ ወጣቶች መካከል ጥቂቶቹ ዛሬ ህዝባዊ ተጋድሎውን ተቀላቅለዋል።
በሌላ በኩል እዚያው ጎጃም ሸርቆሌ አካባቢ ህዝብ ሊገድሉ የሄዱ 16 የወያኔ ወታደሮች ላይ ህዝቡ ራስን የመከላከል እርምጃ ወስዶባቸዋል። ሸርቆሌ አካባቢ የ12ኛ ክፍለ ጦር መገኛ ነው።
ይህ ጎጃም መተከል የሆነው ለሌሎች አካባቢ ወታደሮችም ትልቅ ትርጉም አለው። ዛሬ ላይ ወታደር ሆኖ ከህዝብ ጎን ለመቆም ብቸኛው ምርጫ የኢትዮጵያን ጫካዎች መቀላቀል ወይም የውስጥ አርበኛ መሆን ነው።

04356-barefoot2btplf2bsoldiers2b-2bethiopia

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s