በእስራዔል በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ህጻናት ላይ የተፈጸመ የግርዛት ልምምድ ድርጊት ቁጣን ቀሰቀሰ

Circumcision

http://www.jpost.com/Israel-News/Politics-And-Diplomacy/MKs-slam-ministry-Chief-Rabbinate-over-circumcision-scandal-474542

ሰሞኑን በእስራዔል በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ህጻናት ላይ የተፈጸመ የግርዛት ልምምድ ድርጊት በሃገሪቱ የፓርላማ አባላትና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ ቁጣን ቀሰቀሰ።

አንድ ታዋቂ እስራዔላዊ የህክምና ባለሙያ ተማሪዎቹ ያለምንም ዕውቀት የግርዛት የትምህርት ልምምዳቸውን አነስተኛ ገቢ ካላቸው የኢትዮጵያና የሱዳን ማህበረሰብ ህጻናት ላይ እንዲያካሄዱ ሲያደርግ የቆየው ድርጊት በእስራዔል ፐብሊክ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን መጋለጡን መዘገባችን ይታወሳል።

ይህንኑ ድርጊት ተከትሎ በጉዳዩ ዙሪያ የሚመክር መድረክ የተካሄደ ሲሆን፣ በፕሮግራሙ የታደሙ የፓርላማ አባላትና የተለያዩ የማህብረሰብ ክፍሎች በድርጊቱ ቁጣቸውን እንደገለጹ የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

በዚሁ መድረክ የተሳተፉትና በእስራዔል የመጀመሪያዋ ሴት የፓርላማ አባል የሆኑት ፒኒና ታማኖ-ሻታ በጥቁር አይሁዳዊያን ላይ አድሎ እየተስፋፋ መምጣቱን በቁጣ ገልጸዋል።

በቅርቡ በኢትዮጵያውያንና ሱዳናዊያን ላይ የተፈጸመውን ድርጊት አጥብቀው የኮነኑት የፓርላማ አባሏ ቁጣቸውን ለመግለጽ ሲሉ የውይይት መድረኩን ረግጠው መውጣታቸው ታውቋል።

እንዲህ ያለ ድርጊት በአውሮፓ አይሁዶች ላይ ተፈጽሞ ቢሆን ኖሮ ሁላችም ድምጻችንን በአለም ዙሪያ እናሰማ ነበር ያሉት ፒኒና ታማኖ፣ ጥቁር በመሆናችን ትኩረት አልተሰጠንም ሲሉ ቁጣቸውን አሰምተዋል።

ነዋሪነታቸው በሃገሪቱ የሆነ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከ30 አመት በላይ የህጻናት የግርዛት አገልግሎትን ሲሰጡ የነበሩት መምህር ኤሊያሁ አሱሊን ተማሪዎቻቸው በህጻናቱ ላይ ልምምድ እንዲያደርጉ ማድረጋቸው ከፍተኛ ሃዘን እንዳሳደረባቸው እየገለጹ ይገኛል።

ጸያፍ ቃላቶችን እየተጠቀሙ ተማሪ መስሎ ለቀረባቸው አንድ የምርመራ ጋዜጠኛ የፈጸሙትን ድርጊት በቪድዮ ያስረዱት መምህሩ የሁለቱ ሃገራት አይሁዶች ማንም የተለያዩ ሙከራዎችን የሚፈጽሙባቸው ናቸው ሲሉም ተደምጠዋል።

መምህሩ ለተማሪዎቻቸው የሃሰት ሰነድን በማዘጋጀት ተማሪዎች ልምድ ያላቸው በማስመሰል ህጻናት ላይ ደረጃውን ያልጠበቀ የግርዛት አገልግሎት እንዲሰጡ ሲያደርጉ መቆየታቸው የእስራዔሉ ፐብሊክ ብሮድካስቲንግ ኮርምፖሬሽን ለህዝብ ይፋ ባደረገው ሪፖርቱ አጋልጧል።

የእስራዔል የኢሚግሬሽን ኮሚቴ ሊቀመንበር የሆኑት አብርሃም ቢተን በበኩላቸው ሰሞኑን የተፈጸመው ድርጊት በሁለቱ ሃገራት ማህበረሰብ ላይ መድሎ እየደረሰ ስለመሆኑ ማሳያ ነው ሲሉ አስታውቀዋል።

በህጻናቱ ላይ የግርዛት ልምምድን ሲያካሄዱ የነበሩት ተማሪዎች ለትምህርታቸው እስከ 10 ሺ ዶላር የሚደርስ ክፍያን ይፈጽሙ እንደነበር ጀሩሳሌም ፖስት የተሰኘ የእስራዔል ጋዜጣ ዘግቧል። ነዋሪነታቸው በእስራዔል የሆነ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ ጊዜያት ደርሶብናል ያሉትን የዘር መድሎ ድርጊት በመቃወም የተቃውሞ ትዕይትንት ሲያካሄዱ መቆየታቸው ይታወሳል።

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s