የሲ.አይ.ኤ ዳይሬክተር ፕሬዝዳንት ትራምፕን አስጠነቀቁ

አዲሱ ተመራጭ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ገና የነጩን ቤተ መንግሥት በር ሳይረግጡ ከአሜሪካው ማዕከላዊ የስለላ ድርጅት (CIA) ዋና ዳይሬክተር ጆን በርናን ምክር አዘል ማስጠንቀቂያ እንደደረሳቸው ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በተለይም ትራምፕ አሜሪካ ከኢራን ጋር የጀመረችውን የኑክሊየር ጉዳይ ድርድር ለማቋረጥ ማሰቡ ‹‹ትልቅ ቅዠትና የቂልነት ጥግ ነው›› ያሉት የሲ.አይ.ኤ ዳይሬክተሩ እንደዚህ አይነቱ ውሳኔ አሜሪካን ዋጋ የሚያስከፍልና ኢራንና መሰሎቿን ኑክሊየርን ለጥፋት እንዲታጠቁት የሚያበረታታ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ ጆን በርናን ዶናልድ ትራምፕ ከሩሲያ ጋር ሊመሰርቱት ያሰቡትን ግንኙነትም እንዲያጤኑት አሳስበዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ ‹‹ለምሳሌ በሶርያ ጉዳይ ከአሜሪካ በተቃራኒው በመቆም የእርስ በርስ ጦርነት እንዲባባስና አምባገነኑ ሥርዓት እንዳይወገድ እንዲሁም አሸባሪዎች ጥፋታቸውን እንዲጨምሩ እያደረገች ካለችው ሩሲያ ጋር የተለየ ወዳጅነት የምንመሠርትበት መሠረት የለንም፡፡ ሩሲያዎች በቻሉት ሁሉ አጋጣሚ ለእነርሱ በቂና የተመቻቸቸ የጦር ሜዳ ሳያዘጋጁ የሚደራደሩ ናቸው ብየም አላምንም›› ባይ ናቸው፡፡

በአጠቃላይ የሲ.አይ.ኤ ዋና ዳይሬክተር ጆን በርናን ለአዲሱ ፕሬዝዳት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ኑክሊየር፣ ከሶሪያ ጦርነት፣ ከሩሲያ አጋርነት፣ ከአአሸባሪዎች እንቅስቃሴና የማጥፋት ዘመቻና አሜሪካ ከሙስሊሙ ዓለም ጋር ስለሚኖራት ግንኙነት እና ስለሌሎችም ጉዳዮች ከምርጫ በፊት ያሳዩትን አቋም እንደገና እንዲያጤኑት ምክርም ማስጠንቀቂያም አዘል መልእክት አስተላፈዋል፡፡

Related image

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s