አሜሪካ እና አውሮፓ ያለነው አሁን የቻልነውን ማድረግ የምንችል ይመስለኛል!!!

አሜሪካ እና አውሮፓ ያለነው አሁን የቻልነውን ማድረግ የምንችል ይመስለኛል!!!

በኮማንድ ፖስቱ እስካሁን ድረስ የታሰሩት ብዛት ከአስራሁለት ሺ በላይ መሆኑን የኮማንድ ፖስቱ ተጠሪ ለፋና ገልጸዋል። በምርጫ መቶ በመቶ ተመረጥኩ የሚለው ህውሓት አመት እንካን ሳይሞላው ከአስራሁለት ሺ በላይ ዜጎቻቻን አስረዋል።

ዛሬ የተመስገን ደሳለኝ ወንድም ቃለመጠይቅ ሰማሁት። ተመስገን የት እንዳለ ያላወቁት ቤተሰቦቹ ከአስር ቀን ቦሃላ አግኝተዉታል። የተመስገን ደሳለኝ በሂወት መኖር የሰሙት እናቱ እልል በማለት ፈጣሪያቸውን አንድ ነገር ለመኑት “ብሞትም ልጄን እንዲቀብረኝ ቢለቁልኝ” ይህ አባባል እናት ለሆኑት ምን ያህል ትርጉም እንደሚሰጥ ለማወቅ ከባድ አይደለም። ከዚህም በተጨማሪ ተመስገን በጨጓራ በሽታ እየተሰቃየ መሆኑን ተናግረዋል።

የዛሬ ጥያቄየ አሜሪካ እና አውሮፓ ለምንኖር ኢትዮጵያውያን ነው። የተመስገን ቤተሰቦች ተመስገንን ለመጠየቅ ወደ ዝዋይ ይመላለሳሉ። አዲስ አበባ ዝዋይ ምን ያህል ወጪ እንደሚያስወጣ ለማናችንም ድብቅ አይደለም። በማህበራዊ ሚድያ የምናቃቸው ወድሞቻችን እና እህቶቻችን ለእስር ተዳርገዋል። በቅርቡ ከታሰሩት ውስጥ ስዩም፣በፍቃዱ፣ኤልያስ፣አናንያ፣ዳኒኤል፣ወይንሸት እና መሰሎቻቸው ይገኛሉ። አሜሪካ እና አውሮፓ የምንገኝ ፍትህ ፈላጊዎች ለነዚህ ወንድሞቻችን እንዴት እንድረስላቸው። አሜሪካ እና አውሮፓ የምንኖረው ማድረግ የምንችለው በገንዘብ መርዳት ብቻ ነው።

አሁን በኮማንድ ፖስቱ ለእስር የተዳረጉት በሙሉ ቤተሰቦቻቸው ለችግር ተጋልጠዋል። ኤልያስ ቤተሰቦቹ ከክፍለሃገር እየመጡ ያዩታል ስንቅ ያቀብሉታል፣ ዳኒኤልም ገቢ የለውም ቤተሰቦችም ችግር ላይ ናቸው፣ ሁሉም በመንፈስ ጠንካራ ቢሆኑም ጥለዋቸው የሄዱት ቤተሰቦቻቸው ግን ችግር ላይ ናቸው። ስለዚህ አሜሪካ እና አውሮፓ የምንኖር ኢትዮጲያውያን ምን እናድርግ? አጋርነታችን በምን እናሳይ!!! እነሱ አገርቤት ሆነው ሲታሰሩ ፣ሲቀጠቀጡ፣ ሲሰቃዩ ይህንን ሁሉ መስዋእትነት ሲከፍሉ እኛ አሜሪካ እና አውሮፓ የምንኖር ምን እናድርግ። መልሱ እኔ እና ጥቂቶቹ ብቻ ሳንሆን ሁላችን የምንመልሰው ጥያቄ መሆን አለብት። ለሚገደሉ ለሚሰቃዩ ለሚቀጠቀጡ ወንድሞቻችን ምን እናድርግ?መፍት ሄ ያልኩትን ከስር ለማስቀመጥ መኩራለሁኝ።

አሜሪካ እና አውሮፓ ያለነው አሁን የቻልነውን ማድረግ የምንችል ይመስለኛል። አዲሱ አመት ከመግባቱ በፊት ካለችን አካፍለን ሊንደርስላቸው የምንችል ይመስለኛል። በእስር የተዳረጉት ወንድሞቻችን እስር ላይ ሆነው በቀን ሰዎስቴ ምግብ የሚያመላልስላቸው ይፈልጋሉ፣ ሄደን ማድረስ ባንችልም እንኳን የቻልነው በመርዳት ማድረስ እንችላለን። አራት መቶ ሰዎች አስር አስር ዶላር እንካን ብናዋጣ ለስምንት ሰዎች በቂ ነው ብየ አምናለሁኝ (400 * $10=4000/8= $500 each)።አሜሪካ እና አውሮፓ የምንኖር ኢትዮጲያውያን አዲሱ አመት ከመግባቱ በፊት እስኪ የቻልነውን እናድርግ ወይንም ምን ማድረግ እንዳለብን እንነጋገር።

Image may contain: 1 personImage may contain: 1 person, close-upImage may contain: 1 person, close-upImage may contain: 1 person
Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s