በአዉሮፓ የስደተኛዉ ቁጥር ላይ ዕቀባ ማድረጉን አስከትሎ ወደ አገራቸዉ ለሚመለሱት ስደተኞች አስፈላጊዉን እርዳታ እንደሚያደርጉ የአዉሮፓ ሕብረት ገለፀ።

99fe3-images
በምሕፃረ ቃል IOM በመባል ሚታወቀው የአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት እንደገለፀዉ ባለፉት ሁለት ወራት ዉስጥ ሕጋዊነት የሌላቸዉ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞችን ከየመን፤ ከዛምቢያ፤ ከሳዉዝ አፍሪካ፤ ከታንዛኒያ፤ እና ከሳዉዲ አረቢያ በግዳጅ መመለሳቸዉን ገልፆአል።

በአሁኑ ጊዜ ወደ አገራቸዉ እንዲመለሱ የተባሉት እነዚሁ በአዉሮፓ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸዉ ኢትዮጵያዉያኖች ምን ያህል እንደሆኑ አልታወቀም።

ኢትዮጵያዉያኖቹ ህይወታቸዉን አደጋ ላይ ጥለዉ እና በጣም አስቸጋሪ ጉዞ ተጉዘዉ አሁን ያሉበት ቦታ ሲደርሱ ብዙ ተስፋ ሰንቀዉ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ባለዉ ሁኔታ ግን እጅግ ተስፋ የቆረጡ መሆናቸዉና ከአገር ሲወጡም ሰርቼ ከማፈራዉ ሃብት ላይ እከፍላለሁ በማለት የተበደሩትን ገንዘብ እንኳን ሊከፍሉ ሳይችሉ ወደ አገር ተመልሰዉ አዲስ ህይወት መቋቋም በራሱ በጣም አስቸጋሪ እንደሆነ መግለጻቸዉን አያይዞ አለም አቀፉ የስደተኛ ድርጅት (IOM) አስታዉቋል።

ባለፈዉ የኦክቶበር ወር የአዉሮፓ ሕብረት መሪዎች ሕጋዊ ያልሆኑ ስደተኞችን በተመለከተ አንድ ስምምነት ላይ መድረሳቸዉ የሚታወስ ሲሆን፣ ይህንኑ መሠረት አድርጎ በሜዲትራኒያን ባሕር አቋርጠዉ የሚመጡትን ስደተኞች ለማቆም የአዉሮፓ ሕብረት አገራቱ ከአፍሪካ አገራት ጋር የጋራ ንግድ ሥምምነት ማድረጋቸዉም ይህንኑ የስደተኛዉን ጉዞ ለመግታት በማሰብ እንደሆነም ይታወቃል።

ለዚህ ችግር መፍትሔ ተብሎ የተፈረመዉን የአፍሪካና የአዉሮፓ ሕብረት ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ በቅድሚያ በአምስት የአፍሪካ አገራት ላይ እንደሚጀመር አስታዉቆ፣ እነዚህም አገራት ኒጀር፤ ናይጄርያ፤ ማሊ፤ ሴኔጋል፡ እና ኢትዮጵያ ናቸዉ።

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s