በጋምቢያ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የሃገሪቱ ፕሬዚደንት ያህያ ጃሚህ በተቃዋሚ እጩ ተወዳዳሪ ተሸነፉ

 

በጋምቢያ በተካሄደ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ለ22 አመታት በስልጣን የቆዩት የሃገሪቱ ፕሬዚደንት ያህያ ጃሚህ በተቃዋሚ እጩ ተወዳዳሪ ተሸነፉ።

ከ22 አመት በፊት በመፈንቅለ መንግስት ለስልጣን በቅተው የነበሩት የጋምቢያው ፕሬዚደንት ከተፎካካሪያቸው ሰፊ ልዩነት ያለው ድምፅ በማግኘት መሸነፋቸውን የምዕራባዊቷ ሃገር የምርጫ ኮሚሽን ሃላፊ አሊ’ኡ ሞማር ንጃ’ይ ለመገናኛ ብዙሃን ይፋ አድርገዋል።

በፕሬዚደንታዊ ምርጫ ጠንካራ ተፎካካሪ የነበሩት የተቃዋዋሚ ፓርቲ አመራሩ አዳማ ባሮ ከ45 በመቶ በላይ ድምፅ በማግኘት ቀጣዩ የሃገሪቱ ፕሬዚደንት ለመሆን መብቃታቸውን አልጀዚራ የቴለቪዥን ጣቢያ አርብ ዘግቧል።

ምዕራባዊቷ ሃገር ጋምቢያ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1965 ከብሪታኒያ ነጻነቷን ካገኘች በኋላ በሃገሪቱ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ተካሄዶባት የማይታወቅ ሲሆን፣ ለድል የበቁት የተቃዋሚ ፓርቲ አሸናፊ ከፕሬዚደንት ያህያ የእንኳን ደስ አለህ የስልክ መልዕክት እየተጠባበቁ መሆኑን ለጋዜጠኞች ገልጸዋል።

ሃሙስ ብሄራዊ ምርጫው በተካሄደበት ዕለት የሃገሪቱ ፕሬዚደንት የኢንተርኔትና የስልክ ግንኙነት ሙሉ ለሙሉ እንዲቋረጥ አድረገ እንደነበር ቢቢሲ ዘግቧል።

የጋምቢያው ፕሬዚደንት በ22 አመት የስልጣን ቆይታቸው በርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጽመዋል በሚል ከተለያዩ አካላት ተቃውሞ ሲቀርብባቸው የነበረ ሲሆን፣ ቁጥራቸው በትክልል የማይታወቅ የሃገሪቱ ዜጎችና ጋዜጠኞች ለእስር ተዳርገው እንደሚገኙ ታውቋል።

ለስልጣን የበቁት የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው አዳማ ባሮ ወደ ሃገራቸው ተመልሰው በግል ንግድ ስራ ላይ ከመሰማራታቸው በፊት በብሪታኒያ በጥበቃ ስራ ላይ ይሰሩ እንደነበር መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

የ51 አመቱ ተሰናባቹ ፕሬዚደንት የፈጣሪ ፈቃድ ከሆነ ሃገሪቱ ለአንድ ቢሊዮን አመት ሊመሩ እንደሚችሉ በቅርቡ ገልጸው የነበረ ሲሆን፣ ፕሬዚደንቱ ያጋጠማቸው ሽንፈት በብዙዎቹ ዘንድ ያልተጠበቀ እንደነበር ቢቢሲ በሪፖርቱ አመልክቷል።

በጋምቢያ በተካሄዱ አራት ተከታታይ ምርጫዎች አጨቃጫቂ ነው በተባለ ውጤት ለድል በቅተው የነበሩት ፕሬዚደንት ያህያ በአንድ ወቅት ለHIV/AIDS እና መሃንነትን እፈውሳለሁ ብለው በአለም መነጋገሪያ ሆነው እንደነበር የሚታወስ ነው።

ድምፅ የመስጠት ሂደት በሚካሄድበት ዕለት ሃሙስ ፕሬዚደንቱ ለህዝባቸው ባደረጉት ንግግር ለድል መብቃታቸው የማይቀር ጥያቄ ውስጥ የማይገባ እንደሆነ መግልጻቸውን አልጀዚራ በዘገባው አስነብቧል።

የተቃዋሚ ፓርት ለድል መብቃቱን ተከትሎም የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ዝግጅት አድርጋችኋል ተብለው ለእስር ሲዳረጉ የነበሩ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች እንዲሁም ጋዜጠኞች ከእስር ይለቀቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የምርጫ ውጤቱ ከተደረገ በኋላ በሺዎች የሚቆጠሩ የመዲናይቱ ባንጁል ነዋሪዎች አደባባይ በመውጣት ደስታቸውን ሲገልጹ ውለዋል።

ኢሳት (ኅዳር 23 ፥ 2009)

The election defeat may bring Jammeh's 22-year rule to an end [Reuters]

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s