የፌደራል ፖሊሶችና ወታደሮች ሃረርን አጨናንቀዋል

 ኢሳት ዜና :- ወኪላችን እንደገለጸው ህዳር 29 የሚከበረውን የብሄር ብሄረሰቦች በአል ምክንያት በማድረግ በከተማው የሚታየው የጸጥታ ቁጥጥር የከፋ መሆኑን ገልጿል።

በርካታ ቁጥር ያላቸው ወታደሮች ወደከተማ የገቡ ሲሆን፣ ለጸጥታ ስጋት ናቸው የተባሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተይዘው ታስረዋል።

ከሃረር ወጣ ብሎ በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች በርካታ የኦሮሞ ወጣቶች ተይዘው ታስረዋል። ከ500 በላይ የሚሆኑ የአማራ እና የሌሎችም አካባቢ ተወላጆች ከተለያዩ አካባቢዎች ተይዘው  በምስራቅ እዝ ወታደራዊ ግቢ ውስጥ መታሰራቸውንም ምንጮቹን ዋቢ በማድረግ ወኪላችን ዘግቧል። የባጃጅ አሽከርካሪዎች በአሉ እስከሚጠናቀቅበት ሰአት ድረስ በዋና ዋና መስመሮች እንዳይሰሩ ታግዷል። ትምህርት ቤቶች ለእንግዶች ማረፊያ በሚል ተዘግተዋል።

ነጋዴዎች ደግሞ ከመዘጋጃ ቤት ከ70 እስከ 100 ብር በሚደርስ ዋጋ የክልሉን ባንዲራና ባለኮከቡን የአገሪቱን ባንዲራ ገዝተው በድርጅቶቻቸው ላይ እንዲሰቅሉ ታዘዋል።

በአሉ በ 1 ቢሊዮን 800 ሚሊዮን ብር በሆነ ወጪ በአፍረጺዮን ኮንስትራክሽን በተገነባው ስታዲየም የሚከበር ሲሆን፣ ከተማዋን የማስዋብና ሌሎችንም ተጓዳኝ ሰራዎች ከህወሃት ጋር በቅርበት የሚሰሩ ድርጅቶች ኮንትራት ወስደው እየሰሩ ነውhorn_map

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s