በድርቅ ጉዳት ደርሶባቸው አስቸኳይ ርብርብ የሚፈልጉ አካባቢዎች መለየታቸውን ተመድ ገለጸ

ኢሳት (ኅዳር 26 ፥ 2009)

በኢትዮጵያ በተከሰተው አዲስ የድርቅ አደጋ አምስት አካባቢዎች አስቸኳይ ርብርብ የሚፈልጉ ሆነው መለየታቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰኞ ይፋ አደረገ።

በርካታ እንስሳት በድርቁ ምክንያት በመሞት ላይ መሆናቸውን የገለጸው ድርጅቱ የደቡብ ኦሮሚያ፣ በደቡብ ኦሞ የሰገን እና ጋሞጎፋ አጎራባች ስፍራዎች እንዲሁም የሶማሊ ክልል አዲስ በተከሰተው የድርቅ አደጋ ቅድሚያ ተኮር ተደርገው አስቸኳይ ርብርብ የሚፈልጉ ተብለው መፈረጃቸውን አመልክቷል።  drought

በሃገሪቱ ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ በመስፋፋት ላይ በመሆኑ በቀጣዮቹ ስድስት ወራቶች የምስራቅ ኦሮሚያ እንዲሁም በደቡብ ክልል የሚገኙ በርካታ ዞኖች በአንደኛ ደረጃ የድርቅ አደጋ ውስጥ ሊካተቱ እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅቱ አሳስቧል።

በመሞት ላይ ያሉ የቤት እንሳሳትን ለመታደግ ብቻ 27 ሚሊዮን ዶላር (ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ) እንደሚያስፈልግ የተገለጸ ሲሆን፣ የተባበሩት መንግስታትና ሌሎች የእርዳታ ድርጅቶች በድርቁ ጉዳት የሚያስፈልገውን ድጋፍ በመመርመር ላይ መሆናቸው ታውቋል።

ከአንድ አመት በፊት በስድስት ክልሎች ተከስቶ የነበረው የድርቅ አደጋ ዕልባት ሳያገኝ አዲስ የድርቅ አደጋ መከሰቱን ችግሩን ያባብሰዋል ተብሎ ተሰግቷል።

በአሁኑ ወቅት 9.7 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ለምግብ ድጋፍ ተጋልጠው የሚገኙ ሲሆን ይህ ቁጥር በቀጣዮቹ ስድስት ወራት ውስጥ ከፍተኛ ጭማሪን ሊያሳይ እንደሚችል አለም አቀፉ የእርዳታ ተቋማት በማሳሰብ ላይ ናቸው።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ “የድርቁ አደጋ ከእጃችን ሳይወጣ ያለንን ልምድ ተጠቅመን በቁጥጥር ስር እናውለዋለን” ሲሉ አዲስ የተከሰተውን የድርቅ አደጋ አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል።

አለም አቀፍ የሰብዓዊ ተቋማት በበኩላቸው ተጨማሪ ጊዜ ሳይወስድ አስቸኳይ የእርዳታ ድጋፍ ስራ መከናወን እንዳለበት ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s