በ2002 ምርጫ ኢትዮጵያን ለቆ የተሰደደው፡ ግንቦት ሰባትን በሱዳን እያደራጀ እንደነበር በሃገር መክዳት ክስና ምስክር የቀረበበት፡ የቀድሞው ኢዴአፓ ሊቀመንበር፡ የስዊድን የግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ግንቦት ሰባትን በይፋ መልቀቁ እየተነገረ ነው መባሉ ትልቅ ውሸት የወያኔና የወያኔ ባንዳዎች ወሬ ስለመሆኑ ተነግራል
አቶ ዘለሌ ፀጋሥላሴ የስውዲን የግንቦት 7 ሰብሳቢ ከተወራው ድርጅቱን መሠናበት ጋ ምን ይላል ? ጥቅሙ ምን ይሆን ? ዛሬ በጥዋት የአቶ ዘለሌ ፀጋ ሥላሴን ከግንቦት 7 መልቀቅ እየተቀባበሉ ሲለጥፉ አይቼ ለአቶ ዘለሌ እየተወራ ያለው ምንድነው ብዬ ጠይቄው ነበር አቶ ዘለሌም 100% ውሸት ነው ሥራዬን እየሠራሁ ነው።” ከትግሉ ሊያስቀረኝ የምችል ምድራዊ ኃይል አይኖርም ” ብሎኛል የሚያስገርመው ከእውነት ባፈነገጠ መልኩ ይህን ያህል መሄድ ለማን ጥቅም ይሆን ?
Zelelie Tsegaselassie
ለነፃነት ትግሉ በአርበኞች ግንቦት 7 ውስጥ በአንድ ሃገር ብቻ ሳይሆን ከዚያም ባለፈ አቅሜ የፈቀደውን ሁሉ አስተዋፅኦ ( full Participation) እያደረኩ ነው ።
” በዙሪያዬ ባሉ የግል ጉዳዬች ምክንያት በዋናው የትግል ስፍራ በግንባር መገኘት ያለመቻሌ ለጊዜውም ቢሆን እንቅልፍ የነሳኝ ቢሆንም “
በተረፈ ወድጄና ፈቅጄ የተቀላቀሉት አርበኞች ግንቦት 7 ከመቼውም ጊዜና ከየትኛውም ስብስብ በተለየና በተሻለ ሁኔታ ሃሳብን በነፃነት የማንሸራሸር መብት የተለመደ ባህል የሆነበት ስብስብ መሆኑን ላረጋግጥ እወዳለው ።
ከነፃነት ትግሉና ከንቅናቄው ተሳትፎ የሚነጥለኝ ምድራዊ ኃይል ይኖራል ብዬም አላስብም ።
ጊዜው የትግባርና የተግባር ብቻ ነው !!