በትላንትናው እለት በምእራብ አርሲ በዶዶላ ወረዳ በሂራሮ ከተማ የአጋዚ ጦር በጭካኔ 23 ሰው መግደላቸውን የራዲዮ ዳንዲ ሃቃ ምንጮች ከስፍራው ዘገቡ ።

የአጋዚ ጦር ይህንን እርምጃ የወሰዱት መንገድ ላይ ያገኙትን ሁሉ ያለ ምንም ርህራሄ በመተኮስ ነው ሲል የራዲዮ ዳንዲ ሃቃ ምንጮች አያይዘው ዘግበዋል ከነዚህ መስዋእት ከሆኑት መካከል አባት እና ልጅ የሚገኙበት ሲሆን በዛሬው እለት 18 የሚሆኑት የቀብር ስርአታቸው እንደተፈፀመ የራዲዮ ዳንዲ ሃቃ ምንጮች ዘግበዋል ።

በአካባቢው ያለው ውጥረት እጅግ አስፈሪ እና ከባድ ከመሆኑ የተነሳ በየማሳው የተገደሉትን ሰዎች ሬሳ ለማንሳት እንኩዋን እንደልተቻለ የራዳሃ ምንጮቻችን አያይዘው ዘግበዋል ።

የሄሬሮ ከተማ በአዳባ ከተማ እና በዶዶላ ከተማ ማሀል የምትገኝ ከተማ ናት የሙዋቾቹ ስም እንደደረሰን የምናሳውቅ ይሆናል
ከአላህ ጋ የልጆቻችንን ደም እንበቀላለን ።

በተያያዘ ዜና በአርሲ ዲዳአ በሲዲቃ ከተማ ከትላንትናው እለት ጀምሮ እስካአሁኑ ሳአት ድረስ አመፁ እንደቀጠለ ይገኛል የሲዲቃ ከተማ እና ገጠር አካባቢው ነፃነታቸውን አዉጀዋል በሲዲቃ ከተማ ስር 7 ወረዳዎች ይገኛሉ በከተማው የሚገኙትን የቀበሌ ፅህፈት ቤቶች እንዳለ ቄሮዎቹ አቃጥለዋቸዋል።

የሲዲቃ ከተማው ቄሮዎች ከ50 በላይ ታጣቂዎች ላይ ትጥቅ አስፈትተዋል ። መሳሪያ ለህዝቡ አናስረከብም ያሉትን ታጣቂዎች ደግሞ ቤታቸውን ሙሉ በሙሉ አቃጥለውባቸዋል ሲሉ የራዲዮ ዳንዲ ሃቃ ምንጮች ከስፍራው ዘግበዋል ።

የሀገር ሽማግሌዎች የታጣቂዎችን ቤት አታቃጥሉ እኛ ተቀብለን እንሰጣቹዋለን በማለት ከሲዲቃ ደካ እስከ ሲቢ ከሮቤ እስከ ማሰራንጃ አቡ ያሉት ባጠቃላይ በሀገር ሽማግሌዎች እየተዳደሩ ይገኛሉ ሲሉ የራዲዮ ዳንዲ ሃቃ ምንጮች ዘግበዋል ።

የአጋዚን ጦር ከአካባቢያቸው ሙሉ በሙሉ አባረዋል አገልግሎት የሚባል ቢሮ በመስበር ብር ወስደው ጥይት ለመግዛት ተስማምተዋል ቢሆንም የያዙት መሳሪያ ሚንቶፍ ስለሆን የእሱን ጥይት ማግኘት አልተቻለም በማለት ለራዳሃ ገልፀዋል ።

የሲዲቂ ከተማ ድል እንዲቀጥል በአካባቢው ያሉ ሁሉ ትግሉን አፋፍመው እንዲቀጥሉ ሲሉ መልክታቸውን አሳተላልፈዋል።

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s