በአርማጭሆ የተቀሰቀሰው ጦርነት ቀጥሏል፤ የተጠለፉ የመብራት ኃይል ሠራተኞች እስካሁን አልተመለሱም

በአርማጭሆ የዐማራ ታጋዮች ከሕወሓት ወታደሮች ጋር ሲያደርጉት የዋሉት ጦርነት እስካሁን እንደቀጠለ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ ዛሬ ኅዳር 16 ቀን 2009 ዓ.ም. ጠዋት የዐማራ ታጋዮች ከሕወሓት ወታደሮች ጋር በታች አርማጭሆና በጠገዴ አካባቢዎች የተቀሰቀሰው ጦርነት በከፋኝ የተደራጁ የዐማራ ታጋዮች ድል እንደቀናቸው ተናግረዋል፡፡ ከታጋዮች ጋር የነበረው ግንኙነት ከሰዐት በኋላ በአካባቢው የመገናኛ ኔትወርክ በመቋረጡ ምክንያት የተሟላ ባይሆንም ውጊያው ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ መቀጠሉ ታውቋል፡፡ በአካባቢው በወያኔ የታጠቁ ምንሻዎች የከፋኝን ጦር ተቀላቅለው ከፍተኛ እገዛ እያደረጉ እንደሆነ ያገኘነው መረጃ አመልክቷል፡፡
ታች አርማጭሆ ሳንጃ ላይ የዐማራው ንቅናቄ አመራር የሆኑት የአርበኛ ጎቤ መልኬ ወንድም አቶ ስጦታው መልኬንና የአክስታቸውን ልጅ በቤታቸው ከነመኪናዎቻቸው የሕወሓት ወታደሮች ከበው የሚገኙ ሲሆን ከሕዝብ ጋር ከፍተኛ ፍጥጫ ተፈጥሯል፡፡ በቤታቸው የተከበቡት ወጣቶች በተጠንቀቅ ላይ ቢሆኑም ከሕዝብም ከወያኔ ወታደሮችም የጥይት ተኩስ እንዳልነበር ለማወቅ ችለናል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ ወደ ሳንጃ ኅዳር 14 ቀን 2009 ዓ.ም. ወደ አካባቢው (ሳንጃ) የሔዱ ሦስት የሰሜን ምዕራብ ሪጅን የመብራት ኃይል ሠራተኞች መኪናቸው ተቃጥሎ ግለሰቦቹም መጠለፋቸው የታወቀ ሲሆን እስካሁን ኃላፊነቱን የወሰደ አካል አልተገኘም፡፡ የመብራት ኃይል ሠራተኞቹ የተጠለፉበት አካባቢ ከሳንጃ 24 ኪሎ ሜትር ርቀት ጅንጋር የተባለ ቦታ ሲሆን የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ጌታሰውን ጨምሮ አቶ ይበልጣል ዘውዱ እና ለጊዜው ስሙ ያልታወቀ ሠራተኞች ናቸው ተብሏል፡፡
ከቀኑ 8፡00 አካባቢ ያገኘናቸው የዐማራ ታጋዮች ‹‹የማንነት ጥያቄያችን በወያኔ መንግሥት ተደፋፍኗል፤ የዐማራ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለው በደል ከምንጊዜው በላይ ተጠናክሮ ቀጥሏል፤ ነጻነታችን እስከምናረጋግጥ ድረስ ትግላችን ይቀጥላል።ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ሞት ለወያኔ!!!

 
Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s