ህዝብን ታግሎ ያሸነፈ ሀይል የለም፡፡ /ወይንሸት ሞላ/

14570501_682571641911947_6439070365969092821_n14495392_10154489616709373_6800522450712614320_n

የአምባገነኖች መገለጫ ባህሪ የሆነው አፋኝነት በኢትዬጵያም ላለፉት 25 አመታት ፖለቲከኞችንና ጋዜጠኞችን በማሰርና በማሰደድ የህዝቡን ፖለቲካ በማቀጨጭ እንዲሁም የነሱን የስልጣን ጊዜ በማስረዘም እዚህ ደርሰዋል፡፡ በኢትዬጵያ በሺዎች የሚቆጠሩ ፖለቲከኞች፣ጋዜጠኞችና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በተለያዩ እስር ቤቶች የሚገኙ ሲሆን ዛሬ እነሱ የጀመሩት የነፃነት ትግል ተቀጣጥሎ ትግሉ የህዝብ ሆኗል፡፡ በተለያየ ጊዜ የህትመት ሚድያዎችን ዘግቶ፣ ፓርቲዎችን አፍርሶ፤ ታጋዬችን አስሮና ገሎ እድሜውን ማስረዘም የቻለው ገዥው መንግስት በማህበራዊ ድረገፅ የመጣበትን አጣብቂኝ ግን ማለፍ አልቻለም፡፡ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ማህበራዊ ድረገፅ በኢትዬጵያ የወጣቱ ድምፅ ሆኗል፡፡ ይህ ገዥው መንግስትን ያስደነገጠውና ለስልጣኑ ስጋት የሆነበት ማህበራዊ ድረገፅ በተለያዩ መንገዶች ለህዝቡ የተሳሳተ መረጃ በመስጠት ተቀባይነት ለማሳጣት ቢሞክርም ህዝቡ የሰለቸውን ውሸት ከማዳመጥ የዲሞክራሲ ተምሳሌት በሆነው ማህበራዊ ድረገፅ መረጃዎችን መስጠትና መቀመል ከጀመረ አመታት አልፈውታል፡፡ አሁን እዚህ ደረጃ በደረሰው የነፃነት ትግል ጉልህ አስተዋፅኦ ያለው ማህበራዊ ድረገፅ ስጋት የሆነበት ገዥው መንግስት የሚደርሱበትን ተቃውሞ በማፈን ከዚህ በፊት ይሄድበት በነበረው መንገድ የህዝብን ድምፅ ለማፈን ዛሬም በአዲስ አበባ እና በአንዳንድ ከተሞች የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጧል፡፡ ይህ አፈና ገዥው መንግስት ይመጣብኛል ብሎ የሚያስበውን ማዕበል ለመሸሽ ሲሆን እንደከዚህ ቀደሙ ይሳካለታል ብየ ግን አላስብም፡፡ ምክንያቱም አሁን ትግሉ የህዝቡ ሆኗል፡፡ ጥቂቶች የጀመሩት የነፃነት ትግል ዛሬ ፍሬ አፍርቶ በድፍን ኢትዬጵያ ሁሉም የነፃነት ታጋይ ሆኗል፡፡ ይህን የህዝብ ትግል መግታት ማሰብ በራሱ ቅዠት ነው፡፡ ጥይትንና እስርን የማይፈሩ ወጣቶች አሁን ተፈጥረዋል፡፡ ወገኑ ፊቱ ላይ የተገደለ ወጣት አይደለም ኢንተርኔት በመዝጋት በጥይትም ወደቤቱ መመለስ እንደማይቻል እሩቅ ሳንሄድ የዚህ 3 ቀን ተሞክሮ ማየት በቂ ነው፡፡ ሌላው እና ትልቁ ነገር ሁሉም ኢትዬጵያዊ የቆመበትን መመርመር ያለበት ወሳኝ ጊዜ ነው፡፡ ህዝብን ታግሎ ያሸነፈ ሀይል የለም፡፡ ይህን በመገንዘብ ለገዢው መንግስት ስልጣን ማስረዘምያነት እራሳችሁን ከማዋል፤ ከህዝብ ጋር ቆማችሁ እራሳችሁን ነፃ የምታወጡበት ጊዜ አሁን ነው፡፡ ይህን የምትወስኑበት ጊዜም አልረፈደም፡፡ የገዢው መንግስት አመራሮች ቢችሉ በጥይት እና በእስር ከመጣባቸው ተቃውሞ ለማምለጥ ይሞክሩ ይሆናል፤ ካልቻሉ ደግሞ የዘረፉትን ይዘው መሰደድ የመጨረሻው አማራጫቸው ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ግን የሚሰራው ምናልባትም ለጥቂቶች ነው፡፡ ነገር ግን የስርዓቱ እድሜ ማራዘምያ ለሆኑት የወር ደሞዛቸው ቤተሰባቸውን በአግባቡ እንኳ መመገብ የተሳናቸው የስርዓቱ አገልጋዬች የቆሙበትን ለመመርመር እና ለመወሰን አሁንም ጊዜው አልረፈደም፡፡ የአምባገነኖች መጠቀምያ መሆን እና ህዝብ ላይ መተኮስ ያስከተለውን መዘዝ ከተለያዩ ሀገሮች ተሞክሮ መውሰድ ይቻላል፡፡

14495392_10154489616709373_6800522450712614320_n14570501_682571641911947_6439070365969092821_n

ሁሉም የቆመበትን ይመርምር፤ ድል በጥቂቶች ለተጨቆነው የኢትዬጵያ ህዝብ!!!

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s