በኢትዮጵያ መንግስት የታቀደው “የ11 በመቶ” አድገት አለመሳካቱ ተገለጸ

በኢትዮጵያ መንግስት የታቀደው “የ11 በመቶ” አድገት አለመሳካቱ ተገለጸ

79356-dimtsachin2b

በ2008 የኢትዮጵያ በጀት አመት የታቀደው የ11 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት አለመሳካቱንና እድገቱ በስምንት በመቶ አካባቢ መመዝገቡን የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ይፋ አደረገ።

በቅርቡም የአለም ባንክ በኢትዮጵያ ባለው የኢኮኖሚ መዋዠቅ ምክንያት የሃገሪቱ ኢኮኖሚ በስድስት በመቶ ብቻ ሊያድግ እንደሚችል መገለጹ ይታወሳል።

ኢትዮጵያ ያጋጠማትን የውጭ ንግድ ገቢ መቀነስና በሃገሪቱ የተከሰተው ህዝባዊ ተቃውሞ በኢኮኖሚ ዕድገቱ መዋዠቅ ምክንያት መሆኑ ታውቋል።

የ2008 በጀት አመትን የኢኮኖሚ ሁኔታ አስመልክቶ ሪፖርቱን ያወጣው የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ባለፈው አመት በስድስት ክልሎች ተከስቶ የነበረው የድርቅ አደጋ ለእድገቱ መቀነስ የራሱን አስተዋጽዖ ማድረጉንም አመልክቷል።

ከጥቂት አመታት በፊት ወደ 45 በመቶ አካባቢ ደርሶ የነበረው የግብርና አጠቃላይ የሃገር ውስጥ ምርት ድርሻ በ2008 በጀት አመት ወደ 36 በመቶ ማሽቆልቆሉን ኮሚሽኑ ለሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን አስረድተዋል።

የመንግስት ባለስልጣናት በሃገሪቱ ተከስቶ ያለውን ህዝባዊ ተቃውሞና የድርቅ አደጋ በኢኮኖሚ ዕድገቱ ላይ ተፅዕኖን አያሳድርም በማለት ሲገልጹ ቆይተዋል።

የሃገሪቱ የግብርና ምርት ገቢ መቀነስ በውጭ ምንዛሪ ክምችት ላይ ከሚያሳድረው ተፅዕኖ በተጨማሪ ኢኮኖሚያዊ ዕድገቱ መቀዛቀዝ እንዲያሳይ ማድረጉን የፋይናንስ ተቋማት የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች አስረድተዋል።

መንግስት በተያዘው በጀት አመት የኢኮኖሚ ዕድገት 12 በመቶ እድገትን ያስመዘግባል ቢልም፣ የአለም ባንክ በበኩሉ ዕድገቱ በስድስት በመቶ አካባቢ ብቻ ሊሆን እንደሚችል በቅርቡ ይፋ ማድረጉን መዘገባችን የሚታወስ ነው።

ሃገሪቱ ያጋጠማትን የውጭ ምንዛሪ የመጠባበቂያ ክምችት እጥረት ተከትሎ የብሄራዊ ባንክ የውጭ ባንኮች በኢትዮጵያ ወኪል ቢሮን እንዲከፍቱ በማድረግ ብድር በማቅረብ ስራ ላይ እንዲሰማሩ ፈቃድ መስጠቱን ለመረዳት ተችሏል።

የአውሮፓ የልማት ባንክን ጨምሮ የቱርክ፣ የደቡብ አፍሪካ የኬንያ ግዙፍ ባንኮች በዚሁ ዘርፍ ተሰማርተው የሚገኙ ሲሆን፣ ባንኮቹ ለመንግስትና ለግል ኩባንያዎች ብድርን እያቀረቡ እንደሚገኝ ታውቋል።

በአሁኑ ወቅት የሃገሪቱ ጠቅላላ የእዳ ክምችት ከ36 ቢሊዮን ዶላር በላይ መድረሱን የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የአለም አቀፍ ሞኒተርኒንግ ፈንድ (IMF) የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገት ቀድሞ ከተተነበየለት የባለሁለት አሃዝ እድገት ወደ 4.5 በመቶ ሊያሽቆለቁል እንደሚችል ይፋ ማድረጉን ቢቢሲ ዘግቧል።

የሃገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት በተያዘው በጀት አመት በ10 አመት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ማሽቆልቆል ማሳየቱን ለንባብ ያበቃው የዜና አውታር ባለፈው አመት በኦሮሚያ ክክል የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ በኢኮኖሚ እንቅስቃሴው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን አመልክቷል።

በዚሁ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሁኔታ ዙሪያ ተመሳሳይ ሪፖርትን ያቀረበት አፍሪካ ኒውስ መጽሄት በበኩሉ መንግስት በቅርቡ ያስቀመጠው የ11 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት ሲሳካ እንደማይችል የተለያዩ መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ አርብ ለንባብ አብቅቷል።

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s