የአውሮፓ ሕብረት የፖለቲካ መሪዎችንና ታዋቂ ሰዎችን ማነጋገር ጀመረ

ዛሬ የአውሮፓ ሕብረት በብራስልስ ባደረገው ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያውያኖችን ጋብዞ አነጋገረ። ከተጋባዦቹ መካከል ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ ፕ/ር መረራ ጉዲና እና አትሌት ሌሊሳ ፈይሳ ይገኙበታል።

በስብሰባው ላይ አትሌት ሌሊሳ ፈይሳ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት አስመልክቶ ንግግር ማድረጉን ለኢትዮጵያ ዛሬ የደረሰው ዘገባ ጠቁሟል። ሁለቱም ፕሮፌሠሮች በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ንግግር ማድረጋቸውንም ለመረዳት ችለናል።

የአውሮፓ ሕብረት የኢትዮጵያውያን ጉዳይ በየጊዜው ክትትል የሚያደርግ ሲሆን፣ ሁኔታውም እያሳሰበው እንደሚገኝ በተደጋጋሚ ገልጿል። በአሁኑ ጊዜ ደግሞ ይበልጥ ትኩረት ሰጥቶ በመከታተል ላይ ይገኛል።

በዚህ ጉዳይ ላይ የኢትዮጵያውያን ሁኔታ በተነሳ ቁጥር ይበልጥ ተነሳሽነት ያላቸው ወ/ሮ አና ጎሜዝ (ሃና ጎበዜ) የሚታወሱ ናቸው።

ይህንኑ ተከትሎ ነገ ሐሙስ (November 10, 2016) በአውሮፓ ሕብረት ጽሕፈት ቤት የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚደረግ ታውቋል። በዚሁ ሰልፍ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጥ የተጋበዘው አትሌት ሌሊሳ ፈይሳ ከወገኖቹ ጋር ድምፁን ለማሰማት ይገኛል። በዚሁ ሰልፍ ላይ በሌሎች የአውሮፓ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያኖችም መሳተፍ እንዲችሉ ጥሪ ቀርቧል።

15032252_1274646579254141_5843083535127258692_n14956363_675774532577476_7196150966059779186_n

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s