የአጋዚ ጦር እየተበታተነ ነው ተባለ

በቅርቡ አጋዚ ክፍለጦርን ለቀው የወጡ ወታደሮች ለኢሳት እንደገለጹት ጦሩ ከምንጊዜው በላይ እየተበታተነ ይገኛል። አብዛኛው የሰራዊቱ አባል በክፍለጦሩ ውስጥ የሚታየውን ፍጹም ዘረኝነት በመጥላት እየጠፋ ፣ ክፍለጦሩን አመናምኖታል። በአሁኑ ሰአት 2 ሺ የሚሆኑ አባላት ብቻ የቀሩ ሲሆን፣ ከ2007 ዓም ጀምሮ እስካሁን ወደ 3 ሺ የሚደርሱ የአጋዚ ወታደሮች ጥለው ጠፍተዋል። በተለይ ጦሩ ሶማሊያ ገብቶ ከወጣ በሁዋላ አብዛኛው የሰራዊት አባላት አጋጣሚውን ተጠቅመው ጥለው ጠፍተዋል። በእያንዳንዱ ቲም ውስጥ ቀደም ብሎ 10 ወታደሮች የነበሩ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰአት 3 ብቻ ይገኛሉ።
አብዛኞቹ የአጋዚ ጦር አባላት በአብዛኛው በኦሮምያ ሻሸመኔ አካባቢ እንደሚገኙ ተናግረዋል። የአጋዚ ጦር አባላት ቁጥር መመናመኑን ተከትሎ ከአጋዚ ጦር ውጭ ያሉ ወታደሮች እንዲመደቡ መደረጉንም ገልዋጸል። የአጋዚ ጦር አባላት ሁኔታዎች ቢመቻችላቸው ሁሉም ከሰራዊቱ ለመልቀቅ ፈቀዳኛ ናቸው የሚሉት አባላቱ፣ በአሁኑ ጊዜ አጋጣሚውን እየፈለገ የሚወጣውን ወታደር ለመተካት አዲስ ምልምል ወታደሮችን ማግኘት አልተቻለም ይላሉ።
በሶማሊያ በአጋዚ ጦር አባላት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱንም ወታደሮቹ ተናግረዋል። ሶማሊያ ገብተው ከፍተኛ መስዋትነት ቢከፍሉም፣ በመልሱ ምንም ጥቅም አለማግኘታቸውን ተናግረዋል። ከዚህም በላይ ከሻለቃ በላይ ያሉት አዛዦች ከአንድ ብሄር የተውጣጡ በመሆናቸውና ትእዛዝ የሚሰጡትም እነሱ በመሆናቸው፣ ተራው ወታደር ሊቃወም ቢሞክር በቀጥታ እርምጃ ይወሰድበታል ሲሉ ኢሳት በቡድን ያነጋገራቸው አባላቱ ተናግረዋል።

14495381_727547754050198_1341726531349737107_n

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s