ትጥቅ ለማስፈታት ወደ አማራ ክልል ሰሜን ጎንደር የተንቀሳቀሰው የመንግስት ሃይል ከህዝብና ራሳቸውን የነጻነት ሃይሎች ከሚሉ ታጣቂዎች ከፍተኛ ጥቃት ተሰነዘረበት

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ተከትሎ ትጥቅ ለማስፈታት ወደ አማራ ክልል በተለይም ሰሜን ጎንደር የተንቀሳቀሰው የመንግስት ሃይል ከህዝብና ራሳቸውን የነጻነት ሃይሎች ከሚሉ ታጣቂዎች ከፍተኛ አጸፋ እንደተሰነዘረባቸው መሆኑን የአካባቢው ምንጮች ገልጹ። በወገራ ወረዳ እንቃሽ አካባቢ በተካሄደው ጦርነት 30 ታጣቂዎችና ወታደሮች ከነመሳሪያቸው መማረካቸውን የነጻነት ሃይሎች ተናግረዋል። ተጨማሪ 3 ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ወደ አካባቢው ተጉዘዋል።
በተለይም አንቃሽ በተባለ ቦታ ላይ ሽፍቶችን እወጋለሁ በሚል የተንቀሳቀሰው የመከካከያና የጸረ-ሽምቅ ሃይል ከህዝብና ከነጻነት ሃይሎች ጥቃት እንደተሰነዘረበት ተመልክቷል።
ለኢሳት ረቡዕ በደረሰው መረጃ መሰረት ንጋት ላይ በተካሄደ ግጭት ሶስት የመከላከያ አባላትና 2 የሽምቅ ግብረሃይል አባላት ተገድለዋል።
በነጻነት ሃይሎች በተሰነዘረው የአጸፋ ጥቃት የቆሰሉት ወታደሮችና የጸረሽብር ግብረ ሃይል አባላት ደግሞ ወደ ጎንደር ሆስፒታል መወሰዳቸውን ከስፍራው ለኢሳት የደረሰው ዜና ያስረዳል።
በአካባቢው ነዋሪዎችና በነጻነት ሃይሎች ላይ ስለደረሰው ጉዳት የታወቀ ነገር የለም። ሆኖም በአካባቢው አሁንም ግጭት መቀጠሉ የተሰማ ሲሆን፣ በተጨማሪ በሶስት ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች የተጫኑ ወታደሮች ወደስፍራ መጓጓዛቸውንም መረዳት ተችሏል። ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ በአንቃሽ ውጊያው ቀጥሏል።

14457537_1779246709011447_6947376628893828324_n

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s