ይህ ትግል የህዝብ ትግል እንደመሆኑ መጠን ማንኛውም ግለሰብ የማንንም ፍላጎትና ይሉኝታ ሳያስፈልገው አቅሙ በሚችለው መንገድ መታገልና ወያኔ የተባለን ዘረኛ ሰው በላ ስርዓት በማስወገድ የዜግነት ድርሻችንን እንወጣ :: በአሁኑ ሰዓት ያለውን ስርዓት ለማስወገድ የጎንዮሽ ንትርኩን ትተን የጋራ የሆነውን ጠላታችን ማስወገድ ግድ ይላል 25 አመት የተሰራን ስራ እንዲሁ በቀላሉ ያለ ስራ ወያኔ ወያኔ እያሉ እንደ ዳዊት ከመድገም ህይወት እየተከፈለበት ያለውን ትግል አቅም በሚፈቅድ መልኩ አስተዋፅው ማበርከት ያስፈልጋል ይህን ስንል የአርበኞች ግንቦት ሰባት አባል ሁኑ ወይም በርሃ ወረዱ አደለም የምንለው በተለያዩ መንገዶች የትጥቅ ትግሉን እርዱ ይህ ማረግ ባትችሉ የትግሉ እንቅፋት አትሁኑ አንድ የሃገራችን ጠላት አለን እሱም ወያኔ ብቻ ነውና አይናችንን አፍጠን ጅሮውችንን አቁመን ወያኔን እንታገል
Advertisements