ስቴት ዲፓርትሜንት ከዚህ በፊት የሰጠውን ማስጠንቀቂያ ዛሬ በአዲስ ማስጠንቀቂያ ተካው።

ወያኔ ያወጣው የ 6 ወር አስቸኳይ አዋጅ ዜጎችን ካለፍርድ ቤት ትእዛዝ የማሰር መብትና ሌሎችንም እርምጃ የመውሰድ መብት ያጎናፀፈው መሆኑን በማስገንዘብና ህገ ወጥ ድርጊቶች ብሎ የሰየማቸውን ለምሳሌ ከሁለት በላይ ሁኖ አንድ ላይ ቆሞ መነጋገር፤የተለያዩ የመገናኛ መንገዶችን መጠቀም፤በስብሰባ መሳተፍ፤ ከተለያዩ የውጭ አገር መንግሥታትና ድርጅቶች ጋር መገናኘት(መነጋገር) የሰዓት እላፊ ገደብን ማለፍ እና ሌሎችንም ያልተጠቀሱ ተግባሮችን ምክንያት በማድረግ የአሜሪካ ዜግነት ያላቸውን ጭምር መታሰራቸውን እንኳን ለአሜሪካን ኢምባሲ ሳያውቅ ሊአስር እንደሚችል ጨምሮ ገልጿል።

ኢትዮጵያ  የኢንተርኔትና የተንቀሳቃሽ (mobile telephone) አገልግሎቶችን ካለምንም ማስጠንቀቂያ በየጊዜው ገደብ ስለምታደርግ ወይንም ሙሉ በሙሉ ስለምትዘጋ የአሜሪካ ኢምባሲ ኢትዮጵያ ካሉት ዜጎቹ ጋር ያለውን ግንኙነት እንደገደቡት ገልጿል። በመሆኑም አማራጭ የግንኙነት መስመር እንዲፈጥሩና ይህንንም አማራጭ የመገናኛ መንገድ ቤተሰቦቻቸውና የቅርብ ጓደኞቻቸው እንዲአውቁት እንዲአደርጉ አሳስቧል። ያልታሰበ ክስተት ሊከሰት እንደሚችልም በመግለፅም ጭምር ነዉ ማሳሰቢያውን የሰጠው።

ከላይ ከሰጠው ማሳሰቢያ በተጨማሪ ሰልፎችንና ስብሰባዎችን እንዲአስወግዱና አካባቢአቸውን በመመልከት የደህንነት ሁኔታቸውን እንዲገመግሙ አስጠንቅቋል። ያስጠነቀቀው ሰላማዊ የሆነውም ስብሰባ ሳይቀር በጥይት የሕይዎት ዋጋ እንደሚአስከፍልም አስረግጦ በመናገርም ጭምር ነው። በመሆኑም ድንገት በሚፈጠረው ሁኔታ በአስቸኳይ መዉጣት አስፈላጊ ሁኖ ሲገኝ ለመዉጣት ተለዋጭ አማራጭ እንዲአዘጋጁ መልእክቱን አስተላልፏል።

ሊጨበጥ ባልቻለዉ ተለዋዋጭ የአገሪቱ መገናኛ መንገድ ችግር የተነሳ ሊፈጠር የሚችለዉን ችግር ለማስወገድ የተንቀሳቃሽ የእጅ ስልክ ቁጥራቸውን ለአሜሪካ ኢምባሲ ማስመዝገቡ ስለሚፈጠረው ሁኔታ በቴክስት ከኢምባሲው መልእክት ለማግኘት እንደሚረዳ በመግለፅ ስልካቸውን ለኢምባሲው እንዲአስመዘግቡ አሳስቧል።1r tu kiflehager

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s