የዶ/ር መረራ ጉዲናን መታሰር ተከትሎ በርካታ የኦሮሞ ብሄር ተወላጆች እየተያዙ ነው

14956363_675774532577476_7196150966059779186_n

 ኢሳት ዜና :- ከአውሮፓ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ የታሰሩት የደ/ር መረራ ጉዲናን መታሰር ተከትሎ የእሳቸው ደጋፊ ይሆናሉ የተባሉ ወጣቶች እየተለቀሙ በመያዝ ላይ ናቸው።

እስሩ እርሳቸው በተያዙ ማግስት የጀመረ ሲሆን፣ እስከዛሬ ድረስ በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ የኦሮምያ ወረዳዎች እንዲሁም በአምቦና አጎራባች ቀበሌዎች በርካታ ሰዎች ተይዘው ታስረዋል። በተመሳሳይ ዜና በደቡብ ወሎ ሃይቅ ከተማ በርካታ ወጣቶች በአዲሱ ወታደራዊ እዝ አማካኝነት መሰታሰራቸውን ለማወቅ ተችሎአል። እስካሁን በደረሰን መረጃ ከ50 ያላነሱ ወጣቶች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በሌላ በኩል በተለያዩ መስሪያ ቤቶች በዘበኝነት ተቀጥረው ስራ የሚሰሩ የቀድሞ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እንደገና መታዋቂያ እንዲያወጡና እንዲመዘገቡ እየተደረገ ነው። ሰራተኞቹ ከሚሰሩበት መስሪያ ቤት ጋር አዲስ ውል እንዲፈርሙ እየተደረገ ሲሆን፣ በተለይ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚሰሩ ሰራተኞች የጦር መሳሪያ እንዳይዙ ፣ በስራ ወቅትም ወታደሮች ካልሆኑት ጋር ተመድበው እንዲሰሩ መመሪያ ተላልፏል።

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s