የአማራ ተጋድሎ እና ግንቦት ሰባት እና ደምሂት -ርስቴ ተስፋዬ

የአማራ ተጋድሎ እና ግንቦት ሰባት እና ደምሂት
ርስቴ ተስፋዬ
የአማራ ህዝብ ትግል የህልውና ጉዳይ ነው! የመኖር ወይም ያለ መኖር ጉዳይ ነው! ከግንበት ሰባት እና ደምሂት ጋር ሚያገናኘኝ ነገር አልነበረም!!! በእርግጥ ግንቦት ሰባቶች ሁለገብ ትግል ሲሉ ፥ ለማጭበርበር እንዲመቻቸው እና ክሽፈታቸውን ለመሸፈን ሲሉ የዘተዱት ዘዴ እንጂ ፥ አንድ የትግል አቅጣጫ ይዘው TPLF’ን በተፋለሙ ነበር ። አይፋለሙም ፥ አይችሉም ፥ የሉም ! ኮሽ ባለፈው ቁጥር እኛ አለንበት ፥ ጥይት በጮኸ ቁጥ የኛ ነው እያሉ ፥ የህዝብ ትግልን ማደናቀፋቸው ሳያንስ ፥ ከዚህ የማጭበርበር ትግኣቸው በተጨማሪ ፥ መሬት ላይ በሚታገሉት የአማራ ታጋዮች እና የአማራ ትግል ላይ የፈጠሩትን ችግር ህዝብ ያውቀው ዘንድ ላስቀምጥ
1ኛ የሰው ሀይል ሲደመር አንድ ክፍለጦር እና ከባድ መሳሪያ እናስገባለን በሚል በቴሌኮንፈረንስ እንወያይ በማለት አስማረ ብሩ በተባለ ግለሰብ አማካኝነት ( የማጭበሪያ ስሙ ደሞ ሞላ ይግዛው ) አድራሻ sweden stockholm Skogas, የሚኖር ሰው ፥ ይህንን ስልክ ቁጥር 00467070121171 በመጠቀም ፥ ብርሀኑ ነጋ በተገኘበት የሚስጢር ኮንፈረንስ ፥ አቶ አስማረ የTPLF ደህነቶች እንዲገቡ በማድረግ የከፋኝ አማራ አመራሮች በTPLF ለማስበላት እና የአማራን ትግል ለማኮላሸት ያደረጉት ሴራ አንዱ ነው ።


2ኛ ተስፋሁን የሚባለውን ሰው ይህ አስማረ የተባለ የህውሃት እና የግንቦት ሰባት ቁልፍ ሰው ፥ ስልክ ደውሎ በማነጋገር ፥ ብሎም በገንዘብ በመደለል በኢሳት ወቶ እንዲናገር ፥ አልፎ ተርፎ የአማራ አርበኞች ግንበት ሰባት ጋር አብረን እየሰራን ነው የሚል የቅጥፈት ፕሮፖጋንዳ እንዲነዛ በማድረግ ፥ ከግንቦት ሰባት ጋር አንድ ላይም ሆነናል ብሎ እንዲናገር አደረጉት ።

በዚህ ሁኔታ የተቆጡት የአማራ አርበኞች ተስፋሁንን ስለማናውቀው ግንቦት ሰባት ፥ በሌሉበት ፥ ከኛ ጋር ፍፁም ባልቆሙበት ፥ ለአፍ ፖለቲካቸው ስትል እንዴት ትሰጣለህ ብለው የከፋኝ አማራ አመራር እና ሰራዊት ጥያቄ ያቀርቡለታል ፥ ይህንንም ጥያቄያቸውን ያልወደደው ተስፋሁን ከግንባሩ ጠፋ። በደህና እየሰሩ ያሉቱን ታጋዮች ግንቦት ሰባት ለተራ ፕሮፖጋንዳ ሲል በገንዘብ እየደለለ ይከፋፍላቸው ገባ ። ይህንን ተከትሎ ከሁለት ቀን ቡኋላ TPLF በአማራ ህዝብ ዘመቻውን ቀጠለ። የገበሬዎችን ማሳዎች እና ቤቶች አቃጠለ! አሸባሪዎች ሻቢያ እና ግንበት ሰባት ገቡብኝ በማለት ፥ እንደተለመደው ግንቦት ሰባትን ለዱላነት ( አማራውን ለመምቻነት ) ተጠቀመበት ፥ ግንቦት ሰባቶች በሌሉበት ይህንን ድራማ የተጠቀሙት እንደነሱ ከተቻለ ትግሉን ለመንጠቅ ፥ ካልተቻለ የአማራ አርበኞች በ TPLF ዱላ ሲበዛበት ሳይወድ በግድ ግንቦት ሰባትን እንደ መጠጊያ እና መሸሻ ለማድረግ ነው ። በዚህም የአማራን ትግል ለማስመታት እና ትግሉን ከተቻለ ቀልብሶ የግንቦቴዎች ትግል ለማድረግ ነው ።

ለዚህ ግንቦት ሰባት በተለያየ ወቅት የአማራ አርበኞች መሪዎችን ፈልጎ ካገኘ በኋላ ፥ የገንዘብ እና የቁስ እርድታ አደርጋለሁ እያለ ፥ እያባበለ አስር እና አምስት ሺ ዶላር እየላከ ከኛ ስር ካልሆናችሁ የሚቀጥለውን ገንዘብ ለመላክ ድርጅታችንን ለማሳመን ይከብደናል እያሉ በርሃ ከወያኔ ጋር እየታገሉ ያሉ ወገኖቻችን ላይ ይቀልዳሉ ። ይህንን ጉዳይ ህዝብ ይወቅልን !
ነጋዴዎች ወታደሮች ሲሆኑ የሚመጣው ችግር ይህ ነው ። ድለላ እና ትግል ይለያያል !
ክብር ለጀግኖቹ የአማራ አርበኞች !
ርስቴ ተስፋዬ

17ac1-war

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s