ከሰማያዊ ፓርቲ አቶ የሺዋስ አሰፋ በአቶ ይድነቃቸው ከበደ በተፈረመ ደብዳቤ፤ ምክር ቤቱ ሳያፀድቀው ለምርጫ ቦርድ አስገባ

የአቶ የሺዋስ አሰፋ እና የተወሠኑ የአፍራሽ ተልዕኮ ያላቸው ግለሠቦች “ጠቅላላ ጉባኤ” በመስከረም 28/2009 ዓ.ም ተካሄደ ከተባለ በኃላ ፤ አቶ የሺዋስ አሰፋ ስራ አስፈፃሚዎቼ ናቸው ያላቸውን ኮሚቴዎች ስም ዝርዝር፤ በአቶ ይድነቃቸው ከበደ በተፈረመ ደብዳቤ፤ ምክር ቤቱ ሳያፀድቀው ለምርጫ ቦርድ አስገብቷል። ከገቡት የስም ዝርዝሮች ውስጥ ከታች ቅጂው ተያይዞ ባለው ለምርጫ ቦርድ በተላከው ደብዳቤ፥ በተራ ቁጥር 1. ላይ ያሉት ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ እና በተራ ቁጥር 9. ላይ የምትገኘው ወ/ሪት ብሌን መስፍን ከፓርቲው አባልነት ራሣቸውን ያገለሉ ናቸው። የዶ/ር በቃሉ አጥናፉን ወደ ጎን ትቼ፤ ፓርቲ ውስጥ በነበረችበት ወቅት በምትችለው ሁሉ በተግባር ትሣተፍ ወደ ነበረችው ጓዴ ብሌን መስፍን ይህን ልበል። ወ/ሪት ብሌን መስፍን ከፓርቲው መልቀቋን በፌስ ቡክ ፔጇ ከገለፀች በኃላ፤ ለፓርቲው የመልቀቂያ ደብዳቤ ከማስገባቷ በፊት በግሌ አግኝቻት አውርቻት ነበር። ‹‹ በፓርቲ ከምወከል ይልቅ ፥ በህዝብ ብወከል ይሻላል። ያለው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ( በምክር ቤቱ የመተማመኛ ድምፅ የተነፈገው) ተሟልቶ መስራት ካልቻለ፤ በተጓደለ ሁኔታ እስከመቼ ? ›› ብላኝ ችግሩ ላይ ተስማምተን መፍትሄው ላይ ሳንስማማ ፤ ውሳኔዋን ግን አክብሬ ተለያይተናል ። የአቶ የሺዋስ አሰፋ ጠቅላላ ጉባኤ ሲካሄድም ደውለውላት ተገኚ ሲሏት ፤ ‹‹ከፓርቲው መልቀቄን እያወቁ እንዴት ይደውላሉ? ›› ብላ በስልክ አውርታኛለች ። ይሁን እንጂ እፍረት የሚባል ነገር ያልፈጠረባቸው አቶ የሺዋስ አሰፋ እና ፤ በፍቅረ ንዋይ የተታለሉት ግብረ አብሮቹ በኮማንድ ፓስቱ ቁጥጥር ስር ያለችውን ብሌን መስፍንን ስለ ራሷ ምንም ማለት በማትችልባት ሁኔታ የሴቶች ጉዳይ ሃላፊ አድርጎ ሾሞዋታል። ይህን ዜና በገዢው ስርዓት ድጎማ ከሚታተመው ሰንደቅ ጋዜጣ እንዳነበብኩ ፤ ብሌን በጊዜያዊነት ታስራበት ወደ ነበረው ላዛራሲት ፓሊስ ጣቢያ ሄጄ ያለውን ጉዳይ አጫውቻት ፤ አቋሟን ጠይቄያት ነበር። ቃል በቃል ‹‹ የፓለቲከኛ እስረኛ ሆኜ፤ መቼ ከእስር እንደምፈታ እንኳን ሳላውቅ ፤ ያውም ለቀቅኩ ባልኩበት ፓርቲ፥ እንዴት ስራ ልስራ ብዬ እሺ ልል እችላለው ? ›› ብላ በቁጣ ያለውን እውነታ ነግራኛለች። የአንድ ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እንደ ፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ፤ በፓርቲው ውስጥ ይሁንታ ካገኘና ከፀደቀ በኃላ፥ ለምርጫ ቦርድ ደብዳቤው ሲገባ፤ ከደብዳቤው ጋር የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በስራ አስፈፃሚነት ለመስራት መስማማታቸውን የሚገልፅ፥ በፊርማቸው የተረጋገጠ ደብዳቤ ተያይዞ በአባሪነት መግባት አለበት። የፓርቲዎች የምዝገባ አዋጅ 573/2000 ይህን ያስገድዳል። የፓርቲያችን መተዳደሪያ ደንብም አንቀፅ 26 ንዑስ አንቀፅ 6 ፦በብሄራዊ ምክር ቤቱና በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ውሳኔ መሠረት የሚወጡ ደብዳቤዎችና ሰነዶች ላይ ሊቀመንበሩ ይፈርማል ይላል። ይሁን እንጂ መፈረም የማይገባው ሰው የፈረመበትን ደብዳቤ ፓርቲዎች እግር ሲያወጡ ሊቆርጥ የሚቋምጠው ስርዓት፤ በአንድ ምርኩዙ ምርጫ ቦርድ በኩል ደብዳቤውን ሆን ብሎ ሳያጣራ ተቀብሏቸዋል። አቶ የሺዋስ አሰፋ ከነግብረአበሮቻቸው በስልጣን ጥም ሰክረው በሰማያዊ ውስጥ ሆነው ለገዢው ፓርቲ ከሚሰልሉ የስርዓቱ የደህንነት ሰዎች ጋር ፓርቲውን ለማፍረስ ዳር ተዳርሰዋል።የማውቀውን እውነት ማንንም ሳልወክል እንደ ምክር ቤት አባልነቴ እያጋለጥኩ ስለሆነ እና ምርጫ ቦርድም ሆነ ፓሊስ ጣቢያ መፍትሄ እንደማይኖር እያወቅኩም ቢሆን ለታሪክ ብዬ ጉዳዩን በቅርብ ስለምከታተል ዛሬ ማታ ወደ ቤቴ ስገባ “አርፈህ ተቀመጥ” የሚል ዛቻና ማስፈራሪያ በደህንነት ሠዎች ተልኮብኛል። ይህን የማጋለጥ እና ፓርቲ ውስጥ የተፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት ከሁሉም የፓርቲው መዋቅር ጋር በአባልነት ተደራጅተው ይሰሩ የነበሩት የአባላት ጊዚያዊ አስተባባሪዎች አቶ ጠና ይታየውና አቶ አወቀ ተዘራ ታስረዋል። የአስተባባሪዎቹ ሰብሣቢ የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ አሰፍም ደህንነቶች አስፈራርተውት ከፓርቲው እንዲርቅ ሁኗል። እውነት ነፃ ታወጣለችና ከማውቀው እውነት ሊገፋኝ ከሞከረ ማንኛውም የውሸት ተራራ ጋር እስከመጨረሻው መፋለሜን እንደማላቆም ይታወቅልኝ። ኢትዮጵያ የእውነት አገራቸውን የሚወዱ ሠዎች የሚገፉበት ሣይሆን የሚከበሩባት ፣ የህገወጦች መናኽሪያ ሣይሆን ፍትህ የሚሠፍንባት አገር እስክትሆን ድረስ ትግሉ ይቀጥላል !!! ( ለመረጃ ያህል ፦ በአቶ የሺዋስ አሰፋ በኩል ለሥራ አስፈፃሚነት ከተመረጡት አስሩ ሠዎች መካከል ሁለቱ ሠዎች በራሣቸው የእጅ ፅሁፍና ፊርማ ፓርቲውን የለቀቁበት ደብዳቤ ቅጂና አቶ የሺዋስ አሰፋ ለምርጫ ቦርድ ያስገቡት ደብዳቤ ቅጂ ተያይዟል። የውጭ ጉዳይ ሃላፊ ሆነው የተሾሙትም አቶ አበበ አካሉም እስር ቤት መሆናቸው ይታወቃል ) ።

 
Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s