የአፋሯ ድምጻዊት ታሰረች በአፋር ተወዳጅ የሆነችውና በትግል ዘፈኖቿ የምትታወቀው ድምጻዊት መፈራ ሞሀመድ ላሌ መታሰሯ ታውቋል።

የአፋሯ ድምጻዊት ታሰረች በአፋር ተወዳጅ የሆነችውና በትግል ዘፈኖቿ የምትታወቀው ድምጻዊት መፈራ ሞሀመድ ላሌ መታሰሯ ታውቋል። ሰሞኑን በአፋር ሊካሄድ የታቀደውንና በህዝቡ ተቃውሞ የከሸፈውን ሰልፍ ተከትሎ ነው ድምጻዊቷና ሌሎች 10ሰዎች የታሰሩት። በህወሀት የታቀደው ሰልፍ ለህወሀት መንግስት ድጋፍ የሚያሳይ፡ የጅጅጋውን ዓይነት የአማራውንና የኦሮሞውን እምቢተኝነት እንዲቃወም ታቅዶ የነበረ ቢሆንም ድምጻዊቷ በግልጽ ”ህዝብ እየገደለ ያለው መንግስት እንጂ፡ ህዝብ መንግስትን አልገደልም።” በማለት በማስተባበር ህዝቡ ሰብሰባውን ረግጦ ኣንዲወጣ አድርጋለች። ሰልፉም ሳይካሄድ ቀርቷል። ”ተነሱ ታጠቁ” በተሰኘው የአፋርኛ ዘፈኗ የምትታወቀው ድምጻዊት መፈራ በአሁኑ ሰዓት በአሳይታ በእስር ላይ ትገኛለች። የአፋር ወጣቶች ድምጻዊቷ ካልተፈታች ትምህርት አንማርም፡ እርምጃ እንወስዳለን በሚል ተቃውሞ ሊያሰሙመዘጋጀታቸውን ለማወቅ ተችሏል። ‘የአፋሯ ”ኮ/ል ደመቀ” ልትሆን ትችላለች’ ብሎኛል የአፋር የሰብዓዊ መብት ሰብሳቢ ጋአስ መሀመድ።
ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን

 
Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s